Thursday, November 12, 2009

ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለም !

የቤተ ክርስቲያንቱን ሕጋዊ ህልውና ለማስከበርና የአባላቱንም መንፈሳዊ መብት ለማስጠበቅ ስትሉ ከሕገ ወጦቹና ከአምባገነነኖቹ የቦርድ አባላት ጋር እየታገላችሁ ላላችሁት እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ፤ ሰላም ተዋሕዶ ከፍተኛ አክብሮቷን ትገልጻለች ፡፡

ገንዘባችሁን ጊዜያችሁንና ጉልበታቸውሁን ሁሉ መሥዋዕት በማድረግ እውነት ወደ አደባባይ እንድትወጣና በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ እንድትታይ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን ሁሉ እኩል መብት ኖሯቸው ቤተ ክርስቲያኒቷን በፍቅር፤በደስታና በነጻነት ማገልገል የሚችሉበትን መብት እንዲያገኙ እየደከማችሁ ያለው ድካም ሁሉ ቀላል ግምት የሚሠጠው አይደለም፡፡ ለእውነት የሚደክሙና ስለ እውነት ሲሉ መከራ የሚቀበሉ ሁሉ ከእውነተኛው አምላክ ታላቅ ዋጋን ያገኛሉና እናንተም ባለዋጋዎች ናችሁና በርቱ !
ቤተ ክርስቲያኒቱን ከምሥረታ ጀምሮ ስታገለገሉ ለነበራችሁና በሥራና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ወርሃዊ አስተዋጾአችሁን ለመክፈል ስለዘገያችሁ ከአባልነት ተሠርዛችኋል ፤ ስለዚህ እንደ አዲስ አባል የመመዝገቢያ ሃምሳ ዶላር፤የአባልነት ደግሞ 30 ዶላር እየከፈላችሁ አዲስ አባል ሁኑ፤ተብላችሁ ከገዛ ቤተ ክርስቲያናችሁ የተገለላችሁ ምዕመናን ሁሉ መብታችሁን ለማስከበርና በሃዘን ያፈሰሳችሁትን እንባ ሁሉ በደስታ የምታብሱበት ጊዜ አሁን ነውና አይዞአችሁ፡፡ ብሶታችሁንና ሃዘናችሁን የሰማ አምላክ አሁንም ፍርዱን በምድር ሊያሳያችሁ ቀርቦአልና እናንተም ከእናንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርጉ፡፡
ድምጻችሁን ለማሰማትና ምስክርነታችሁን ለመስጠት ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለምና ብሶታችሁን ያለምንም ዋጋ ለከሳሾች የሕግ አማካሪ በኢ-ሜል በመግለጽ እውነት በቤተክርስቲያናችን አደባባይ ፈጥና እንድትቆም የበኩላችሁን ግዴታ ተወጡ ፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት