Tuesday, September 7, 2010

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ካሣ እንዲከፍል በሕግ ተጠየቀ !
በዚህ በምንኖርበት የሰሜን አሜሪካ ግዛት በወሲብና በገንዘብ ቅሌት ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንዲከፍሉ ቅጣት የተጣለባችውና ይህን መክፈል ተስኖአቸው ቤተ ክርስቲያኖቻቸው በላያቸው ላይ የተሸጡባቸው የኒውዮርክና የካሊፎረኒያ ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ለአብነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በዚህና በተመሳሳይ ችግሮች ምክንያት ለገበያ የሚቀርቡ ቤተ ክርስቲያኖችም ቁጥራቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ ክርስትናውን ግምት ውስጥ እየከተተው መምጣቱን ያመለክታል፡፡
በሜይ 2 2010 የዳለስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቦርድ ኬጂ ናይን የሚል መጠሪያ ያለቸውንና በቦንብ ፈታሽ ውሾች እየታገዙ ወንጀለኞችን የሚያሳድዱ ፖሊሶችን በከፍተኛ ገንዘብ በመቅጠር በቅዳሴ ጸሎት ላይ የነበሩትን ሰላማዊ ምእመናንን ያለ ጥፋታቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ ማስደብደቡና በተለይም ወ/ሮ ሶፊያ ዘርይሁን የተባሉትን ወጣት ወይዘሮ ከሶስት ህጻናት ልጆቻቸው ነጥለው ሰብዐዊነት በጎደለው ሁኔታ እየጎቱና እያንገላቱ እጃቸውን ወደኋላ የፊጥኝ በሰንሰለት በማሰር የአካል ጉዳት እንዳደረሱባቸው በዚያኑ ሰሞን የፎክስ ቻናል ፎር ቴሌቪዥን ክስተቱን ለአለም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በዚህ መሠረት በአስተዳደር ቦርዱ ገንዘብ ያዥና ምክትል ሊቀመንበር ትዕዛዝ ሰጪነትና መሪነት በፖሊስ የደረሰባቸውን ድብደባና እንግልት ወደ ሕግ በማቅባቸው ከፍተኛ አደጋን በቤተክርስቲያኑ ህልውና ላይ ደቅኗል፡፡
ወይዘሮዋ በሃማኖትና በመልካም ሥነ ምግባራቸው የሚታወቁ ሲሆኑ ሕገ ወጥ በሆኑና የሃይማኖት ሰዎች ባልሆኑ ትቂት ግለሰቦች ቤተ ክርስቲያኑዋ በመደፈሩዋና ከመንፈሳዊ መንግዱዋ በመውጣቷ እንዲሁም የተሞከሩትን የሰላም መንገዶች ሁሉ የአስተዳደር ቦርዱ በኃይል አልቀበለም በማለቱና በኃይል ለመግዛት በመሞከሩ ምክንያት በመቆጨት አማራጭ በለሌው ሕግ አስከባሪ ኃይል ለመጠቀም ለመገደዳቸው የታዩት አሳዛኝ ሁኔታዎች ሁሉ ምስክሮች ናቸው፡፡
ሰው ብዙ ጊዜ ተመክሮና ክፉ መንገዱን እንዲተው ተደጋግሞ በሽማግሌ ተለምኖ እምቢ ካለ፤ እንኳን የሰውን የእግዚአብሔርንም ትእግስት የሚፈታተን መሆኑ የሚያጠራጥር አይሆንም ፡፡የእግዚአብሔር ቁጣና ቅጣት ደግሞ ሊቋቋሙት የማይችሉት ስለሆነ ከሁሉ የከበደ ይሆናል፡፡ የአስተዳደር ቦርዱ በሰው መብት ረገጣ ወንጀል ተከሶ የዚህን ክስ ውጤት ለመስማት ለዲሴምበር 6 2010 የተቀጠረ መሆኑ ቢታወቅም ይህ የወ/ሮ ሶፊያ ክስ ግን የድብደባ ወንጀል ክስ በመሆኑ ከአሜሪካ ሕግ በተለይም በሴቶች መብትና ክብር በኩል ያለውን ሕግ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጋፋ ስለሆነ የቦርድ አባለቱን ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍተኛ ችግርና ዕዳ ውስጥ የሚጥል ጉዳይ ሆኗል፡፡ይህ ጦስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ለጋርላንድ ሲቲንም ተርፏል፡፡ በዚህ መሠረት የጋርላንድ ሲቲ ፖሊስም ለፈጸመው የድብደባ ወንጀል የሦስት ሚሊዮን ዶላር ካሣ እንዲከፍል መጠየቁን ከታመኑ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡
የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ባልተጠበቀ ሁኔታ እንዲህ ዓይን አፍጥጦ ጥርስ አግጥጦ በመጣበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከአስተዳደር ቦርዱና ደጋፊዎቻቸው ከሆኑት ብሎጎች የሚወጡት ዘለፋና ስድብ የተቀላቀለባቸው ጽሑፎች ከሳሽዋን ወይዘሮ የበለጠ እልህና ቁጭት ውስጥ የሚከቱ እንጂ ሰላምን ስለማያመጣ ከዚህ ለቤተክርስቲያኒቱም ሆነ ለቦርዱ ህልውና ከማይጠቅሙ አሉባልታዎች ተቆጥበው ችግሩ የሚቀረፍበትንና ስምምነቱ የሚመጣበትን መንገድ መፈለግ ይሻላል በማለት ሰላም ተዋሕዶ በዚሁ አጋጣሚ ልባዊ ምክሯን ትለግሳለች፡፡
አለበለዚያ ግን በከሳሽዋ ጠበቃ በኩል በሕግ የተጠየቀው ገንዘብ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ከጸና ቤተ ክርስቲያኑ በባንክ ያለው ገንዘብ በሙሉ ይወሰድበታል፡፡ ያ በቂ ሆኖ ካልተገኘ ግን ጠበቃው ሕንጻውን በላያችን ላይ ለሐራጅ ሽያጭ ለማውጣት ሙሉ መብቱ በፍርድ ቤቱ የተከበረለት ይሆናል፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም ነገር ከእጅ ይወጣና ከላይ በምሳሌነት ያነሳናቸው የኒውዮርክና የካሊፎርኒያው አብያተክርስቲያናት እጣ በእኛ ላይ ይደርሳል፡፡
በሌላም በኩል የአስተዳደር ቦርዱ ጠበቃ ይህንን የመከላከያ ክስ ፋይል ለመክፈትና ለማንቀሳቀስ 45፣000 ዶላር ከቤተክርስቲያኑ አካውንት እንደጠየቀና እንደተሠጠው መረጃዎች የሚጠቁሙ ሲሆኑ የአስተዳደር ቦርድ እስካሁን ክሶቹን ለመከላከል ያወጣው አጠቃላይ ገንዘብ ወደ 170፣000 ዶላር መድረሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡


8 comments:

  1. በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

    ድሮም በአመጽ የተሰበሰበ ገንዘብ መድረሻው አይታወቅም በቀ ይበለን እስኪ

    ReplyDelete
  2. I pray for the members of the Board and their families and the Father and son priests to make their heads up and see the sky is still blue.

    I pray for the members of the Board and their families and the Father and son priests not to look down all the way deep, to the 'world life', the revenge and hate.

    I pray for the members of the Board, their friends and the Father and son priests to have a spiritual gut to see on their eye and remember to what happened in and around St. Michael church ... past and present....
    the tears… of kids,
    the tears and the sorrow of hundreds ….. of mothers and sisters, all Mimens ....

    .. awe keep pray !

    ReplyDelete
  3. Dallaseotc.blogspot.com ገጽን የምትከታተሉና በሚወጡት ስድቦች የምታዝኑ ምእመናን፦ እኔ ሲመስለኝ የዚህ ብሎግ ባለቤት ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ የሌለው፣ የእግዚአብሔርን ቃል የናቀ፣ ፀረ ሰላም፣ የካህን ውግዘት የማይፈራ፣ ቤተክርስቲያኗን እያረጋጉ ያሉትን ካህን የናቀ ፀረ ከርስትና ወይም ሌላ አላማ ያለው አለያም ህይወቱ በስድብና ..... የተጥለቀለቀ አለማዊ፣ ፖለቲከኛ ብቻ የሆነ ሰው ሊሆን ስለሚችል ናቅ አድርጋችሁ ብታልፉት በእርግጥ በነሱ ጎራ ያሉትን ሰዎችን ማሳያ ናሙና መሆኑ እርግጥ ነው ይሁንና ሀሰት ኖረም አልኖረ እውነት መፍካቷ ብርሀን ጨለማን መግለጡ አይቀሬ ነው:: ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳን እንጂ የተሳዳቢያን ተከራካሪ ሊኖራት አይችልም፣ በቅዱሳን ፀሎት እንጂ በሀጥያተኞች እርግማን አትጠበቅም አትገለገልም ምን አልባት ወንድም መካሪ ካላቸው ከፅሁፎቻቸው ውስጥ ስድቦቹን ለቅመው እያወጡ እንዲለጥፉ ብትመክሯቸው ከዚህ በተረፈ ተሰደብን ብላችሁ የምታስቡ ሀይማኖተኞች አይድነቃችሁ just ignore
    it ይህንን ጽሁፍ በገጻቸው ላይ ካወጡት ብዬ ለመለጠፍ ሞክሬ ስላላወጡልኝ ነው እዚህ ጎራ ያልኩት። እግዜር ይስጥልኝ።

    ReplyDelete
  4. ባለፈው እሁድ ቅዳሴ ላይ ቄስ መስፍንን በማየቴ በጣም በጣም ደስ አለኝ፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ ሰው፡፡ እንደገናም በዚህ በሎግ ላይ ምስላቸውን በማየቴ ሰላምና ጥሩ ቅዳሴ ያስቀደስንበትን ጊዜ አስታወሰኝ ፡፡ ምቀኝነትና ጥላቻ የተጠናወታቸውን አባትና ልጅ ቄሶችን ሳይ ደግሞ ክፉና የጥላቻ መንፈስ በአዕምሮዬ እየመጣ ተቸግሬአለሁና እባካችሁ እግዚአብሔር ይህን ክፉ መንፈስ ከእኔ እንዲያርቅልኝ ጸልዩልኝ ፡፡ እኔም ይህን ላማርቅ እየታገልኩ ነው፡፡

