Tuesday, June 29, 2010

ለፈገግታ

‹የብሎጋችሁ ተከታታይና አንባቢ ነኝ ፡፡ አምዳችሁ አንዳንዴም ፈገግ የሚያሰኝ ቁም ነገር አዘል ቀልድ ሊኖረው ይገባል ብዬ ስላሰብኩ ይህንን በአስተያየት መስጫ ሳጥናችሁ በኩል ልኬላችኋለሁና እንደምታደርጉ አድርጓት ፡፡ › ያሉን ደንበኛችንን ከልብ እያመሰገን እኛም በፈገግታ ቀልዱን ለአንባቢያን ከጓዳው ሳጥን አውጥተን ወደ ብሎጉ ሳሎን አምጥተነዋልና እነሆ፡፡

Sunday, June 27, 2010

የጁን 26 ሕዝባዊ ስብሰባ በመልካም ሁኔታ ተጠናቀቀ !
በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርቲያን አስተዳደር ችግር ምክንያት የተናጋውን የቤተክርስቲያኒቱን ሰላም በውይይት ማስተካከል ባለመቻሉ ጉዳዩ እጅግ ባሳሰባቸው በርካታ ምእመናን በሜይ 8ቱ ሕዝባዊ ስብሰባ ተወክሎ ጥረቶችን ሲያደርግ የሰነበተው የመፍትሔ ፈላጊ ኮሚቴ ቅዳሜ ጁን 26 ቀን 2010 በተጠራው ሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ስላከናወናቸው ተግባራት ሪፖርቱን አቀረበ፡፡

Saturday, June 19, 2010

የዓርብ ጉባዔ በአዲስ መልክ ተጀመረ፡፡

ቀደም ሲል በሃይማኖት አባቶች በመልአከ ሣህል አወቀ ተሰማና በቀሲስ መስፍን ደምሴ ይሰይጥ የነበረው የዓርብ ጉባዔ ካለፈው ዓርብ June 18 2010 ዓ.ም ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል ፡፡ይህ በደብሩ በተከሠተው ችግር ምክንያት የተበተኑትንና አዝነው በየቤታቸው የተቀመጡትን ምእመናን ሁሉ በማሰባሰብና አንድ ቤተ ሰብእ ለማድረግ የተጀመረው ጉባዔ በእለቱ በርካታ ምእመናን የተገኙበት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡ 

Friday, June 11, 2010

 የስብሰባ ጥሪ

በስመ አብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በአስተዳደር ብቃት አለመኖር ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ ቀደም ሲል በበጎ ፈቃደኝነት በተነሳሱ ሽማግሌዎችና የሰላም ልዑካን አማካኝነት ብዙ ጥረት እንደ ተደረገ ይታወቃል፡፡

Tuesday, June 8, 2010

የአስተዳደር ቦርዱ የአባላትን መብት ከመርገጥ አልፎ ጨፈለቀው !

እዚህ ይጫኑበአስተዳደር ቦርድ ችሎታ ማነስ ምክንያት እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጥፋት በወቅቱ ለማስቆምና የሚበጀውን ሰላም ለማምጣት ሲሉ ግለሰቦች ፤ሽማግሌዎችና የሰላም ልዑካን ሁሉ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ድካሙ በአስተዳደር ቦርዱ እምተኝነት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጥረቱን በመቀጠልና ተስፋ ባለመቁረጥ የቤተክርስቲያኑ የወደፊት ሁኔታና ዕጣ እጅግ አድርጎ ያሳሰባቸው ቁጥራቸው ከ35 በላይ የሚሆኑ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ለመሻትና ሌሎች ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉትን አባላት ሁሉ ጨምረው ለመወያየትና በጋራ መፍትሔ ለመፈለግ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጥያቄ በጽሑፍ ቢያቀርቡም የአስተዳደር ቦርዱ በተለመደው የእንቢተኝነት ባሕርዪው አዳራሹን መጠቀም እንደማይችሉ በመግለጽ ከልክሏል፡፡ 

Monday, June 7, 2010

ሠበር ዜና !

   
አዲስ አበባ

 የዳላሰ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ጸሐፊና የውብ እንጀራ ባለቤት የሆኑት አቶ አበበ ጤፉ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያደረሱት የከፋ የአስተዳደር በደል 90% በሚሆኑ አማንያን ዘንድ እጅግ እንዲጠሉ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ለአካካቢው ነዋሪ በየመደብሩ የሚያስቀምጡት የውብ እንጀራ ገዢ አጥቶ በመበላሸት እየተጣለ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ አቶ አበበና አጋሮቻቸው የቤተክርስቲያኒቱን ካህን ያለአግባብ ከሥራ ያሰናበቱትና ፖሊስ በመቅጥር ሕዝቡን ያስደበደቡት ገና ወደ ቦርድ በገቡ በሦስት ወራቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ 

Tuesday, June 1, 2010

ማኅበረ ቅዱሳን ጉባዔውን በመልካም ሁኔታ ጀምሮ አጠናቀቀ !

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 12ኛ መደበኛ ጉባዔ በዳላስ ከተማ ተካሄደ ፡፡
ከ May 28 - 30 ድረስ በቆየው በዚሁ ጉባዔ የዓመቱ የማኅበሩ ሥራዎች ግምገማ ሪፖረት የቀረበ ሲሆን የቀጣዩን ዓመት የሥራ ዕቅድና በጀትንም አጽድቋል፡፡http://www.timeanddate.com/worldclock/fullscreen.html?n=7
;

አስካሁን ከተደረጉት የማኅበሩ ዓመታዊ ጉድባዔያት በዐይነቱና በይዘቱ ከፍተኛ ነው በተባለው በዚሁ ጉባዔ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤዎስታጤዎስ የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች በርከት ያሉ ካህናትና ከመቶ ሃያ በላይ የሚሆኑ የማኅበሩ አባላት በተወካይነት ተካፋይ ሆነዋል ተብሏል፡፡
ይህንኑ የሰሜን አሜሪካ 12ኛውን ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ May 31 2010 በክራውን ፕላዛ ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀው ትምህርታዊ ጉባዔ ቁጥሩ ከ 200 በላይ የሚሆን ህዝብ የተገኛ ሲሆን ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረትና ማኅበሩ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ተሳትፎ ከማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በነበሩና ማኅበሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያገለገሉ ባሉ አባቶችና ወንድሞች ሰፊ ገለጻና ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ትምህርታዊ ጉባዔ መልአከ ሳሌም አባ ገብረ ኪዳን ፤ መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅንና ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ በተጋባዥ መምህርነት ተሳትፈዋል፡፡
በዚሁ ጉባኤ ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያም ሆነ በውጭው አለም ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከተውንና እያበረከተ ያለው የሙያ፤የገንዘብ፤የጉልበትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በእውነተኛዪቱ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ እንዲወደድና እንዲደገፍ ያደረገው ቢሆንም የቤተክርስቲያናችን መሠረታዊ ጠላቶች የሆኑ መናፍቃንና አስመሳይ ፖለቲከኞች ግን የስም ማጥፋት ሥራዎችን እንደተያያዙትም ተገልጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሕዝቡም ለመናፍቃንና ለእነዚህ አስመሳይ ፖለቲከኞች ፕሮፓጋንዳና የሐሰት ወሬ ጆሮውን እንደማይሠጥና ዳግመኛ እንደማይወናበድ ውስጣዊ ስሜቱን በቁጭትና በቃላት ገልጧል፡፡

በመጨረሻም ሕዝቡ ስለቤተክርስቲያን አጠቃላይ ገጽታዎች ግንዛቤንና እውቀትን እንዲያገኝ እንዲህ ዓይነት ጉባዔያት በተወሰኑ ወራት ሊዘጋጁ እንደሚገባ በማሳሰብ የጉባዔው ፍጻሜ ሆኗል፡፡