Wednesday, May 11, 2011

አሰቸኳይ መልእክት ለኢ-ሜይል 
ተጠቃሚዎች በሙሉ !
በአልቃይዳው መሪ በኦሳማ ቢላዲን መገደል ምክንያት ለበቀል የተዘጋጁ አሸባሪዎች ከትናት ማክሰኞ እለት ጀምረው የመርዝ ቫይረሶቻቸውን በዓለም ንጹሐን ዜጎች ኮምፒውተሮች ላይ በኢሜል በመልቀቅ የተለመደ የጥፋት ተግባራቸውን አሁንም ቀጥለውበታል ፡፡በዚህ መሠረት ኦሳማ ቢላዲን በስቅላት እንዶሞተ ተዶርጎ በተሠራ የሐሰት ፎቶግራፍ ና ይህንኑ በሚገልጽ ('Osama Bin Laden Captured' or 'Osama Hanged',) በሚል ርእስ የተዘጋጀ ኮምፒውተርን የሚሰብር አዲስ ቫይረስ በአለም መለቀቁን McAFree የተባለው የማይክሮሶፍት ካምፓኒ የኮምፒውተር ቫይረስ መከላከያ ክፍል አስታውቋል፡፡