Thursday, November 12, 2009

ዲሞክራሲያዊ የተባለው የአስተዳደር ቦርድ አባላቱ ምርጫ ፉርሽ ሆነ !

ዘመናቸውን በጨረሱ ሦስት የአስተዳደር አባላት ምትክ ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ በመረጣቸው የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት በኩል ዲስኩር ሲያስነፋ የሰነበተው የአስተዳደር ቦርድ ምርጫውን እንዳያካሂድ ዛሬ NOV 11 2009 የዋለው ችሎት አገደ፡፡


የዛሬው ፍርድ ቤት ችሎት ምርጫው እንዳይካሄድ ያገደው ቦርዱ ሁሉንም የቤተክርስቲያን አባለት የማይወክል ቡድናዊና ወገናዊ አሠራር በመያዙና የማስመርጠው ሕዝብ ባያጸድቀውም እኔ ባወጣሁትና ሥራ ላይ እዲውል ባደረኩት አዲስ ሕግ መሠረት ነው ብሎ በአምባገነንነት በመነሣቱና የሌላውን መብት በመግፈፉ ነው፡፡

ከሳሾቹን ጨምሮ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው በሚል ሰንካለ ሰበብ ብዙ አባላትን ከኮሚቴ አባልነትና ከቤተ ክርስቲያኑ አባልነት ሠርዞ የከሰሱን የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ሳይሆኑ ቤተ ክርስቲያኑን ለአባ ጳውሎስ ሊሠጡ የመጡ ዘራፊዎች ናቸው እያለ ቦርዱ ሕዝቡንና ፍርድ ቤቱን ሲያወናብድባና ሲያጭበረብር መቆየቱ ይታወሳል፡፡


ሁሉቱን መምህራን ካህናትን ጨምሮ ቁጥራቸው ወደ 80 የሚደርሱትን የቤተክርስቲያኒቱን አባላት የቦርዱ ተቃዋሚዎችና የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች ናቸው በሚል ሰበብ ከቤተክርስቲያኑ በፖሊስ ለማስወጣትና ለማባረር ወስኖ የነበረው ቦርድ ይህ እኩይ ተግባሩ የታገደው በሕግ በኩል እነደሆነም ይታወቃል፡፡
አሁንም ቢሆን ቦርዱ እልኸኛነቱን፤ወገንተኝነቱንና አምባገነንነቱን ትቶ ቤተክርስቲያኒቱ የሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን የጋራ ቤት መሆኑዋን አምኖ እስካልተቀበለ ድረስ ወደፊት ከዚህ የበለጠ ችግር ሊገጥመው እንደሚችል ከወዲሁ ሊያውቀው ይገባል፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት