Tuesday, November 3, 2009

ይህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ነው

በብዙ የተመሰቃቀለና የተበላሸ የአስተዳደር ሥራ ውስጥ ገብቶ የሚዳክረው ቦርድ ጨርሶ ቤተ ክርስቲያኑዋን ለማስተዳደር እንዳቃተው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡ ከእለት ወደ እለት ከመታረም ይልቅ ጥፋትን እንደ ሥራ የተያያዙት የቦርድ አባላቱ ከምርጫው ወሬ ዋዜማ ጀምረው በወደቀ አጥንት እርስ በእርስ እንደሚናከሱ ውሾች በቡድን ተከፋፍለው እርስ በእርሳቸው ሲባሉና በሃይለኛ የቃላት ጥይት ሲጠዛጠዙ እንደሰነበቱ ተገለጸ፡፡

ይህም የወላጅ ኮሚቴ አባላትን ደጀን አድርጎ ግልጽ በሆነ የሥልጣን ትግል ውስጥ የገባው የሂሳብ ሹሙና የገንዘብ ያዡ ቡድን ሊቀ መንበሩና ጸሐፊውን ከቦርዱ ሥልጣን አስወግዶ የራሱን ቡድን ለማጠናክር ማቀዱንና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ የድጋፍ ጥሪ መጠየቁን ሰንበት በሚባለው ብሎጉ ላይ ገለጸ ፡፡
ይሁን እንጂ ቀደም ሲል የሂሳብ ሹሙና ጸሐፊው እንዲሁም የእቃ ግዢ ክፍ‹ የነበራቸው ፍቅር በአንድ ማንኪያ እንጉረስ እስከ ማለት የደረሰ እንደነበረም ይታወሳል፡፡ ዛሬ ግን ሁሉም ነገር የተገላቢጦሽ ሆኖ ለበቀል እንደሚፈላለጉም ታውቋል ፡፡
በአንጻሩም ደግሞ የኮሚኒቲውን አንኩዋር ሰዎች ተገን አድርገው በሌላው የትግል መሥመር የተሰለፉት የቦርዱ ሊቀ መንበር ሌሎች አራት የቦርድ አባላትን በማስተባበር በአዲሱ የቦርድ አባላት ምርጫ ወቅት ስልጣናቸው እንዳይነካና ወደ ሂሳብ ሹሙ እንዳያልፍ እየተሯሯጡ እንደሆነም ለማወቅ ተች‹ል፡፡ይህንኑ ሃሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ከዋናዎቹ የኮሚኒቲ ሰዎች ጋር ሲመክሩ እንደሰነበቱም ታውቋአል፡፡ የምክሩም ውጤት እንደሚያመለክተው ዘመናቸውን ጨርሰው በሚወጡት ሶስት አባላት ምትክ ከኮሚኒቲው አባላት መካከልል አቶ በትሩ ገብረ እግዚአብሔርና አቶ አምሃ ገብረ አማኑኤል በምርጫ ውስጥ እንዲገቡ ያጨ መኖኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ይህም በአቅም እጦት ምክንያት እየተንገዳገደ ያለውንና ሊወድቅ የደረሰውን ቦርድ በትኩስ ሃይላቸው እንዲያቆሙትና ስብራቱን እንዲጠግኑ ነው ተብሎአል፡፡
በሃይል ሚዛን ከሂሳብ ሹሙ ይልቅ ሊቀመንበሩ ይሻሉኛል ብለው ሂሳብ ሹሙን ትተው ወደ ሊቀ መንበሩ ሄደው የተለጠፉት የቦርዱ ጸሐፊም እንደገና ለመመረጥ ሲሉ ወደ አንዳንድ የቦርድ አባላት ቤት በመሄድ ሂሳብ ሹሙና ገንዘብ ያዡ በምን መልኩ ከአስተዳደር ቦርድ መወገድ እንደሚችሉ እያማከሩ መሰንበታቸውም ታውቆአል፡፡
በአንደበተ ርቱዕነታቸው፤ በቀና አመለካከታቸውና በአስተዋይነታቸው የሚታወቁት አቶ በትሩ ለመዋረድና የያዙትን መልካም ስምና ክብር ለማጣት ካልሆነ በስተቀር በአመለካከትና በአስተሳሰብ ከማይመጥኑአቸው ከቀሪዎቹ የቦርድ አባላት ጋር ሆነው አስተዳደሩን ይለውጣሉ ማለት ዘበት ነው ፡፡ ይህ ከሆነ ግን በአረጀና በተቀዳደ ልብስ ላይ አዲስ ጨርቅ እንደመጣፍ ይቆጠራልና ውርደት ነው ፡፡ የአቶ በትሩ ትኩስ ጉልበት ምናልባት ሊጠቅም የሚችለው ያለችሎታና እውቀት ቤተ ክርስቲያኒቷን ያዋረዱና አሁን በአስተዳደር ውስጥ ያሉት የቦርድ አባላት በሙሉ ወርደው ተመሳሳይ አስተሳሰብና እውቀት ያላቸው አስተዋይ ሰዎች ሲመረጡ ብቻ ነው፡፡ ምንም እንÎን ይህን ዓይነቱን አስተዳደር በዚህ ቦታ ለማየት ከባድ ቢሆንም እነዚህ በሥልጣን ፍቅርና በጥቅም ምክንያት በቤተክርስቲያኑዋ ላይ እንደመዥገር ተጣብቀው ደሟን የሚመጡ ማፈሪያዎችን ግን በቅርቡ መገላገል እንደሚቻል የታመነ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት