Monday, November 16, 2009

ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለ ዕዳው አይሸከመውም !

ክህነትን አክብሮ ለመረጣቸው ሰዎች የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፡፡ ክብሩም ታላቅና ዘለዓለማዊ ነው፡፡ከእግዚአብሔር በተሰጠ የክህነት ስልጣን ሕዝብ ይገለገላል ፤ ይባረካል፡፡የሰው ልጆች በደልና ኃጢኣትም በክህነቱ አገልግሎት ይሥተሠረያል፡፡ከዚህ አንጻር የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ለካህናት አባቶች ከፍተኛ አክብሮት አለን፡፡

ይሁን እንጂ በሃገራችን ኢትዮጵያ ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ባሉ ካህናት አባቶች መካከል የሚታየው ያአለመግባበትና አብሮ የመሥራት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰና እያደገ በመምጣቱ ችግሩ ባህር ማዶ በመሻገር አለም አቀፋዊ እየሆነ መጥቶአል፡፡

ከዚህ የተነሣ የክህነቱን ክብር እያቀለለውና በምእመናንም ዘንድ እንዲናቅ እያደረገው ነው፡፡ እንደሌላው ቦታ ሁሉ በዚሁ በደብራችን የምናየው የካህናት አንድ አለመሆንና መከፋፈልም አንዱ ተጠቃሽ ነው፡፡ይህ ለምን ሆነ ? መሆን አልነበረበትም አንልም፡፡ ይህን ለማለት እንዳይቻል ደግሞ ወደ ኋላ መለስ ብለን ታሪክን ስንመለከት ከሐዋርያት መካከል ይሁዳ ፣ ከሊቃውንትም መካከል እነ አርዮስና ሌሎችም እንክርዳድ እየሆኑ እየወጡ የተጠሩበትና የተቀበሉትን ሥልጣነ ክህነት አርክሰው እንደጠፉበት ታሪክ ይነግረናል፡፡

ዛሬም የምናየውን ችግር ያመጣው አንደኛው የዚህ ነጸብራቅ ሲሆን ሌለኛው ደግሞ በዘመናችን ያለውትልቁ ችግር የገንዘብና የሥልጣን ፍቅር ነው፡፡ ከእነዚህ በአንደኛው የተለከፈ ሰው በቤተክርስቲኑዋን ውስጥ በሰላም ይኖራል ፤ ሌላውንም ሰው ያኖራል ለማለት አያስደፍርም፡፡
ሃይማኖትና ፍርሃተ እግዚአብሔር ያለው ካህን ለክህነቱና ለሃይማኖቱ ብሎም ለሰብአዊ ክብሩ (ለስሙ) ሲል ይጠነቀቃል፡፡ጥቅምና ገንዘብ የሚገኙበትን ቦታዎች የሚያውቅ ቢሆንም እንኩዋን ገንዘብ፤ጥቅምና ሥልጣን ከሚያመጡት ችግሮች ለመራቅ ይሞክራል፡፡
ይህ የማይታየውና ገንዘብ፤ጥቅምንና ሥልጣን የሚገኙበትን ሥፍራ በጽኑ እየፈለገ የሚከተል ካህን ደግሞ ጥቅሙን ያግኝ እንጂ ቀድሞም ቢሆን ይሁዳ ፈጣሪውን ለ30 ብር አሳልፎ እንደሰጠ ይህም ሰው ወዳጆቹንና ወገኖቹን ለገንዘብ ሲል አሳልፎ ለመስጠትና ለማጥፋት ወደኋላ አይልም፡፡ ‹….መጨረሻቸው እንደ ሥራቸው ነው ! › እንደተባለ የዚህ ዓይነት ሰው ፍጻሜው የሚያመር አይሆንም ፡፡
ካላይ በርእሱ ወደተቀመጠው ዝርዝር ጉዳይ ለመመለስ አዲት እህት በደብራችን ካሉ አንድ አዛውንት ካህን ጋር ባደረገቸው ቆይታና የደረሰባትን ቅሬታ መሠረት በማድረግ እንነሣ፡፡ የሌሎች ምዕመናንንም አስተያየቶች አክለን ካህኑ ይህን ተረድተው ከቻሉ ስህተታቸውን እዲያርሙ በማለት አቅርበነዋል፡፡

ካህኑ በቀና አመለካከት ቢመለከቱትና ቢስተካከሉ እራሳቸውን ይጠቅማሉ፡፡ ቤተክርስቲያኗንና ክህነቱንም ከማስነቀፍ ያድናሉ ፡፡

አንዲት ወጣት ሴት ብሶቷን ‹እኚህ አዛውንት ቄስ ጠዋትም ማታም በቤተክርስቲያን ሳያቸው ፍጹም ጸሎተኛና ትልቅ ሰው ይመስሉኝ ነበር፡፡ ግን መሆናቸውን ተጠራጥሬአለሁ፡፡ ብዙም ነገር ታዝቤአለሁ ፡፡ለግል ጉዳዬ፤ መንፈሳዊ አገልግሎት ፈልጌ ለነጋግራቸው ቢሮአቸውን አንኩዋኩቼ ገባሁ፡፡ ስገባ ግን የእጅ ስልክ ላይ ነበሩ ፡፡ ስልኩን ለሚያወራው ሰው ‹ጉዳዩ ብዙ ነው ፤ በስልክ የምንጨርሰው አይደለም ፡፡ በል ስንገናኝ እናወራለን አሁን እንግዳ መጥቶብኛል፡፡› ብለው ዘጉ፡፡ እኔም እንዲሁ በርቀት እንጂ ያለ እዚያን ቀን ቀርቤአቸው አላውቅም፡፡እርሳቸውም ቢሆኑ እርግጠኛ ነኝ አያውቁኝም፡፡ እጅ ነስቼ ከገባሁበት ሰዓትና መስቀል ተሳልሜ ከተቀመጥኩበት ደቂቃ ጀምሮ ለምን እንደመጣሁ ሳይጠይቁኝ በቀጥታ ጉዳዩን በስልክ ሲያወሩት ከነበረው አጀንዳ ጋር አያይዘው ወሬ ጀመሩ፡፡ ያወራሉ፤ያወራሉ፤ ያወራሉ… ፡፡ የሚያወሩት ነገር ማለቂያ የለውም፡፡መነሻውን ባውቀውም መድረሻው የት እንደሚሆንና መቼ እንደሚያቆሙ ናፈቀኝ፡፡ አንዴ ስለ ከሳሾቹ ፤ አንዴ ስለሌሎቹ ካህናት፤ አንዴ ስለቦርድ አምላክነት፤ አንዴ ስም እየጠሩ ስለእነ እገሌ ያወራሉ ፤ ያወራሉ ….በመጨረሻም የሄድኩበትን ጉዳይ ለመናገር ምንም እድልና ጊዜ ሳላገኝ ውስጤ ይሉኝታና ንዴት እንደሞላበት ‹ በይ ልጄ መሸ፤ እናቴም ትጠብቀኛለች (ባለቤታቸውን ማለታቸው ነው) ያንቺን ጉዳይ በሌላ ጊዜ ነይና እንነጋገራለን› ብለው ቀጠሮ ሰጥተውኝ ወጣሁ ፡፡ በከንቱ ያለ ሥራ ያጠፋሁት ጊዜ ቆጨኝ፤ አንገበገበኝ፡፡ ያለማጋነን ሲያወሩ የነበረው ሁለት ሰዓት ያህል ይሆናል፡፡በዚያ ሰዓት እኔ መስማት የምፈልገው ከችግሬ አንጻር የሚያጽናና የእግዚአብሔር ቃል እንጂ እንቶ ፈንቶ ወሬ አልነበረምና በጣም ተበሳጨሁ፡፡በስልክም ቢሆን አንድ ካህን ፈልጌ ዛሬውኑ ማነጋገር አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡ እኔም ቁጥር አፈላልጌ ከሌሎቹ ካህናት ወደ አንዱ በመደወል ችግሬን በመናገር የምፈልገውን መረጋጋት አግኝቼ ያቺን ቀን አለፍኩ፡፡ › በማለት ትገልጻለች፡፡

