Saturday, September 25, 2010

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሣችሁ ! !
ጌታችን እና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድህነተ ዓለምን ከፈጸመ በኋላ መስቀሉ ሕሙማነ ስጋን በተአምራቱ የሚፈውስ፣ የዳሰሱትን ሁሉ የሚያድን ሆኗል። በዚህ ተዓምራት የተሳቡ አንድ አንድ አይሁዶችም ክርስቲያኖች ይሆኑ ነበር። ይህ ያስቆጣቸው አይሁዶች ደግሞ መሬት ቆፍረው ቆሻሻ ደፍተው እና ተራራ ሰርተው መስቀሉን ቀበሩት። በዚህ ሁኔታ ለሶስት መቶ አመታት መስቀለ ክርስቶስ ተዳፍኖ ቆየ።

በሮም ላይ ነግሰው ከነበሩት ደጋግ ነገስታት ቆስጠንጢኖስ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነገሰ። ንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናቱ እሌኒ በልዩ ክርስቲያናዊ ህይወት ኮትኩታ ያሳደገችው ክርስቲያን ንጉስ በመሆኑ በዘመነ መንግስቱ የክርስቲያኖችን ነጻነት ያወጀ ነበር። እናቱ ቅድስት እሌኒ በአረጋዊ ኪራኮስ ምክር ደመራ አስደምራ፣ እጣን አስጢሳ ሊቀ ቅዱስ ያሬድ በድጓው “ዘእጣን አንጾረ ሰገደ ጢስ” እንዲል፤ የእጣኑ ጢስ ወደላይ ወጥቶ ወደታች በመመለስ መስቀሉ ያለበትን ስፍራ አመለከታት። ለዘመናት ተቀብሮ የኖረውን መስቀል አስቆፍራ አወጣችው።

ለድህነተ አለም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋውን የቆረሰበት ደሙን ያፈሰሰበት እጸ መስቀል በአረማዊያን ዘመን ቢቀበርም ክርስቲያኖች ነጻነት ባገኙበት የሰላም ዘመን ወጣ። ሲወጣም እወር በማብራት፣ አንካሳ በማርታት፣ ጎባጣ በማቅናት፣ ለምጽ በማንጻት፣ ሙት በማስነሳት ተዓምራት አድርጓል።

ሰለ ክብረ መስቀል ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ቅዱሳት መጻህፍት እና የልዩ ልዩ ጉባኤያተ ቀኖናት ያወሳሉ። ነገረ መስቀል የማናቸውም አገልግሎት መግቢያ በር እንደመሆኑ መጠን ካህናት በእጀ መስቀላቸው፣ ምእመናን በትምህርተ መስቀል ማማተብ ከተግባሮቻችን ሁሉ ቀዳሚ ነው።የመስቀሉ በረከት በሁላችንም ይደር አሜን !

Tuesday, September 21, 2010

የአህዮች እናት እንደምን አደሩ?

በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ሁለት አህዮች ያሏቸው አንድ አሮጊት ሴት ነበሩ፡፡በዚያው መንደር ውስጥ ደግሞ አሮጊቷ ሴት አህዮቻቸውን እየነዱ ዘወትር በሚመላለሱበት መስቀለኛ መንገድ ላይ የተከመረ ድንጋይ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ተኮልኩለው አላፊ አግዳሚውን የሚተቹና የሚተርቡ ስነ ምግባር የጎደላቸው ጥቂት ወጣቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ የመንደር ጎረምሶች እንደ ለማዳቸው አሮቷ ሴት አህዮቻቸውን በጧት እየነዱ በዚያ መንገድ ሲያልፉ አሮጊቷን ለማብሸቅ ብለው ‹ የአህዮች እናት እንደምን አደሩ ? › አሏቸው ፡፡ ሰላምታው የተረብ መሆኑ የገባቸው አሮጊቷም መለስ አድርገው ‹ እግዚአብሔር ይመስገን ልጆቼ ! እንደምን አደራችሁ ፡፡ › ብለው አጸፋቸውን መለሱ፡፡

Monday, September 13, 2010

  IF YOU WANT..... 

Friday, September 10, 2010

በአዲስ ዓመት አዲስ ፍሬ

ስማቸውንና ምንጩን ሳይጠቅሱ ይህን ትምህርታዊ ጽሑፍ በአድራሻችን የላኩልንና የዝግጅታችንን ተከታታይ ከልብ እያመሰገን ትምህርቱ ወቅታዊ ሆኖ ስላገኘነው እኛም አንባቢያን እንዲማሩበት በማለት አቅርበነዋል።

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ በእለተ ረቡዕ ቀንና ሌሊትን ብርሃንና ጨለማን የሚለዩ ለዕለታትታት ለወራትና ለዓመታት መቁጠሪያ የሚያገለግሉ በሰማይ ጠፍር ላይ ብርሃናት ይሁኑ ብሎ በማዘዝ ጸሐይን በቀን ጨረቃንና ከዋክብትን በሌሊት እንዲያበሩ ፈጥሯል። እነዚህም ፍጥረታት ከተፈጠሩበት ዕለት ጀምሮ የተፈጠሩበትን አላማ ሳያዛቡ የፈጣሪን ትእዛዝ ሳያጓድሉ ክረምትንና በጋን ሲያፈራርቁ ሰዓታትን በዕለታት እለታትን በሳምንታት ሳምንታትን በወረት ወራትንም በአመታት እያፈራረቁ ለሰው ልጅ ሕይወት ጥቅም እየሰጡ ይገኛሉ። ኦሪት ዘፍ1፥14፡19

Thursday, September 9, 2010

ለምን የሚጠቅመንን አንለምንም ?
አንድ እራሱን በጣም አድረጎ የሚወድ ሰው ሁል ጊዜ ‹ እግዚአብሔር ሆይ ስጠኝ ስጠኝ ስጠኝ ... › እያለ አዘውትሮ ይጸልይ ነበር ፡፡ የነገሩትን የማይረሣ የለመኑትንም የማይነሣ አምላክም አንድ ቀን ተገለጠለትና ‹ ጸሎትህን ሰምቼ አሁን የምትሻውን ነገር ሁሉ ላደርግልህ መጥቼአለሁና ደስ ይበልህ ! አለው፡፡ ሰውየውም ጸሎቱን ሰምቶለት እግዚአብሔር ወደ እርሱ ስለመጣ እጅግ በጣም ደስ አለው፡፡እግዚአብሔርም መልሶ ‹አንተ የለመንከኝን ነገር ሁሉ እጥፍ አድርጌ ለጓደኛህም እሰጠዋለሁና ምን እንዳደርግልህ ትፍጋለህ ? አለው፡፡ ይህን ጊዜ ሰውየው ባዘነ መንፈስ ትንሽ አሰብ አደረገና ‹ ጌታ ሆይ እንግዲያውስ አንድ አይኔን አጥፋው ፡፡ › ብሎ አረፈ ፡፡ የእርሱ አንድ ዓይን ሲጠፋ የጓደኛ ሁለት ዓይኑ ይጠፋልና፡፡

Tuesday, September 7, 2010

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ካሣ እንዲከፍል በሕግ ተጠየቀ !
በዚህ በምንኖርበት የሰሜን አሜሪካ ግዛት በወሲብና በገንዘብ ቅሌት ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንዲከፍሉ ቅጣት የተጣለባችውና ይህን መክፈል ተስኖአቸው ቤተ ክርስቲያኖቻቸው በላያቸው ላይ የተሸጡባቸው የኒውዮርክና የካሊፎረኒያ ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ለአብነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በዚህና በተመሳሳይ ችግሮች ምክንያት ለገበያ የሚቀርቡ ቤተ ክርስቲያኖችም ቁጥራቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ ክርስትናውን ግምት ውስጥ እየከተተው መምጣቱን ያመለክታል፡፡