    ReplyDelete
  5. እኔም እንዳንተው ቄስ መስፍንን በማየቴ ደስ ብሎኛል አድንቄአቸዋለሁም እንደማይፈልጓቸውና ያለውን ጥላቻ ተቋቁመው በልጆቻቸው ስርአተ ተክሊል ላይ በመገኘታቸው ጥሩ ሰውነታቸውን አስመስክረዋል። ታዲያ ምነው አባትና ልጅ ዘወትር ከሚቀመጡበት የፊት ለፊት ወንበር ሸሽተው መጣብህ መጣብህ ተባብለው ማዶ የጎን ወንበር ላይ ተቀመጡሳ። አስተማሪው አባት ምኑም ውስጥ የሌለበትን ምዕመንን ያን ያህል ከሚጫኑ ዞር ብለው እናንተስ አይሉም ነበር። ችግሩም መፍትሄውም ያለው እዛው (ትምህርቱ ፈፅሞ ልብን የሚነካ ሁላችንም የተነካንበት የንስሀ ጥሪ ነበረ ነገር ግን አባታችን ዘወትር ተጨንቀው ሊለውጡ በሚፈልጉት ችግር የተተበተቡት ባለ ልዩ ጥቅመኞችን የነካ የደረሳቸው አይመስለኝም እንጂ) በተረፈ ወንድሜ ሰውን አትጥላ ይልቅስ ቤተክርስቲያናችንን ፈተና ውስጥ የከተተውን ክፋትና ተንኮል እንጂ። ለቤተክርስቲያን የሚጠቅሙ ስራዎችን በመስራት እውነተኛ አገልጋዮችን በስራቸው በማገዝ ከሰም ለበስ (ለቤተክርስቲያን ጥቅም ከሚመስሉ)ክፉ ስራዎችና ሰዎች በመራቅና በመሳሰሉት መበቀል ብቻ ይበቃል ከዛ በተረፈ በልብ ውስጥ ያለን ጥላቻ ከሚያባብስ ከተማችንን ከተቆጣጠረው ከዜናነት ያለፈ የዘወትር የጥላቻ ወሬ እራስን መቆጠብና በፀጋህ ለማገልገል መጣር ጥላቻን ከልብ ለማጥፋት ይጠቅማል።

    ReplyDelete
  6. I am sure the master mind of everything happening in our church is the fake doctor and his psychopath wife and they will go to prison very soon. They are protestants and underestimated the power of the Arch Angel Saint Michael. Along with the other board members (Abera Fita and Andualem), they chased away too many Christians from the church. Now is pay back time. They will reap what they sow.

    I was also glad to see Kesis Mesfin last Sunday. I always admire him being a man of God and a good shepherd. May God protect him and his family. Amen!

    ReplyDelete
  7. እንደ ፖለቲከኞች እኔ የቦርድ ደጋፊ ወይም የከሳሽ ወገን ተብሎ በሚለጣጥፈው የማላምንና በግሌ የሌለሁበትም ብሆን ግን በዚህች አንዲት ቤተ ክረስቲያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ምንጊዜም ፈፅሞ ኣልቀበልም። ታዲያ እኔም በዚህች ባሳለፍናት የሰንበት ዕለት መነኩሴ አባታችን እያስተማሩ ሳለ ትልቁ አባታችን ደግሞ የቤተክረስቲያኑን ሊቀ-መንበር (ባልሳሳት አቶ ዮሴፍ)ን ጠርተው ሲያበቁ ወደ ቤተ-መቅደስ አስገብተው በር ሲዘጉ በማየቴ አዘንኩ። ባልንሰቀሰቅም አይኔ ግን በእንባ ተሞልቶ ነበር።

    እንደ ሰማሁት በሴቶች በኩል ያለው በር በቀጥታ ወደ እቃ ቤት ማለትም ወደ መጽሀፍት፤አልባሳትና ሌሎች የቤተ-ክርስቲያኗ መገልገያ የሚያስገባ ሲሆን በወንዶች በኩል ያለው በር ግን በቀጥታ ወደ ቅድስቱ የሚያስግባ ነው። እባካቹህ ከተሳሳትኩ እንድታርሙኝ ካልተሳሳትኩም እኚህን አባት የምትቀርቡ ወንድሞች እህቶች ካላችሁ ቀርባችሁ ማነጋግሩ መልካም ነው።

    በትምህርቱ ግን ጠነከርኩ።

    ReplyDelete
  8. Hulachihum atirebum lekachu wituna sertachu bilu - wanaw betbach degimo mahibere kidusan endehona awkenewal - ersu yesiachihun yistachu.

    ReplyDelete

አስተያየት