የምእመናንን ችግርና ጭንቀት በማረጋጋት ለማስወገድ ክህነቱ የሚጠይቀውን መንፈሳዊ ግዴታ በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችልና ተወቃሹም ካህን ይህንና ሌሎች ስህተቶቻቸውን ማረም እንዲችሉ ፤ ሌሎቹም ካህናት ከዚህ ትምህርት ቀስመው ምእመናንን በጥንቃቄ ለማገልገል እንዲረዳቸው በማለት አዛውንቱ ካህን ፈጽመዋቸዋል የተባሉትን ስህተቶችና በሌሎችም ምእመናን የሚሰሙባቸውን ሮሮዎች ሰላም ተዋሕዶ ከምክር ጋር እንደሚከተለው አቅርባዋለች ፡፡

1.መንፈሳዊ አገልግሎት ፈልገው ወደርሶ የሚመጡትን ምእመናን ችግሮቻቸውን በመስተዋል ያድምጡ፡፡እንደ ክህነቶ ከቀረበልዎ ነጥብ በመነሣት ለችግሩ መፍትሄ የሚሆነውን አቅሞ የፈቀደሎትን የእግዚአብሔር ቃል ይናገሩ፡፡ ነገር አያርዝሙ፡፡ ርእሱን እየተዉ ሌላ ነገር ውስጥም አይግቡ፡፡የማንንም ስም እያነሱ ለገባው ለወጣው ሁሉ አይሙ፡፡ ‹ሞቴን ከቦርዱ ውድቀት በፊት ያድርገው› ዓይነት ንግግርንም በምዕመናን ፊት አይናገሩ፡፡በሚናገሩት ነገር ሁሉ ይገመታሉና አንደበትዎ የታረመ ይሁን፡፡

2.ካህን ያለኝን እግዚአብሔር ይባርክልኛል ብሎ በረከትን ተሥፋ አድርጎ የሚኖር ነው፡፡ እርሶ ግን የሚያገኙት ከፍተኛ ደሞዝ ሆኖ ሳለ መንግስት ከሚያገኙት ላይ የሥራ ታክስ እንዳይቆርጥ ሰስተው ፤ የቦርድ አባለቱን በማስጨነቅ ደሞዝዎ ለሁለት ቦታ ተከፍሎ አንደኛውን ቼክ በስሞ ሌለኛው ቼክ ደሞ በልጆ ስም ተሠረቶ እንዲከፈሎት በማድረግ ከካህን የማይጠበቅ የማጭበርበር ሥራ እየሠሩ ነው፡፡ይህ ደግሞ እርሶንም የአስተዳደር ቦርዱንም በሕግ ከማስጠየቁም በላይ ክህነቱንና ቤተክርስቲያኑዋን የሚያሰድብ ጸያፍ ተግባር ስለሆነ ያርሙት፡፡
3.ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ስህተት አልበቃ ብሎት ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ መንግስት ለችግረች የሚሠጠው ነጻ የምግብ ካርድ(Food Stump) እንዲፈቀድልኝ ቦርዱ ችግረኛ ነው ብሎ ይጻፍልኝ በማለት እርሶ የጠየቁትን አግባብ ያልሆነ ጥያቄ ቀደም ሲል ከነበሩትና በሃቅ ሲያገለግሉ በቆዩት አንዳንድ የቦርድ አባላት ጥያቄዎ ውሸትን ያዘለና የቤተ ክርስቲያኑዋን ክብር የሚነካ መሆኑ ቢገለጥሎትም እንደምቀኝነት በመቁጠር ቂም ይዘው እስካሁን ሥማቸውን በክፉ በማንሳት እያጠፉ ስለሆነ ይህንንም ስህተቶን ያርሙት፡፡

4.ከእርሶና ከካህኑ ልጆ በስተቀር በዚህች ቤተ ክርስቲያን ሌላ ካህን እንዳይኖር የሚያደርጉት የሥም ማጥፋት ዘመቻና የተንኮል ሤራ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ እጅግ እጅግ ክፉ ጠባዮ ነውና እባክዎን ያርሙት፡፡ ለዚህም ውሃ ቀጠነ እያሉ በየጊዜው ለቦርዱ ዘወትር እንደ እጅ መንሻ የሚያቀርቡት ሰብቅና ወሬ ጥሩ ምስክር ነው ፡፡እርሶ የሚያገለግሉት ታቦት እንደርሶ ሁሉ ሌሎቹን ካህናት እንደሚረዳና ከክፉ ነገር ሁሉ እንደሚጠብቃቸው አይዘንጉ፡፡ ለቦርድ የሚያቀርቡትን ወሬና ሰብቅ በግልባጭ ለታቦቱ ማቅረቦንም ይተው ፡፡ የታቦቱ ፍርዱ እንደ ቦርድ ወደ አንድ ወገን ያጋደለ ሳይሆን ሁሉንም በእኩል አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ መሆኑንም ይረዱ፡፡ ለታቦት የሚቀርበውንም ለይተው ይወቁ ፡፡ እርሶ ግን ጸሎትንና ሰብቅን የለዩ አይመስልምና በዚህ የሽማግልና እድሜዎ ከዚህ ዐይነቱ ክፉና ሰይጣናዊ ድርጊት ይራቁ፡፡

5.አቋምን በተመለከተ ዛሬ የሚያሳዩትን ጀግንነት ነገ አይደግሙትም ፡፡ ዛሬ የተናገሩትንና ያመኑበትን ነገር ነገ ሽምጥጥ አድርገው ይክዱታል፡፡ ይህ ነው የሚባል አቋም የሎትምና እባክዎ እንደ ክህነትዎ አቋምዎ የአማናዊቷ ቤተክርስቲያን አቋም ይሁን፡፡

6. በቦርድ በመመካትና በአምባ ገነንነትዎ በሚጭሩት ጠብ ምክንያት በካህናት መካከል ሰላማዊ አገልግሎት እንዳይኖር እየተፈታነ ስለሆነ አባክዎን ይህንን ወታደራዊ ጠባዮን ወደ ትህትናና ተመካክሮ ወደ መሥራት መልካም ጠባይ ቀይረው አብረው ለመሥራት ይሞክሩ፡፡የአሥራ ምናምን አመቱን አለመግባባት ዛሬ እያስታወሱ አገልጋዮችን መበቀሉንም ያቁሙ፡፡ ያለምንም ምክንያትና ማስረጃ ቅዳሴ እንዳይቀድሱ ያገዱዋቸው በዚህ ደብር ለብዙ አመታት በማህሌቱ በመራዳት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ክህነት ተቀብለው ያገለግሉ የነበሩት ካህን ጥሩ ምሳሌ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ቦርዱ ሊያነጋገሮት ቢሞክርም ‹ እናንተ ደግሞ ምንድናችሁ በካህናት ጉዳይ ምን አገባችሁ በማለት › ከእግዚአብሔር አብልጠው የሚመኩበትንና እንደ ጣዖት የሚያመልኩትን ቦርድ ተሳድበውና አዋርደው ወጥተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የነበሩትን የቦርድ አባላት በሙሉ አሳዝነዋል፡፡ ሰላም ተዋሕዶ ይህን የምታነሣው ለቦርዱ ጥብቅና ለመቆም ሳይሆን - እርሶ ሌላውን ለመክሰስና በእርሱ ላይ ለማስፈረድ ሲፈልጉ ቦርድን የበላይ ዳኛ አድርገው ወደ እርሱ ለሰብቅ መሮጦን፤ሌላው እርሶ የሚበድሉት ካህን ደግሞ አቤት ለማለት ወደ ቦርዱ ሲሄድ ደግሞ ቦርዱ እንደመያገባውና ፈላጭ ቆራጩ እርሶ እንደሆኑ መፎከርዎትን ሰምታ ስለታዘበች ነው፡፡

ፈሪ እንደሆኑና ያንያን ያህል ድፍረት እንደሌሎት ይታወቃል፡፡ ለዚህም በቦርድ ላይ የሠነዘሩት የስድብ ቡጢ አስፈርቶትና አሳስቦት ከቅዳሴ ያገዱዋቸው ካህን እንዲመጡና ቦርዱ ዳኛ ሆኖ እንዲያስማማችሁ ‹ምን አገባህ› ያሉትን ቦርድ እንደገና ሲማጸኑ መሰንበትዎ ተሰምቶአል ፡፡ ስለዚህ እባክዎትን የሚሠሩትን ሥራ ሁሉ በማስተዋል ያድርጉ፡፡ የሰላም እንጂ የነገር ሰው አይሁኑ፡፡ የሽማግሌ ተግባር ማስማማት እንጂ ማጣላት ፡ ይቅር ማለት እንጂ ቂም ይዞ መበቀል አይደለምና፡፡


7.ሠሞኑን በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ከአንዱ ካህን ጋር በቤተ መቅደስ ውስጥ የነበረውን አለመግባባት ‹ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ › ጉዳዩን ይቅር በመባባልና በእርቅ እንደጨረሳቸሁት ተሰምቶ ነበር፡፡.እርሶ ግን የተጠናወቶት የወሬና የጠብ አጫሪነት ጾር በሰላም አላስቀምጥ ስላሎት ነገረ ሠሪዎችንና የእርሶን ቢጤ ወረኞች ሰብስበው አልተሳካሎትም እንጂ ጉዳዩ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄድ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡በዚህ በኩል ብዙ ማለት ቢቻልም ‹ውሾን ያነሣ ውሾ ይሁን› የሚለው የአባቶች ወግ እዚሁ ላይ እንድናቆም ያስገድደናል፡፡

8. በአንድ በቅርቡ በተደረገ የካህናትና የቦርድ ስብሰባ ላይ ‹አለቃ ካላደረጋችሁኝና ካህናቱን እየቀጣሁ የሥልጣን ደረጃዬን ለእነሱ ካላሣየሁ ከዛሬ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኑን ቁልፍ ብትረከቡኝ ይቀለኛል› በማለት ያደረጉት ንግግር የስብሰባውን እድምተኞች ሁሉ አስደንቋል ፡፡ይህም በእድሜዎ መጨረሻ ዘመን እንደ ጾር የተጠናወትዎትን የሥልጣን ጥማት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ ያሳየና እርሶንም ትዝብትና ውርደት ውስጥ የጨመረ ነው፡፡ እባክዎ ሥልጣንን ካህናትን ለመጉዳትና ቂም በቀልን ለመወጫ አይናፍቁት፡፡ ‹በደምባራ ፈረስ ቃጭል ተጨምሮ› እንዲሉ በዚህ ከሰው ጋር በማይገጥም አውሬ ጠባዮ ላይ የእልቅና ሥልጣን ቢጨመርበት አጠቃቀሙን ስለማይችሉበት ለእርሶ እይሆንምና ይህንን ከአእምሮዎ ያወጣሎት ዘንድ አብዝተው ይጸልዩ ይህ በራሱ ደዌ ነውና፡፡


9.እርሶ የሚያገለግሉት በደሞዝ ተቀጥረው ነው፡፡ የንስሐ ልጆቾን ጉርሻ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው አድርገው አይቁጠሩ ፡፡ይህን የሚያደርጉትን ሲመርቁና ሲያሞካሹ፤ ያማይሠጡትና ወይም በአቅም እጦት አሣንሰው የቸሮትን ሲዋርዱና ሲንቁ በግልጽ ይሰማሉ፡፡ እንደውም አሥር አማራ ንስሐ ልጅ ከመያዝ አንድ ትገሬ ልጅ መያዝ ይሻላል እያሉ ከአንድ ካህን የማይጠበቀውን ጸያፍ ቃል በመናገር ክህነቱን እያሰደቡ ነውና እባክዎን ከዚህ አይነቱ ክፉ አመልዎና አሣፋሪ ንግግሮ ይታረሙ፡፡ አለበለዚያ ግን በለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለ እዳው አይሸከመውም› የሚለው ተረት በእርሶ ላይ ይተረታልና እባክዎን ክህነቱንና እግዚአብሔር የሰጦትን የእርግና ዘመን ትርጉም አልባ አያድርጉት ፡፡

3 comments:

  1. ታዲያ አለቆች/ ሒሳብ ቤት/ ሒሳብ ሹም/ ፈንጂ ላይ ቆመው ነው፧፧/? ....ወዸ ፍርዽ ቤት ምልልስ/?

    ነገ ጠዋት ግን፤
    የፌደራል ና የስቴት አቶርኒስ፤
    የ irs ና የCounty ሰዎች ወደ ቤ/ክርስቲያናቸን ብቅ ቢሉና
    አባትና ልጅን ሌሎቸንም 1᎐2᎑3᎒4᎓5᎔_፟]ከአስተዳደርና ከጽ/ቤት ቢለቅሙ አይደንቀኝም!

    ReplyDelete
  2. ይህ ሁሉ መባላትለምንድን ይሆን?

    ReplyDelete
  3. For Money. Please let us pray for our chrch.

    ReplyDelete

አስተያየት