Wednesday, July 28, 2010

የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል !
ይህ የሃገራችን አባባል ብዙ ጊዜ ለሚቸኩሉና በችኮላቸው ጥፋት ለሚያደርሱ ሰዎች መረጋጋት እንዲኖረቸው ለመምከር የሚተረት ወግ ነው፡፡ ቅቤ በክብርና በፍቅር ከሚበሉ ምግቦች መካካል አንዱ ሲሆን አወጣጡና አዘገጃጀቱም በየሃገሩና በየባህሉ የተለያየ ነው፡፡እንደምናውቀው በእኛ ባህል ቅቤን ለማውጣት ወተቱ ጊዜ ወስዶ መርጋት አለበት፡፡ ለዚህ ነው አበው ሰውም ከተረጋጋና ጊዜ ወስዶ ነገሮችን እያስተዋለ ከሠራ ለጥሩ ውጤት እንደሚበቃ ለማመልከት ‹የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል› በማለት የሚተርቱት ፡፡ ከዚህ አንጻር እኛም ስለመረጋጋት ግንዛቤ ታገኙ ዘንድ የሚከተለውን ጽሑፍ በአጭሩ አቅርበነዋል፡፡


መረጋጋት መንድነው ? - መረጋጋት ሰላምን በልባችን ውስጥ ቦታ እንድንሰጠውና ቀስ በቀስም እንዲያድግ የሚያግዘን ሰላማዊ መንፈስ ነው፡፡መረጋጋት አዕምሮአችንን ማንኛውንም ሁኔታ በሰከነ መንገድ እንዲመለከት የሚያደርግና በችኮላ ከሚመጡ ተደጋጋሚ ስህተቶች እንዲጠበቅ የሚረዳ ሕሊናዊ ጥበብ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ነቢይ ሙሴ በእምነት ይመራው የነበረው ሕዝብ እግዚአብሔርን ወደ መርሳትና ወደ ባእድ አምልኮ ባዘነበለ ጊዜ ሳይቸኩል በመረጋጋት የወሰደው አቋም ሕዝቡን ጨርሶውኑ ከመጥፋት እንዲድኑ አድርጓቸዋል፡፡ ዘፀ 32 ፡ 41፡፡

የተረጋጋ ሰው ቶሎ የማይበሳጭና ሌሎችን የሚታገስ መንፈሳዊ አቅም አለው፡፡ ይህንን እንዲያገኝ የሚረዳው ደግሞ በውስጡ ያለው የተረጋጋ መንፈስ ነው፡፡ሰላማዊና ትዕግስተኛ ሰው መሆን ይቻል ዘንድ መረጋጋት የመጀመሪያው መንገድ ነው፡፡

እንግዲህ መረጋጋት የውስጥ ጠባይ በመሆኑ ከውጫዊው ጠባይ ጋር እስኪዛመድ ድረስ በመረጋጋት የሕሊና ሰላም እስኪገኝ ድረስ ከራስ ጋር ዘወትር በመታገል እራስን በጣም የተረጋጋ ሰው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

2 comments:

  1. የመልክታችሁ ማጠር አንባቢያንን አያሰለችምና ጥሩ ነው፡፡ የምታቅርቡት መልእክትም ሄዶ አዕምሮ ውስጥ የሚቀመጥ ምክር ነውና ለእኔ በጣም ተስማምቶኛልና በዚሁ ቀጥሉበት፡፡በጣም ችኩል ወንድም አለኝና ይህቺን መልዕክት ለእርሱ ለማድረስ ቸኩያለው ፡፡መረጋጋትንም እንዲያገኝ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡ ዘማርያም ነኝ ከፎርት ዎርዝ፡፡

    ReplyDelete
  2. The article that you wrote about stability is very interesting . Keep on providing us these kinds of inspiring and touching articles. Do not go back to those dirty church politics of st. Michael church . Thanks

    ReplyDelete

አስተያየት