Tuesday, November 17, 2009

ንቁ ! ስለ ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም እወቁ !

የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቦርድ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ ችግር ውስጥ መውደቅ ፤ የምርጫው በሕግ መታገድና የአስተዳደር ቦርዱ መፍረክረክና አቅም ማጣት በቤተክርስቲያኗ ላይ ከፍተኛ ችግር ለመጋረጡ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡
በተለይም ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑቱ ለገጠማት ዐቢይ ችግር ግምባር ቀደም ተጠያቂ የሚሆኑት በቦርድ ውስጥ የሚገኙትን ባሎቻቸውን ተገን አድርገው በወላጅ ኮሚቴ ስም የተሰባሰቡት ሥራ ፈት ሴቶችና ገና የጉርምስና ጊዜያቸውን ያልጨረሱ ማፈሪያ ወንዶች ናቸው፡፡ ይህ እራሱን ወላጅ ኮሚቴ ብሎ የሰየመና ትምህርት ቤቱን ወደ ቦርድ ሥልጣን መሸጋገሪያ ድልድይ አድርጎ ለመጠቀም በአድማ እንቅስቃሴ የጀመረው የአመጸኞች ቡድን ዓላማው አልተቻለም እንጂ ቢቻል የአስተዳደሩን ሥልጣን ሙሉ ለሙሉ ተረክቦ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ለመኖርና የቤተ ክርስቲያኒቱን ገንዝብ ባለተራ ሆኖ ለመብላትና ለመዝረፍ ነው፡፡

በምርጫው ዙሪያ የነበረው ዓላማ ቢሳካ ኖሮ ዶክተሩን ሊቀመንበር ፤ ወ/ሮ ሶሎሜን ጸሐፊ ፤ አቶ ስጦታውንና አቶ ሙሉዓለም የተባሉትን ጋጠ ወጦች ደግሞ በቦርድ አባልነት አስመርጦ ‹ከእጅ አይሻል ዶማ› ዓይነት መሳቂያ ቦርድ ለመመሥረት ነበር፡፡ ‹ደህና ሰው አይብቀልብህ› ተብሎ የተረገመ ይመስል የደብሩ አስተዳደር በማይረቡ ሰዎች እንዲያዝ መታሰቡም በራሱ የሚያሳዝን ነው፡፡ ከእነዚህ ልበ ትልቆች መካከል አራቱ ማለትም የለበኩ ዶክተር ፤ገንዘብ ያዡ ፤ ወ/ሮ ሶሎሜና አቶ ሥጦታው የፕሮቴስታንትን እሳት ሞቀው ገና ሳይቀዘቅዙ የመጡ ናቸው፡፡ የዚያንም የዚህንም ሃይማኖት ዶክትሪን ጠንቅቀው የማያውቁ ቢሆንም መንፈሳቸው ግን ከኦርቶዶክስ ወደ ፕሮቴስታንቱ ሃይማኖት ያዘነበለ ለመሆኑ በአነጋገራቸውና በሚሰጧቸው አስተያየቶች ተረጋግጧል፡፡ እነሱም አሁን እዚህ የተቀመተጡት የያዘ ይዟቸው ነው፡፡ይኸውም ሲያዩት እንደበሰለ ቡርቱካን የሚያጓጓው የቤተ ክርስቲያኑዋ ገንዘብ ነው፡፡

አቶ ሙሉ ዓለም ደግሞ ገና እርጥብ እንጨት ናቸው፡፡ በሚስታቸው አስፈራሪነት ሳይወዱ በግድ የብዙ ጊዜ ማኅበርተኛቸውና ወዳጃቸው የሆኑትን ሊቀመንበሩን ከድተው ወደ አመጸኞቹ ጎራ የተቀላቀሉት ምክትል ሊቀ መንበሩም ቢሆኑ ሌለኛው እርጥብ እንጨት ናቸው፡፡ እርጥብ እንጨት አይነድም፤ እሳትም አያወጣም፡፡ እሳት አደገኛነቱ ያለአግባብ ሲለኮስና የማይሆን ቦታ ሲነድ ነው እንጂ እሳት ለብዙ ነገር ስለሚጠቅም ተፈላጊ ነው፡፡ እንጨትም በእሳት ነዶ ለማብሰል የግድ መድረቅ አለበት፡፡ ወደ ፋብሪካ የሚገባ እንጨት ተልጎ ወንበር ፤ ጠረቤዛ ወዘተ… ሆኖ ለመውጣት የግድ መድረቅ አለበት፡፡ እነዚህም ሰዎች በአመራር ደረጃ ተቀምጦ የበሰለ ነገር ለመሥራትና ቤተ ክርስቲያኗን ለማገልገል ገና ያልበሰሉ ጥሬዎች በመሆናቸው በእርጥብ እንጨት ተመስለዋል፡፡ ከዚያ የተሸሉ አይደሉምና፡፡ ይህን የምንለው የሰውን ሰብአዊ ክብር ለመንካት ሳይሆን አላዋቂ ሳሚ የሰውን ፊት በንፍጥ ለቅልቆ እንደሚያበላሽ ለመግለጥ ነው፡፡

‹ የሚበላ እንጀራ ገና ከምጣዱ ያስታውቃል › እንዲሉ የእንዚህን ሰዎች ሰብአዊ ባሕርዪና ብስለት የሌለው አስተሳሰባቸውን በማየት ብቻ በአዲስ መልክ ሊዋቀር የነበረው አስተዳደር ምን ያህል አሳፋሪ ሊሆን ይችል እንደነበር ከወዲሁ መገመት አያዳግትም፡፡ ይህ ደግሞ ቤተክርስቲያኗን ከድጥ ወደ ማጥ ሊወስድ የነበረ በመሆኑ ምርጫው ለጊዜው መታገዱ የእነዚህን ሰዎች ሤራ ያከሸፈ ነውና የቤተ ክርስቲያናችን እውነተኛ ልጆች የሆናችሁ ምእመናን ሁሉ እግዚአብሔርን ልታመሰግኑት ይገባል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉዳይ በንቃትና በትጋት ሆናችሁ ከዚህ አደጋኛና ወሮ በላ ቡድን እንድትጠብቁ ሰላም ተዋሕዶ በጥብቅ ታሳስባለች፡፡

በብዙ የተጭበረበረ መንገድ ቦርድን ተገን አድርገው ከካህን የማይጠበቀውን ጸያፍ ሥራ ሢሰሩ አመታትን ያስቆጠሩት አዛውንቱ ቄስም ኃይል ያጣውንና የተከፋፈለውን ቦርድ ሁኔታ አጢነው አቅጣጫቸውን በመቀየር ፕሮቴስታንት መንፈስ የተጠናወታቸውን የወላጅ ኮሚቴ አመጸኛ ቡድንን ከነልጃቸው ተቀላቅለዋል፡፡ ይህም ሊቀመንበሩንና ቀሪዎቹን የቦርድ አባላት በጣም አሳዝኗል ፡፡ ይህ አዲስ አይደለም ፤100% እውነት የሆነውን የእኚህን ሰው ጠባይ ሰላም ተወሕዶ ቀደሰም ሲል መዘገቧ ይታወሳል፡፡እኚህ ሰው ገንዘብና ጥቅምን ያግኙ እንጂ እስልምናን የሚከተሉ ሌሎች የቦርድ አባላት ቢፈጠሩ ደግሞ አብረው እንደሚሰልሙ አያጠራጥርም ፡፡

ሳይገባው ቤተክርስቲያኒቱን በዲቁና አገለግላለው ብሎ የተነሣውና በመሃል ሰፋሪነቱ ፤ በጆሮ ጠቢነቱና በባንዳነቱ የሚታወቀው የንስሐ ልጃቸው ኤርምያስ ታደሰም ለገንዘብ ሲል በትዳሩ ላይ እስላም ሴት አግብቶ የተቀደሰውን ቤተ መቅደስ ሲያረክስ እያዩ ዝም ማለታቸውና እንዲቀድስ መፍቀዳቸው ሌላም እንዲህ አይነት ቢዝነስ ካገኘህ ለእኔም አምጣ ያሉ አስመስሎባቸዋል፡፡

ዲያቆን ነኝ ባዩ ይህ ሰው ገንዘብን ለማግኘት ሲል በትዳሩ ላይ ከክርስትና ውጭ ከሆነች እስላም ሴት ጋር ሁለተኛ ጋብቻን በመፈጸሙ ክህነቱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም አጉድፏል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሚሰት በተባለቸው እስላም ሴት ላይ በፈጸመው ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባር ሃይማኖታችንንም አሰድቧል፡፡ ስለዚህ ሰላም ተዋሕዶ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ሕግ ካላት ተቆርቋሪነት አንጻር ጉዳዩ በፖሊስ በኩል ክትትል እንዲደረግበትና እንዲህ ዓይነቶቹ ወንበዴዎችና ማፈሪያዎች ቤተ መቅደሱን እንዳያረክሱና ምእመናንን እንዳያሰናክሉ ለማድረግ ኃላፊነቷን በአግባቡ ትወጣለች፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት