Friday, December 3, 2010

አሜሪካኖች ባል ለሚስቱ ምን ያድርግ ይላሉ?
ከሰላዩ ብእር የቀጠለ
ክፍል አራት
ለባለቤቴ እጅግ ጥሩ ባል መሆን እንዳለብኝ ገና ድሮ በወጣትነት ዘመኔ ሳላገባ በፊት አስብ ነበር ፡፡ከዚሁ ጋር በተገናኘ ሀሳብ ብዙ መጻሕፍትን እንብቤአለሁ፡፡ ካነበብኩዋቸው መጻሕፍት ብዙ ዕውቀትና ምክርንም አግንቻለሁ፡፡ ለዚህ ነው ባለቤቴን በተቻለኝ ሁሉ ለማስደሰትና ለመንከባከብ ጥረት ያደረኩት ፡፡ ከባለቤቴ ጋር የነበረንን የሆቴል ቤት ቆይታ ትርኢት ከማጠቃለሌ በፊት ምናልባት አንባቢያን ትምህርት ታገኙበት ይሆናል በማለት አንድ መጽሔት ሳነብ ካገኘሁት ላካፍላችሁ ብዬ ይህንን የእንጊሊዘኛ ጽሑፍ ጋብዤአለሁና አንብቡት ፡፡የተዘረዘረውን ሁሉ ለመፈጸም ቢከብድም ጽሑፉ በትዳር ሕይወት ውስጥ ከሚስት ጋር ሰላማዊ ኑሮን ለመምራት ባል ማድረግ ያለበትንና ሚስት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ የሚዘረዝር ነውና አንብባችሁ የራሳችሁን ግንዛቤ ውሰዱ ፡፡ 

Friday, November 26, 2010

ክራባት ! የሰላዩ ብዕር 
ረዳት ካሜራ
ክፍል ሦስት
እኔም በበኩሌ የባለቤቴ ጠባይ ባልተጠበቀ ሁኔታ መለወጥና በትዳራችን መካከል የነበረው ጣዕም ያለው ፍቅር እየቀዘቀዘ መምጣት እጅግ በጣም አሳስቦኝ ነበር ፡፡ እስከ ሕይወቴ ፍጻሜ ድረስ ከእርሷ ጋር ለመኖር ወስኜና ወድጃት ያገባኋት የትዳር ጓደኛዬን ከምንም በላይ እወዳታለሁ፡፡እርሷ ስሜታዊ ሆና በየምክንያቱ ብትበሳጭም ብስጭቷን የሚያበርድ እንጂ ንዴቷን የሚጨምር ሥራ ሠራሁ የምለው በእኔ በኩል አንዳች ነገር የለም፡፡እሷን የሚያስቀይም መጭፎ ነገር ማደረጌም ጨርሶ ትዝ አይለኝም፡፡ ይሁን እንጂ ለምታሳየኝ አክብሮት ለሌለው ሥነ ምግባሯ ቂም ይዤ ወይም እርሷን በክፉ ለመበቀል በጭራሽ አልሜም አስቤ አላውቅም፡፡የእኔ የሁሉ ጊዜ ምኞት እርሷ በአእምሮዋ ታድሳና ተለውጣ ማየት ነው፡፡ ወዲያው መልሳ ብትረሳውም ከእርሷ ያየሁትና የምወድላት መልካም ነገር ቢኖር ካጠፋች በኋላ የምታደርገው ጸጸት ነው፡፡ ያ እንዳልሰለቻትና እንዳልጠላት አድርጎኛል፡፡
ሰላዩ ብዕር ! ክፍል ሁለት
ከባለቤቴ ጋር ከተጋባን አምስት ዓመታት አለፉን ፡፡ በሰላምና በጥሩ ፍቅር አሳለፍን የምላቸው ዓመታት ቢኖሩ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ብቻ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በመካከላችን በሚፈጠሩ ችግሮች ዙሪያ መነጋገሩ ፤ መወያየቱና መግባባቱ ነበረን፡፡ ከሁለት አንዳችን ቅሬታ የተሰማው ሰው ካለ በግልጽ ‹ በዚህ ጉዳይ ቅር ስላለኝ መነጋገር እፈልጋለሁ › ካለ ሁለታችንም ያለምንም ተቃውሞ ለመነጋገር በደስታ እንቀመጣለን፡፡ መግባባት ባለበት ሥርዓት እንነጋገራለን ፤ እንደማመጣለን፡፡ይህ ባህሪያችን በመካከላችን ያለውን መተማመንና ፍቅር ጥሩ ደረጃ ላይ አድርሶት ነበር፡፡ 

Wednesday, November 10, 2010

       
ሰላዩ ብዕር
በዚህ ዓለም የምናየው ከፍተኛውና አስገራሚው የቴክኖሎጂ ውጤት ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድና ስጦታ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው በመልካም ሁኔታና በምቾት እርሱን እያመሰገነው እንዲኖር ነበር፡፡ ለዚህም አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ቀድመው ለሰው ልጅ የምቾት ኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ መፈጠራቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሰው እንዳይራብና እንዳይጠማ አስቀድሞ ምግብንና መጠጥን እግዚአብሔር ፈጥሮ አዘጋጀለት፡፡ እንዲሁም የሰው ልጅ በተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻቹለት፡፡ይህም እግዚአብሔር ሰውን ደስ እያለው እንዲሮር መፍጠሩን ያስገነዝበናል፡፡ ነገር ግን ስው ከተፈቀደለት የኑሮ አጥር ዘሎ ባልተፈቀደለት የሕግ ማፍረስ ኑሮ ውስጥ ሲገባ ፤ ሁኔታዎች ሁሉ ተለዋውጠው ተገላቢጦሽ ሆኑበት ፡፡ በፈጸመው ስህተት የሰው ልጅ ተፈጥሮን በራሱ ጥረትና ወዝ እየታገለና እያቀና እንዲኖር በፈጣሪ ተወሰነበት ፡፡

Friday, October 15, 2010



የልጄ ተንኮል ቢያናድደኝም መልሶ ደግሞ አሳቀኝ !
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው ሲል ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ መዝ ፡፡የሰው ልጆችም ይህንን አምላካዊ ቃል ትርጉሙን በትክክል የሚረዱት ባልና ሚስት ሆነው በሚኖሩበት ቤታቸው ውሰጥ ከአብራካቸው የወጣ ህጻን ልጅ ሲያገኙ ነው፡፡ በምጥና በጋር ልጇን ለመወለድ የቀረበች ነፈሰ ጡር ሴት ልጇን በወለደች ጊዜ ምጥና ጋሯን በመርሳት በደስታ ትዋጣለች፡፡ አባትም እንደዚሁ፡፡
የተወለዱ ልጆች ከእንጭጭነት አልፈው ሲፋፉና ድክ ድክ እያሉ ሲወድቁ ሲነሱ ማየት ትልቅ የኅሊና ደስታን ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ ልጆች በሁለትና በሶስት ዐመት እድሜ ላይ ሲደርሱ በአእምሮ፤ በአካልና በቋንቋ እድገት ቢያሳዩም ለጫወታ እያሉ የሚሠሯቸው አንዳንድ ሥራዎቻቸው የሚያስገረሙና የሚያስቁ ናቸው፡፡ በዚህ እድሜ ደግሞ የወላጆች ጥብቅ ክትትልም እጅጉን ያስፈልጋል፡፡ ልጆች በተለይ ዘወትር ከሚጫወቱበት የቤት ውስጥ ሥፍራ ሰወር ሲሉና ድምጻቸው ሲጠፋ በመጠራጠር የት እንዳሉና ምን እየሠሩ እንደሆነ በቅርብ መከታተል ተገቢ ነው፡፡ ዛሬ ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነን < Family Fun > በመባል በእንግሊዘኛ እየታተመ በሚወጣው የቤተሰብ መጽሔት ላይ ያገኘው የአንድ ቤተ ሰብ ገጠመኝ ነው፡፡ ድርጊቱ እንዲህ ነው፡፡

Thursday, October 7, 2010

እጅግ አደገኛ ነው !
እለቱ እሁድ ነው፡፡ችግሩም የተከሰተው በሰሜን ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በቅርብ ቀን ነው፡፡ ሴትየዋ በሚዝናኑበት የጀልባ ፍሪጅ ውስጥ ካስቀመጡት በቆርቆሮ የታሸጉ የለስላሳ መጠጦች መካከል ኮካ ኮላን መርጠው ይጠጣሉ ፡፡በማግስቱ ሰኞ በድንገተኛ አምቡላንስ ተወስደው ወደ ሆስፒታል ይገባሉ፡፡በጣም በመድከማቸው ወደ አይሲዩ( Intensive care unit) ይወሰዳሉ፡፡ብዙም ሳይቆዩ ከሁለት ቀናት በኋላ ረቡዕ ዕለት ሕይወታቸው ያልፋል፡፡ ሀኪሞች ለሴትየዋ ሞት ምክንያት የሆነው ‹ሌፕቶስፒሮሲሰ› በመባል የሚታወቀው አደገኛ በሽታ መሆኑን በምርመራ ያረጋግጣሉ፡፡የዚህ በሽታ ምልክት ደግሞ ሴትየዋ ከጠጡት የኮካኮላ ቆርቆሮ መጠጫ ቀዳዳ አካባቢ ባለው የቆርቆሮው አካል ላይ በምርመራው ይገኛል፡፡
የአይጥ ሽንት መርዛማና ሰው ሊገድል የሚችል አደገኛ ‹ሌፕቶስፒሮሲሰ› መርዝ በውስጡ እንደለው የሳንይስ ምርምር ውጤት ያረጋግጣል፡፡በዚህ መሠረት ሴትየዋም የሞቱት በለስላሳ መጠጥ ማመርረቻም ሆነ በማከፋፈያ ትላልቅ መጋዘኖችና በየመሸጫ መደብሮች ውስጥ የሚኖሩ አይጦች በላዩ ላይ በመሄድና በላዩ ላይ በመሽናት የተበከለውን የኮካኮላ ቆርቆሮ ሳያጥቡ ከነመርዙ አፋቸው ላይ ደቅነው በመጠጣታቸው ምክንያት ነው፡፡

Saturday, September 25, 2010

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሣችሁ ! !
ጌታችን እና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድህነተ ዓለምን ከፈጸመ በኋላ መስቀሉ ሕሙማነ ስጋን በተአምራቱ የሚፈውስ፣ የዳሰሱትን ሁሉ የሚያድን ሆኗል። በዚህ ተዓምራት የተሳቡ አንድ አንድ አይሁዶችም ክርስቲያኖች ይሆኑ ነበር። ይህ ያስቆጣቸው አይሁዶች ደግሞ መሬት ቆፍረው ቆሻሻ ደፍተው እና ተራራ ሰርተው መስቀሉን ቀበሩት። በዚህ ሁኔታ ለሶስት መቶ አመታት መስቀለ ክርስቶስ ተዳፍኖ ቆየ።

በሮም ላይ ነግሰው ከነበሩት ደጋግ ነገስታት ቆስጠንጢኖስ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነገሰ። ንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናቱ እሌኒ በልዩ ክርስቲያናዊ ህይወት ኮትኩታ ያሳደገችው ክርስቲያን ንጉስ በመሆኑ በዘመነ መንግስቱ የክርስቲያኖችን ነጻነት ያወጀ ነበር። እናቱ ቅድስት እሌኒ በአረጋዊ ኪራኮስ ምክር ደመራ አስደምራ፣ እጣን አስጢሳ ሊቀ ቅዱስ ያሬድ በድጓው “ዘእጣን አንጾረ ሰገደ ጢስ” እንዲል፤ የእጣኑ ጢስ ወደላይ ወጥቶ ወደታች በመመለስ መስቀሉ ያለበትን ስፍራ አመለከታት። ለዘመናት ተቀብሮ የኖረውን መስቀል አስቆፍራ አወጣችው።

ለድህነተ አለም ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋውን የቆረሰበት ደሙን ያፈሰሰበት እጸ መስቀል በአረማዊያን ዘመን ቢቀበርም ክርስቲያኖች ነጻነት ባገኙበት የሰላም ዘመን ወጣ። ሲወጣም እወር በማብራት፣ አንካሳ በማርታት፣ ጎባጣ በማቅናት፣ ለምጽ በማንጻት፣ ሙት በማስነሳት ተዓምራት አድርጓል።

ሰለ ክብረ መስቀል ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ቅዱሳት መጻህፍት እና የልዩ ልዩ ጉባኤያተ ቀኖናት ያወሳሉ። ነገረ መስቀል የማናቸውም አገልግሎት መግቢያ በር እንደመሆኑ መጠን ካህናት በእጀ መስቀላቸው፣ ምእመናን በትምህርተ መስቀል ማማተብ ከተግባሮቻችን ሁሉ ቀዳሚ ነው።የመስቀሉ በረከት በሁላችንም ይደር አሜን !

Tuesday, September 21, 2010

የአህዮች እናት እንደምን አደሩ?

በአንድ የገጠር መንደር ውስጥ ሁለት አህዮች ያሏቸው አንድ አሮጊት ሴት ነበሩ፡፡በዚያው መንደር ውስጥ ደግሞ አሮጊቷ ሴት አህዮቻቸውን እየነዱ ዘወትር በሚመላለሱበት መስቀለኛ መንገድ ላይ የተከመረ ድንጋይ ነበር፡፡ በዚያ ላይ ተኮልኩለው አላፊ አግዳሚውን የሚተቹና የሚተርቡ ስነ ምግባር የጎደላቸው ጥቂት ወጣቶች ነበሩ፡፡ እነዚህ የመንደር ጎረምሶች እንደ ለማዳቸው አሮቷ ሴት አህዮቻቸውን በጧት እየነዱ በዚያ መንገድ ሲያልፉ አሮጊቷን ለማብሸቅ ብለው ‹ የአህዮች እናት እንደምን አደሩ ? › አሏቸው ፡፡ ሰላምታው የተረብ መሆኑ የገባቸው አሮጊቷም መለስ አድርገው ‹ እግዚአብሔር ይመስገን ልጆቼ ! እንደምን አደራችሁ ፡፡ › ብለው አጸፋቸውን መለሱ፡፡

Monday, September 13, 2010

  IF YOU WANT..... 

Friday, September 10, 2010

በአዲስ ዓመት አዲስ ፍሬ

ስማቸውንና ምንጩን ሳይጠቅሱ ይህን ትምህርታዊ ጽሑፍ በአድራሻችን የላኩልንና የዝግጅታችንን ተከታታይ ከልብ እያመሰገን ትምህርቱ ወቅታዊ ሆኖ ስላገኘነው እኛም አንባቢያን እንዲማሩበት በማለት አቅርበነዋል።

አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ በእለተ ረቡዕ ቀንና ሌሊትን ብርሃንና ጨለማን የሚለዩ ለዕለታትታት ለወራትና ለዓመታት መቁጠሪያ የሚያገለግሉ በሰማይ ጠፍር ላይ ብርሃናት ይሁኑ ብሎ በማዘዝ ጸሐይን በቀን ጨረቃንና ከዋክብትን በሌሊት እንዲያበሩ ፈጥሯል። እነዚህም ፍጥረታት ከተፈጠሩበት ዕለት ጀምሮ የተፈጠሩበትን አላማ ሳያዛቡ የፈጣሪን ትእዛዝ ሳያጓድሉ ክረምትንና በጋን ሲያፈራርቁ ሰዓታትን በዕለታት እለታትን በሳምንታት ሳምንታትን በወረት ወራትንም በአመታት እያፈራረቁ ለሰው ልጅ ሕይወት ጥቅም እየሰጡ ይገኛሉ። ኦሪት ዘፍ1፥14፡19

Thursday, September 9, 2010

ለምን የሚጠቅመንን አንለምንም ?
አንድ እራሱን በጣም አድረጎ የሚወድ ሰው ሁል ጊዜ ‹ እግዚአብሔር ሆይ ስጠኝ ስጠኝ ስጠኝ ... › እያለ አዘውትሮ ይጸልይ ነበር ፡፡ የነገሩትን የማይረሣ የለመኑትንም የማይነሣ አምላክም አንድ ቀን ተገለጠለትና ‹ ጸሎትህን ሰምቼ አሁን የምትሻውን ነገር ሁሉ ላደርግልህ መጥቼአለሁና ደስ ይበልህ ! አለው፡፡ ሰውየውም ጸሎቱን ሰምቶለት እግዚአብሔር ወደ እርሱ ስለመጣ እጅግ በጣም ደስ አለው፡፡እግዚአብሔርም መልሶ ‹አንተ የለመንከኝን ነገር ሁሉ እጥፍ አድርጌ ለጓደኛህም እሰጠዋለሁና ምን እንዳደርግልህ ትፍጋለህ ? አለው፡፡ ይህን ጊዜ ሰውየው ባዘነ መንፈስ ትንሽ አሰብ አደረገና ‹ ጌታ ሆይ እንግዲያውስ አንድ አይኔን አጥፋው ፡፡ › ብሎ አረፈ ፡፡ የእርሱ አንድ ዓይን ሲጠፋ የጓደኛ ሁለት ዓይኑ ይጠፋልና፡፡

Tuesday, September 7, 2010

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የ1.5 ሚሊዮን ዶላር ካሣ እንዲከፍል በሕግ ተጠየቀ !
በዚህ በምንኖርበት የሰሜን አሜሪካ ግዛት በወሲብና በገንዘብ ቅሌት ምክንያት ፍርድ ቤት ቀርበው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንዲከፍሉ ቅጣት የተጣለባችውና ይህን መክፈል ተስኖአቸው ቤተ ክርስቲያኖቻቸው በላያቸው ላይ የተሸጡባቸው የኒውዮርክና የካሊፎረኒያ ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ለአብነት የሚጠቀሱ ሲሆኑ በዚህና በተመሳሳይ ችግሮች ምክንያት ለገበያ የሚቀርቡ ቤተ ክርስቲያኖችም ቁጥራቸው ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱ ክርስትናውን ግምት ውስጥ እየከተተው መምጣቱን ያመለክታል፡፡

Wednesday, August 25, 2010

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለYahoo, Hot mail , AOL ወ.ዘተ. ሜይል ተጠቃሚዎች በሙሉ
ዓለም በቴክኖሎጂው ስልጣኔ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሳለች ፡፡ብዙም ነገር ከሰው አእምሮና ጉልበት አሠራር ወደ ኮምፒውተር ሥራ እየተቀየረ ነው፡፡ ሥራ ፈትነትን ከማስፋፋት አንጻር ደግሞ ይህ ሁኔታ በሰው ልጅ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እራሱን የቻለ ችግር ቢኖረውም ሥራን ከማቀላጠፍና በጥራት ከመሥራት አንጻር ደግሞ ኮምፒውተር የሚሠጠው ጥቅም ቀላል ግምት የሚሠጠው አይደለም ፡፡ይሁን እንጂ ይህንኑ መልካም ሥራውን ለማደናቀፍ የኮምፒውተርን ውስጣዊ አካል እንደ ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ጠንቅቀው የሚያውቁ ባለሙያዎች በኢንተርኔቱ መረብ በኮምፒውተር ውስጣዊ የመረጃ ክፍል ላይ የኤሌክትሪ መርዝ በመልቀቅ የኮምፒውተሩን መዝገብ ቤት ፋሎች በመደመስስ ከፍተኛ ጉዳትና ኪሣራን በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ላይ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡

Monday, August 23, 2010

Saturday, August 21, 2010

የሚያኖረን ቸርነቱ ነው !
የእግዚአብሔር ቸርነትና ጸጋ ሃብታሙንም ደሃውንም ፤ ጤነኛውንም ታማሚውንም ፤የሚደስት የሚያዝነውን ወዘተ... ሁሉንም በየደረጃው ያኖረዋል፡፡ ለምሳሌ በሰው ዘንድ ማጣት ችግር በሆንም ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሰውን በምቾት ምክንያት እግዚአብሔርን እንዳያጣ መጠበቂያ መንገድ ነው፡፡ ሕመም በሰው ዘንድ ስቃይ ቢሆንም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሰውን ወደ እርሱ ማቅረቢያ ሌለኛው መንገድ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ሁሉንም በእኛ የምናየውና ጉዳት የሚመስለን ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ በጎና መልካም የሆነ ምክንያት አለውና ነገር ሁሉ ለበጎ መሆኑን አንዘንጋ ፡፡ የሚያኖርን የእግዚአብሔር ቸርነትና ጸጋ እንጂ ገንዘባቸን ወይም ጥበብና እውቀታችን ብቻ እንደሆነ አድርገን እንዳናስብ እንጠንቀቅ፡፡

Tuesday, August 17, 2010


BE BLESSED BY READING THIS!!!
Learn from yesterday, Live for today, Hope for tomorrow…

An Angel says, 'Never borrow from the future. If you worry about what may happen tomorrow and it doesn't happen, you have worried in vain. Even if it does happen, you have to worry twice.'

Monday, August 16, 2010


Saturday, August 7, 2010



ነፋስም ወደ ፊታቸው ነበ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር እየተመላለሰ በሚያስተምርበት ጊዜ ልዩ ልዩ አስደናቂ ገቢረ ተአምራትን አድርጓል። ድውያነ ሥጋን በተአምራት ድውያነ ነፍስን በቅዱስ ቃሉ ፈውሷል። በባሕር ላይ በመሄድ ነፋሳትን በመገሰጽ በተፈጥሮ ላይ ያለውን ኃይል አሳይቷል። ምንም በሌለበት ምድረ በዳ ሁለት ዓሣና አምስት የገብስ እንጀራ አበርክቶ ከአምስት ሺህ ሰው በላይ እንዲመገብ አድርጓል። በልተው የተረፈ አሥራ ሁለት መሶብ ቅርጫት ተነስቷል። ይንን ያዩ እሥራኤላዊያን ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት የተናገሩለት መሲህ ይህ ነው በማለት ሊያነግሱት ፈልገው ነበር።
ዮሐ 6፥15

Monday, August 2, 2010

የጤፍ አዝመራ በሰሜን አሜሪካ

Thursday, July 29, 2010

በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን !

“ነአምን በአሐቲ ቤተ ክርስቲያን፣ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” (ጸሎተ ሃይማኖት)
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ሐዋርያዊት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት። በአንድነቷ ጸንታ፣ በሐርያዊነቷ የአበው ሐዋርያትን ትምህርትና ትውፊት እንዲሁም ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ጠብቃ፣ በቅድስናዋ ዕድፍ ጉድፍ ሳይወድቅባት፣ ኃጥአንን ከኃጢአት ርኵሰት የምትቀድስ ናት። የምናምነው፣ የምናገለግለው፣ የምንኖረው ለዚህች እና በዚህች ቤተ ክርስቲያን ነው። “በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን” ስንል ሁሉን በሁሉ ይዘን እንጂ በግማሽ አይደለም። ለሚጠይቁንም ስንመልስ ጊዜውን አይተን፣ የሰዎችን ፊት አይተን ሳይሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ብቻ ተመልክተን ነው።

Wednesday, July 28, 2010

ዘዳላሰ ነኝ ፡፡ከፌስ ቡክ ያገኘሁትን እነሆ ልኬአለሁ ያሉንን የዝግጅታችንን ተካታታይ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል !
ይህ የሃገራችን አባባል ብዙ ጊዜ ለሚቸኩሉና በችኮላቸው ጥፋት ለሚያደርሱ ሰዎች መረጋጋት እንዲኖረቸው ለመምከር የሚተረት ወግ ነው፡፡ ቅቤ በክብርና በፍቅር ከሚበሉ ምግቦች መካካል አንዱ ሲሆን አወጣጡና አዘገጃጀቱም በየሃገሩና በየባህሉ የተለያየ ነው፡፡እንደምናውቀው በእኛ ባህል ቅቤን ለማውጣት ወተቱ ጊዜ ወስዶ መርጋት አለበት፡፡ ለዚህ ነው አበው ሰውም ከተረጋጋና ጊዜ ወስዶ ነገሮችን እያስተዋለ ከሠራ ለጥሩ ውጤት እንደሚበቃ ለማመልከት ‹የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል› በማለት የሚተርቱት ፡፡ ከዚህ አንጻር እኛም ስለመረጋጋት ግንዛቤ ታገኙ ዘንድ የሚከተለውን ጽሑፍ በአጭሩ አቅርበነዋል፡፡

Wednesday, July 21, 2010




አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ! በቤተ ክርስቲያን ከሚቀልዱ ፤ ግፍ ከሚሠሩና ፖሊተከኞች ነን ከሚሉ ኢ-አማንያን እጅና አመራር ቤተ ክርስቲያንህን ታወጣት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ስትል ባፈሰስከው ደምህና በቆረስከው ሥጋህ እንለምንሃለን ፡፡

መለያየት በመካካላቸው ገብቶ የተለያዩትን አገልጋዮችህ የሆኑ አባቶቻችንንም በሃሳባቸው ሁሉ አንድ እንድታደርግለን እንማጸንሃለን፡፡ አሜን፡፡

Monday, July 19, 2010

ትዕቢት እና ትሕትና 
ትዕቢት የትሕትና ተቃራኒ ነው፡፡ትዕቢትን ከሚገልጡት ድርጊቶች መካከል አንዱ የኩራትና የእብሪት ንግግር ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ንግግራችን ተጠያቂ የሚያደርገን ክፉ ቃላትን ከሚወልደው የትዕቢት ልብ የተነሣ ነው፡፡

ትሑት መሆን የሚሻ ሰው ሰውን ከሚያሳዝንና የሰውን ኅሊና ከሚጎዳ የትዕቢት ንግግር መራቅ አለበት፡፡ ስሜት የሚጎዱ ንግግሮች የምንናገረው ሰዎች ስላስቆጡን ሊሆን ይችላል ፡፡ይሁን እንጂ ቁጣና ኃይል የተቀላቀለበት ንግግራችን ከመንፈሳዊ ሥነ ምግባራችን መገለጫዎች አንዱ የሆነውን ትሕትናችንን በእጅጉ የሚጎዳ ነው፡፡ስለዚህ ምንጊዜም ቢሆን ቶሎ ከመቆጣትና የሌሎችን ሰዎች ስሜቶች ከሚጎዱ ንግግሮች መራቅ ተገቢ ነው፡፡የትዕቢት ንግግር ሰይጣን የወደቀበትና ክብሩን ያጣበት ክፉ ተግባር ነውና፡፡

ሰው ትዕቢትን ከልቡ ማራቅ ከቻለ የትሕትና ባለቤት ለመሆን አይቸገርም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ‹እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል› በማለት ትዕቢት የውርደት ምልክት ፤ ትሕትና ደግሞ ለሰው ልጆች ክብርና ሞገስን የሚያጎናጽፍ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደ ምግባር እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ያዕ 4፡6


ትሕትና የመንፈሳዊ ሰዎች መገለጫ ጠባይ ነው፡፡ትሑት ሰው ሁሉን ይወዳል ፤ታዛዥና ትዕግስተኛም ነው፡፡ እስቲ ታዲያ እኛም ትዕቢትን ከልባችን አጥፍተን የትሕትና ሰዎች ለመሆን እንሞክር !

Monday, July 12, 2010

እንዳትለያዩ እለምናችኋለሁ !


‹ወንድሞቻችን ሆይ !ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ እንዳትለያዩ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆናችሁ አንድ ቃል ትናገሩ ዘንድ በአንድ ሃሳብም ትመሩ ዘንድ በጌታችን ፤ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥም እለምናችኋለሁ፡፡›1ኛ ቆሮ 1፡10

በሐዋርያው ትምህርት አንድ ልብ አንድ ሃሳብ መሆን ማለት በመልካም ሥራና በሃይማኖት ከእግዚአብሔር ጋር አንድ መሆን ማለት ሲሆን ልቡናን ከቂምና ከበቀል ከክፋት ንጹሕ በማድረግ የዋህነትን ፤ትህትናንና ንጽሕናን ገንዘብ አድርጎ መገኘት ማለት ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ በ 50 ዓ.ም ወደ ቆሮንቶስ ከተማ ገብቶ ወንጌልን አስተምሮ የቆሮንቶስን ሰዎች ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር ፤ ከኃጢኣት ኑሮ ወደ ቅድስና ሕይወት መለሳቸው፡፡ ጌታም ለሐዋርያነት ሲጠራው ‹በአሕዛብ ፊት ስሜን ትሸከም ዘንድ ምርጥ ሐዋርያ አድርጌ ሾሜሃለሁ፡፡ ›ሐዋ 9፡15 ብሎ እንደ መሠከረለት ብዙ አሕዛብን በወንጌል አስተምሮ ወደ ክርስትናው በረት አስገብቷል፡፡

Thursday, July 8, 2010

 ለፈገግታ
በብዙ የዓለም ሀገሮች በተለይም በሃገራችን በኢትዮጵያ ያላውን የኑሮ ሁኔታ ስናስብ በአዕምሮአችን የሚመጣው የብዙኃኑ ሕዝብ ድኅነትና የጥቂት ሃብታሞች ጣራ የነካ የምቾት ኑሮ ነው፡፡ የድኃውና የሃብታሙ ኑሮ ልዩነቱ የሰማይና የምድር ያህል የተራራቀ ነው፡፡ድሃው በእግዚአብሔር ቸርነት የሚኖር እንጂ የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ፍጹም ድኃ ነው፡፡ ሃብታሙ ደግሞ የእግዚአብሔር ቸርነት በዝቶለት ገንዘቡን የት ላድርሰው የሚል ቱጃር ነው፡፡ በዚህ መሃል ያለው ደግሞ የድሃና የሃብታም ክልስ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ ድሃውም ሃብታሙም መካከለኛውም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋና በወሰነለት የኑሮ ደረጃ ይኖራል፡፡ ግን ደግሞ ማኅበራዊ ኑሮ አለና በአጋጣሚ ፤በሃዘን ወይ በደስታ አንዱ ሌላውን የመጎብኘትና የኑሮ ሁኔታውን ማየት እድል ያገኝ ይሆናል ፡፡ብዙ ጊዜ ደሃው ወደ ሃብታም ቤት ለጉልበት ሥራ ወይም ሃብታሙ ሰው ለሚፈልገው ጉዳይ እየጠራው ሊሄድ ይችላል፡፡አልፎ አልፎ ደግሞ ምናልባትም ለቅሶ ካለ ለቅሶ ለመድረስ ሃብታም ወደ ድሃው ቤት ሊሔድ ይችል ይሆናል እንጂ የሃብታሙ እግር ወደ ድሃው ቤት ለመሄድ ያጠረ ነው፡፡ጊዜውም ፍላጎቱም የለውም ፡፡ታዲያ አንድ ድሃ የጉልበት ሠራተኛ አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው ቦሌ ሠፈር የሃብታሞችን ቤት የግቢ አትክልት ለመኮትኮትና ሣር ለማጨድ እያሰለሰ ይሄዳል፡፡ሥራውን የጀመረ ሰሞን ጥቂቶቹ ሃብታሞቹ ወደ ቤት ገባ ብሎ ሻይ እንዲጠጣ ይጋብዙታል፡፡ እርሱም ደስ እያለው ይገባና እየተናደደ ይወጣል፡፡

ግን አንድ ቀን እንደህ ሊል ሰማሁት፡፡ የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ ነው እንጂ አሁንስ እንደ ሃብታም ቤት መሄድ የጠላሁት ነገር የለም፡፡ እኔም ምነው ለምን አልኩት እሱም የሆነውን ነገር በጥያቄና መልስ አስመስሎ ነገረኝ እኔም ተደነኩኝ በማለት ለፈገግታ ያቀረበልን እኛም ስሙን የማናውቀው አንድ ኢትዮጵያዊ ወገናችን ነው፡፡ እኛም ከአስተያየት መቀበያ ሳጥናችን ውስጥ ስላገኘነው የላኩልንን ደንበኛችንን ከልብ እያመሰገንን አንባቢዎቻችን እንዲያነቡት በማለት በብሎጉ ፊት ለፊት ሰሌዳ ላይ ለጥፈነዋልና ያንብቡት፡፡

Wednesday, July 7, 2010

ለምኑ ይሰጣችኋል !
                                       ማቴ 7፡7

እግዚአብሔርን ፈልጎ ያላገኘው ፤ ለምኖም ከእርሱ ያልተቀበለ ሰው የለም ፡፡ ቢሮር እርሱ በእግዚአብሔር ያልታመነ ወይም ለጸሎት የሰነፈ ብቻ ነው፡፡ የተራበ ፤የተጠማ ፤ የታረዘ፤ የተራቆተ፤ በችግር የተጎዳና የመሰከነ ሁሉ ቢለምን እግዚአብሔር ሊሰጠው የታመነ አምላክ ነው፡፡

ምክንያቱም እግዚአብሔር በቅዱስ ቃሉ ‹ ለምኑ ይሰጣችኋል ፤ ፈልጉ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያውን አንኳኩ ይከፈትላችኋል ፡፡ የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና ፡፡የሚፈልገውንም ያገኛል፡፡መዝጊያውንም ለሚያንኳኳ ሁሉ ይከፈትለታል፡፡ › በማለት ተናግሯልና፡፡ ማቴ 7 ፡ 7

ከዚህ አንጻር የልመናው ( የጸሎት ) ዘዴው የገባቸው ብልጦች ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን በመለመን ብዙ አግኝተዋል፡፡ ስለተደረገላቸው ሁሉ ብዙ አመስግነዋል፡፡ያመሰግናሉም፡፡ ስለዚህ ስለጸሎትና ምስጋና ሰላም ተዋሕዶ ከበራሪ ኢ-ሜይል ያገኘቻትን አጭር የእንግሊዘኛ ጽሑፍ ለአንባቢያን ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘችው እንደሚከተለው ታቀርበዋለች፡፡


Tuesday, July 6, 2010

እንቁላል በመወርወር የሚፈጸም ዝርፊያ
በጭለማና ጭር ባለ አካባቢ ሲነዱ የተወረወረ የዶሮ እንቁላል በመኪናዎ የፊት መስታወት ላይ አርፎ ከተሠበረ የዝናም መጥረጊያ መሣሪያውን ወይም መስታወቱን ለማጽዳት የሚረጨውን ውሃ እንዳይጠቀሙ ይጠንቀቁ ፡፡ በመስታወት ላይ የፈሰሰ የእንቁላል አስኳል ከውሃ ጋር ሲደባለቅና በዝናም መጥረጊያ ሲጠረግ ወተታማ ወይም ደመናማ ቀለምን ይፈጥርና መስታውቱን 92.5 % ያህል ከእይታ አገልግሎት ውጪ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ፊት ለፊትዎን በመኪናው የፊት መስታወት ማየት ስለሚሳኖት ለአደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ አሊያም አደጋውን ለመሸሽ ሲሉ መኪናውን ወደ ዳር አውጥተው ለማቆም ይገደዳሉ ፡፡ በዚህ ጊዜ በአካባቢው የመሸጉና እንቁላሉን በመኪናዎ መስታወት ላይ የወረወሩት ዘራፊዎች በፍጥነት ወደ እርሶ በመምጣት ችግር ላይ ሊጥልዎት ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ ይህ አዲሱ የዘራፊዎች የዘረፋ ስልት ነውና መንገድዎን ለእግዚአብሔር አደራ በመስጠት በማያውቁት መንደር በጨለማ ሲነዱ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

Monday, July 5, 2010

ማሳሰቢያ
ሰላም ተዋሕዶ ላለፉት በርካታ ወራት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲን ችግሮችና ከዚሁ ጋር በተያያዙ እንዲሁም እውነትን በተመረኮዙ ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ በስፋት ስትዘግብ መክረሟ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚሁ ጋር የአገልግሎት አድማስዋን ከፍ በማድረግ ከዳላስ ውጭ ለማንኛውም የብሎጉ አንባቢ ትምሕርት ይሰጣሉ ተብለው የሚታመኑባቸውን መንፈሳዊና አስተማሪ ጽሑፎችን በማቅረብ ተጠናክራ የምትቀጥል መሆኑን በአክብሮት ትገልጻለች ፡፡

Thursday, July 1, 2010

Marriage is an institution in which a man loses his Bachelor's Degree and the woman gets her masters.
ስለ ትዳርና ጋብቻ በእኛም ሆነ በሌላው ዓለመ ሰብእ ብዙ ተብሏል፡፡ብዙም ይባላል፡፡ በትዳር ውስጥ ስላለ ደስታና ኃዘን ፤ ቁጣና ትዕግስት ወ.ዘ.ተ… በጋዜጣ ፤ በመጽሔት፤ በሙቪና በሌሎችም መገናኛ ብዙኃን በየቋንቋውና በየባህሉ በመዝናኛና በትምህርት መልክ ብዙ ጊዜ ይተላለፋል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትዳርስ የእነ እገሌ ነው› እየተባለም ይመሰገናል፡፡ ይወደሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ‹ትዳር እንዲህ ከሆነስ ቆሞ መቅረት ይሻላል፡፡› እየተባለ ትዳር ሲነቀፍና ሲቀለድበት ይሰማል፡፡ለማንኛውም ባለትዳሮች ትዳራችሁን ዘወር ብላችሁ እንድታዩት ወደ ትዳር ለመምጣት በመንገድ ያላችሁና የወጠናችሁ ሁሉ ትምህርት ታገኙበት ይሆናል በማለት አሜሪካኖች በቋንቋቸው ስለትዳር የከተቧትን ቁምነገር አዘል ቀልድ ከበራሪ ኢ-ሜይል አግኝተን ከዚህ ቀጥለን አቅርበነዋልና አንብባችሁ ተማሩበት፡፡

Tuesday, June 29, 2010

ለፈገግታ

‹የብሎጋችሁ ተከታታይና አንባቢ ነኝ ፡፡ አምዳችሁ አንዳንዴም ፈገግ የሚያሰኝ ቁም ነገር አዘል ቀልድ ሊኖረው ይገባል ብዬ ስላሰብኩ ይህንን በአስተያየት መስጫ ሳጥናችሁ በኩል ልኬላችኋለሁና እንደምታደርጉ አድርጓት ፡፡ › ያሉን ደንበኛችንን ከልብ እያመሰገን እኛም በፈገግታ ቀልዱን ለአንባቢያን ከጓዳው ሳጥን አውጥተን ወደ ብሎጉ ሳሎን አምጥተነዋልና እነሆ፡፡

Sunday, June 27, 2010

የጁን 26 ሕዝባዊ ስብሰባ በመልካም ሁኔታ ተጠናቀቀ !
በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርቲያን አስተዳደር ችግር ምክንያት የተናጋውን የቤተክርስቲያኒቱን ሰላም በውይይት ማስተካከል ባለመቻሉ ጉዳዩ እጅግ ባሳሰባቸው በርካታ ምእመናን በሜይ 8ቱ ሕዝባዊ ስብሰባ ተወክሎ ጥረቶችን ሲያደርግ የሰነበተው የመፍትሔ ፈላጊ ኮሚቴ ቅዳሜ ጁን 26 ቀን 2010 በተጠራው ሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ስላከናወናቸው ተግባራት ሪፖርቱን አቀረበ፡፡

Saturday, June 19, 2010

የዓርብ ጉባዔ በአዲስ መልክ ተጀመረ፡፡

ቀደም ሲል በሃይማኖት አባቶች በመልአከ ሣህል አወቀ ተሰማና በቀሲስ መስፍን ደምሴ ይሰይጥ የነበረው የዓርብ ጉባዔ ካለፈው ዓርብ June 18 2010 ዓ.ም ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል ፡፡ይህ በደብሩ በተከሠተው ችግር ምክንያት የተበተኑትንና አዝነው በየቤታቸው የተቀመጡትን ምእመናን ሁሉ በማሰባሰብና አንድ ቤተ ሰብእ ለማድረግ የተጀመረው ጉባዔ በእለቱ በርካታ ምእመናን የተገኙበት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡ 

Friday, June 11, 2010

 የስብሰባ ጥሪ

በስመ አብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በአስተዳደር ብቃት አለመኖር ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ ቀደም ሲል በበጎ ፈቃደኝነት በተነሳሱ ሽማግሌዎችና የሰላም ልዑካን አማካኝነት ብዙ ጥረት እንደ ተደረገ ይታወቃል፡፡

Tuesday, June 8, 2010

የአስተዳደር ቦርዱ የአባላትን መብት ከመርገጥ አልፎ ጨፈለቀው !

እዚህ ይጫኑበአስተዳደር ቦርድ ችሎታ ማነስ ምክንያት እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጥፋት በወቅቱ ለማስቆምና የሚበጀውን ሰላም ለማምጣት ሲሉ ግለሰቦች ፤ሽማግሌዎችና የሰላም ልዑካን ሁሉ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ድካሙ በአስተዳደር ቦርዱ እምተኝነት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጥረቱን በመቀጠልና ተስፋ ባለመቁረጥ የቤተክርስቲያኑ የወደፊት ሁኔታና ዕጣ እጅግ አድርጎ ያሳሰባቸው ቁጥራቸው ከ35 በላይ የሚሆኑ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ለመሻትና ሌሎች ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉትን አባላት ሁሉ ጨምረው ለመወያየትና በጋራ መፍትሔ ለመፈለግ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጥያቄ በጽሑፍ ቢያቀርቡም የአስተዳደር ቦርዱ በተለመደው የእንቢተኝነት ባሕርዪው አዳራሹን መጠቀም እንደማይችሉ በመግለጽ ከልክሏል፡፡ 

Monday, June 7, 2010

ሠበር ዜና !

   
አዲስ አበባ

 የዳላሰ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ጸሐፊና የውብ እንጀራ ባለቤት የሆኑት አቶ አበበ ጤፉ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያደረሱት የከፋ የአስተዳደር በደል 90% በሚሆኑ አማንያን ዘንድ እጅግ እንዲጠሉ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ለአካካቢው ነዋሪ በየመደብሩ የሚያስቀምጡት የውብ እንጀራ ገዢ አጥቶ በመበላሸት እየተጣለ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ አቶ አበበና አጋሮቻቸው የቤተክርስቲያኒቱን ካህን ያለአግባብ ከሥራ ያሰናበቱትና ፖሊስ በመቅጥር ሕዝቡን ያስደበደቡት ገና ወደ ቦርድ በገቡ በሦስት ወራቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ 

Tuesday, June 1, 2010

ማኅበረ ቅዱሳን ጉባዔውን በመልካም ሁኔታ ጀምሮ አጠናቀቀ !

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 12ኛ መደበኛ ጉባዔ በዳላስ ከተማ ተካሄደ ፡፡
ከ May 28 - 30 ድረስ በቆየው በዚሁ ጉባዔ የዓመቱ የማኅበሩ ሥራዎች ግምገማ ሪፖረት የቀረበ ሲሆን የቀጣዩን ዓመት የሥራ ዕቅድና በጀትንም አጽድቋል፡፡http://www.timeanddate.com/worldclock/fullscreen.html?n=7
;

አስካሁን ከተደረጉት የማኅበሩ ዓመታዊ ጉድባዔያት በዐይነቱና በይዘቱ ከፍተኛ ነው በተባለው በዚሁ ጉባዔ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤዎስታጤዎስ የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች በርከት ያሉ ካህናትና ከመቶ ሃያ በላይ የሚሆኑ የማኅበሩ አባላት በተወካይነት ተካፋይ ሆነዋል ተብሏል፡፡
ይህንኑ የሰሜን አሜሪካ 12ኛውን ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ May 31 2010 በክራውን ፕላዛ ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀው ትምህርታዊ ጉባዔ ቁጥሩ ከ 200 በላይ የሚሆን ህዝብ የተገኛ ሲሆን ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረትና ማኅበሩ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ተሳትፎ ከማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በነበሩና ማኅበሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያገለገሉ ባሉ አባቶችና ወንድሞች ሰፊ ገለጻና ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ትምህርታዊ ጉባዔ መልአከ ሳሌም አባ ገብረ ኪዳን ፤ መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅንና ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ በተጋባዥ መምህርነት ተሳትፈዋል፡፡
በዚሁ ጉባኤ ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያም ሆነ በውጭው አለም ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከተውንና እያበረከተ ያለው የሙያ፤የገንዘብ፤የጉልበትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በእውነተኛዪቱ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ እንዲወደድና እንዲደገፍ ያደረገው ቢሆንም የቤተክርስቲያናችን መሠረታዊ ጠላቶች የሆኑ መናፍቃንና አስመሳይ ፖለቲከኞች ግን የስም ማጥፋት ሥራዎችን እንደተያያዙትም ተገልጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሕዝቡም ለመናፍቃንና ለእነዚህ አስመሳይ ፖለቲከኞች ፕሮፓጋንዳና የሐሰት ወሬ ጆሮውን እንደማይሠጥና ዳግመኛ እንደማይወናበድ ውስጣዊ ስሜቱን በቁጭትና በቃላት ገልጧል፡፡

በመጨረሻም ሕዝቡ ስለቤተክርስቲያን አጠቃላይ ገጽታዎች ግንዛቤንና እውቀትን እንዲያገኝ እንዲህ ዓይነት ጉባዔያት በተወሰኑ ወራት ሊዘጋጁ እንደሚገባ በማሳሰብ የጉባዔው ፍጻሜ ሆኗል፡፡






Tuesday, May 25, 2010

መንፈሳዊ ጉባዔ

ቤተ ክርስቲያን በውጪው ዓለም ስላላት ይዘት

በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የማኅበረ ቅዱሳን ተሳትፎ

ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ትምህርት የሚሠጥበትና ውይይት የሚደረግበት 
መንፈሳዊ ጉባዔ

ግንቦት 23 2002 ( May 31 2010)

ከ 5:00 pm ጀምሮ
ቦታ
Crown Plaza on the NW corner of 1635 &  coit Rd.7800 Alfa Rd
Dallas , TX, 75240

 የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት በዐውደ ርእይ ይመልከቱ 
 

Saturday, May 22, 2010

Be Aware of a Silent Dog ከዝምተኛ ውሻ ተጠበቁ!

ከላይ በርእስ ለተቀመጠው ኃይለ ቃል ባለቤቱ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፡፡ፊል 3፡2፡፡ ይሁን እንጂ እንግሊዞችም Be aware of a silent Dog and still water ከዝምተኛና ከረጋ ውሃ ተጠበቁ ! በማለት ወደ ወግ ቀይረውታል ፡፡ 

Tuesday, May 18, 2010

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውዝግብ በቻናል 4 FoX ቴሌቪዥን በአየር ላይ ዋለ



በዚህ ባለንበት በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዲሞክራሲያዊት ሀገር በአሜሪካ ይህ መደረጉ የሚያስገርም ነው !

Monday, May 17, 2010

ሠበር ዜና

ሚያዚያ 24 2002 ( May 2 2010 ) በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ ወንጀለኛን በውሻ የሚፈልጉና ቦንብ ፈታሽ የሆኑ ልዩ የፖሊስ ሠራዊትን ቀጥሮ በቤተ መቅደስ ውስጥ የፈጸመውን ግፍና ድብደባ በተመለከተ በዩቱብ ለአለም የተሠራጨው የቪዲዮ ፊልም የሜዲያን ትኩረትን ስለሳበ ዛሬ ሰኞ May 17 2010 ከምሽቱ 9.00pm ላይ በቻናል 4 ላይ በቴሌ ቪዥን ይተላለፋል፡፡

Sunday, May 16, 2010

የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ ሆይ ነው !

ከላይ ለዚህ ጽሑፍ ርእስ የሆነውን ዓረፍተ ነገር ‹የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ› ነው፡፡ የሚለው የአገራችን ይትበሀልና ተረት የበለጠ ይገልጸዋል፡፡ ሰንበቴ የሚባለው የቦርድ ልሳን የሆነው ብሎግ ከጀመረበት ቀን አንስቶ እንደ ሞኝ ዘፈን ወይም ለቅሶ መላልሶ የሚያሰማው አንድ ነገር አለው፡፡ ይህ ደግሞ ቦርድን በምን መንፈስ እንደሚያስብና እንደሚሠራ ለማን ሲል ደግሞ መከራውን እንደሚያይ በግልጽ መረዳት የሚያስችልና የሚጠቁም ነው፡፡

Friday, May 14, 2010

የሰሞኑ ዜና

የአስተዳደር ቦርዱ መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ ካሰናበተበትና ቀሲስ መስፍንም የአስተዳደሩን የተባላሸ አሠራር በመጠየፍ ሥራቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁበት ቀን ጀምሮ በአስተዳደሩም ሆነ በአባትና ልጅ ካህናት እንዲሁም በምእመናኑ መካከል ውጥረትና አለመረጋጋት መፈጠሩን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ካህናትንና ምእመናንን በማባረር ሰላም አመጣለሁ በማለት ሌት ከቀን ለጥፋት የሚደክመው ቦርድ በስሜትና ባለማስተዋል የፈጸማቸው ከፍተኛ ስህተቶች ከአስተዳደሩ አልፎ በቤተ ክርስቲያኒቱ የወደፊት አገልግሎት ላይ ከባድና አስቸጋሪ ክስተቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ አንዳንድ ሁኔታዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tuesday, May 4, 2010

እጅግ አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ

እጅግ አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ

በዳላስ የሚገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከድሮው ጀምሮ በልማት እድገቱ እዚህ እስኪደርስ ድረስ በጉልበታችሁ የደከማችሁና በገንዘባችሁ የተራዳችሁ፤
አሁን ግን በአምባ ገነኑ ቦርድ አባላት አይደላችሁም ተብላችሁ የተሠረዛችሁ የቤተ ክርስቲያኑ መሥራች አባላት በሙሉ

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋና የክርስትናውን መንገድ እየለቀቀ በመምጣቱ ምክንያት እንዲሁም የተረገጠውን የአባላት ክርስቲያናዊ መብት በሕግ ለማስከበር ፍርድ ቤት በመቆም ፍትህን እየጠበቃችሁ ያላችሁ ወገኖች በሙሉ

ክህነታችሁ እውነተኛውን አምላክ ክርስቶስንና ሕዝቡን የሚያገለግል እንጂ በውሸት፤በክህደትና በዛገ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የተበላሸ የቦርድን አሠራር የሚደግፍ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት በግፍና በሐዘን ከአገልግሎት የታገዳችሁና የተለያችሁ ክቡራን አባቶቻችን ካህናት በሙሉ

ስለ ቤተ መቅደሱና ስለ አባቶች ካህናት ክብር ስትሉ ሰብአዊነት የሌለው አምባገነኑ ቦርድ በቀጠራቸው ፖሊሶች በቤተ መቅደስ ውስጥ የተደበደባችሁና ያለጥፋታችሁ በእጅ ብረት በመታሠር የግፍን ጽዋን የቀመሳችሁ በሙሉhttp://www.youtube.com/watch?v=QTV8QUwlwFI

የተወሰኑ የቦርድ አባላእራሳቸውን በቡድን በማደራጀት የቤተክርስቲያኒቱን ገንዘብና ንብረትያላግባብ በማባከንና እንዲሁም በጥላቻና በበቀል ላይ ተመርኩዘው የሚሠሩትን ኢክርስቲያናዊ ሥራ በመቃወም እራሳችሁን ከቦርድ አባልነት ያገለላችሁና የቀድሞ የአስተዳደር ቦርድ አባላት የነበራችሁ በሙሉ፤

አረመኔው ቦርድ በሚፈጽመውና በመፈጸም ላይ በሚገኘው ግፍ ምክንያት ማታና ጧት በማዘን የምታለቅሱ የአጥቢያው ቤተክርስቲያን አማኞች አባቶችና እናቶች፤ወንድሞችና እህቶች በሙሉ

በአምባገነኑ አስተዳደና የአስተዳደሩን ክፉ ተግባር በተቃወሙ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት መካከል የተከሠተውን ግጭትና የክስ ሂደት በሰላም ፤ በእርቅና በይቅርታ እንዲፈታ ሌት ተቀን የደማችሁ የሠላም ልዑካንና የደብራችን ሽማግሌዎች በሙሉ፤

የደብሩን ሰላምና ፍቅር ወደ ቀድሞ ሥፍራው ለመመለስና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ዱብዳ ሆነው የወደቁትን ካባድ ችግሮች በጋራ ለማስወገድ እንዲቻል የፊታችን ቅዳሜ May 8 2010 ቀን 4.00 PM ላይ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተዘጋጅቷል ፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ቀደም ሲል የነበሩ ልዩነቶቻችን ወደ ጎን በመተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከጉልበተኞችና ከአንባገነኖች ለማዳን በሚደረገው በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘት ክርስቲያናዊ ግዴታችንን በጋራ እንድንወጣ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን፡፡

የሠላም አምላክ ስብሰባችንን ይባርክ !

የስብሰባው ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ

የስብሰባው ቦታ

Double Tree Hotel Dallas / Richardson
1981 North Central Expressway , Richardson
TX ,75080
972 808 5386

Wednesday, April 28, 2010

<ልጆቹዋን ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ሊለቀስላት ይገባል።›

የአስተዳደር ቦርድ መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ ካሰናበተበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ ባደረበት የፍርሃት መንፈስ ባልተለመደ ሁኔታና ከወትሮው በተለየ መልኩ በርካታ የፖሊስ ሠራዊትን ከሌሊቱ 3 ጀምሮ በቤተክርስቲያኒቱ ግቢ ውስጥ እንዲሠማሩ ማድረጉ ብዙውን አማኝ ክርስቲያን አሳዝኗል፡፡

Saturday, April 24, 2010

አምባ ገነኑ ቦርድ መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ አሰናበተ !

ትናንት ቅዳሜ ማምሻውን ለስብሰባ ይፈለጋሉ ተብለው በስልክ ተጠርተው ቦርድ ጽ/ቤት ተጠርተው የቀረቡት መልአከ ሣህል በሚያስተምሩት እውነተኛ የወንጌል ትምህርት ምክንያት እንደ ክርስቶስ በሐሰት ተወንጅለው አስተዳደርን በማያውቅ አምባገነን ቦርድ የስንብት ደብዳቤ ተነቦላቸው ሁለተኛ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ በሴት ፖሊስ ተገደው በመፈረም የስንብት ደብዳቤውን ተረክበው መውጣታቸውን ለማውቅ ተችሏል፡፡

Monday, April 19, 2010

የሂሳብ መርማሪና አጣሪ ኮሚቴ የሥራውን ውጤት አቀረበ !

ሰላም ተዋህዶ ቅዳሜ April 17 2010 በተደረገው ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ ያልተካፈለች ብትሆንም ስብሰባውን የተካፈሉ አንዳንድ ሰዎችን በማነጋገር ያገኘችውን ዘገባ በአጭሩ እንደሚከተለው ዘግባዋለች፡፡

Tuesday, April 13, 2010

ቦርድና ወታደራዊ መግለጫው !

የውብ እንጀራ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤
በሰሜን አሜሪካ የቴክሳስና አካባቢዋ የኢህአፓ አባላት ሰብሳቢ
የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ ዋና ጸሐፊ ወዘተ… አቶ አበበ ጤፉ ወታደራዊ መግጫ ሰጡ፡፡

Thursday, April 8, 2010

የአስተዳደር ቦርዱ ለአዲስ በቀል እየተዘጋጀ ነው፡፡

ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የትንሳኤ ዋዜማ በተአምረ ማርያም መቅድም ንባባ ምክንያት መምሬ ሞገስ ከቤተ መቅደሱ በኃይለኛ የቁጣ መንፈስ ተሞልተው በመውጣት‹ በሕግ አምላክ ፤ በሕግ አምላክ ፤ ሃይማኖት ነው … › እያሉ እንደ አበደ ሰው ደጋግመው በመጮኸቸው ምክንያት ሕዝበ ክርስቲያኑንና የበዓሉን ታዳሚዎች በሙሉ ማስደንገጣቸውና ማሳዘናቸው ይታወቃል፡፡ በአንጻሩም ደግሞ መልአከ ሣህል አወቀ ትዕግሥት በሞላበትና በተረጋጋ መንፈስ ያደረጉት የማረጋጊያ ንግግርና ሲመሩት የነበረው መንፈሳዊ የማሕሌት አገልግሎት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማማስመሰል ሊበላሽ የነበረውን በዓል በቦታው እንዲመለስ አድርገውታል፡፡

Thursday, February 25, 2010

ምሁራኑ ባልና ሚስት ተራቡ ! የቤተክርስቲያኒቱንም ካዝና ከበቡ !

 በኢኮኖሚክስ እንጀራ ያልተበላበት ዶክትሬት ያላቸው ዶክተር ግርማና በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ባለሙያ የነበሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ ዙሪያሽ በሙያቸው ከሚሠሩበት ካምፓኒ ከተባረሩ ከራርመዋል ፡፡ ዶክተሩም ባለባቸው በወዝ ሠርቶ የማግኘት ስንፍና ምክንያት የጀመሩትን የታክሲ ሥራ እንጀራዬ ብለው ጠንክረው መሥራት አልቻሉም፡፡ስለዚህ ችግር በቤታቸው ውስጥ ዘመድ ሆኖ መኖር ከጀመረም ሰነባብቷል፡፡ በዚህ የተነሣ የቅርብ የሆኑ ወዳጆቻቸው ገንዘብ በማዋጣት ቢደጉሟቸውም ዘለቄታዊ አይደለምና ኑሮ  እጅግ ከብዶባቸዋል፡፡  

Tuesday, February 16, 2010

‹ከዚህ የመጨረሻ ዕድል በኋላ ግን እጃችንን አጣምረን አንቀመጥም ! መረጃዎቻችንን ይዘን የ I.R.S ን በር እናኳኳለን ! ሕዝቡ ግን ያን ጊዜ ይህ ለምን ሆነ እንዳይለን !

ሰላም ተዋሕዶ በአስተዳደር ቦርድ ጤናማ ያልሆነ አሠራር ችግር ምክንያት የተናጋውን የቤተክርስቲያኗን ሰላም አስመልክቶ የችግሩን ምንጮችና ለዚህ አስተዋጽዖ ያበረከቱትን ግለሰቦች በግልጽ ከመተቸት ጀምሮ ምእመናኑ እንዲገነዘቡትና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ምን እየተደረገ እንደሆን ከውስጥ የምታገኘውን መረጃ መሠረት በማድረግ ስታሳውቅ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ በመሄዱና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሠጠውም ገንዘብ ያለይሉኝታ እየተዘረፈና ምሥጢሩም አደባባይ እየወጣ በመውጣቱ ድርጊቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪዎች ነን የሚሉትን ሁሉ አበሳጭቷል ፡፡ አስቆጭቷል፡፡

Monday, February 1, 2010

የሂሳብ ሹሙ በገንዘብ ወንበር ላይ መቀመጥ ምስጢሩ ምንድን ነው ?

ሂሳብ ሹሙ ሊቀመንበር ለመሆን ያደረጉትን የትግል መሥመር ቀይረው በቦታቸው ላይ ለመቆየት መወሳነቸው ሁለት ነገሮችን ያመላክታል፡፡

1.ቦታውን ለማገኘት ያደርጉ የነበረው ትግል በአደባባይ ተደጋግሞ በመነገሩና ምሥጢሩ በብሎግም ላይ በመውጣቱ የዚህን እውነታ መንገድ ለማስቀየርና የተባለው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ተብሎ እንዲነገር ለማድረግ ነው፡፡( ይህ አይነቱ ዘዴ ደግሞ ከፖለቲካዊ ጫወታዎች አንዱ ነው፡፡)

2.እርሳቸው የተማሩና የከተማ ልጅ (አራዳ) በመሆናቸው በዋና ዋናዎቹ የሥልጣን ቦታዎች ላይ የገጠር ሰዎችንና ያልተማሩ ሰዎችን በማስቀመጥ ቦርዱን ባሉበት ቦታ ላይ ሆነው እንደፈለጉ ለማሽከርከርና የገንዘብ ጥማታቸውን በዘዴ ለማርካት ነው፡፡

Saturday, January 30, 2010

በአስተዳደር ቦርድ አባላት መካከል የነበረው ጠብ ለሕዝብ ይፋ ሆነ !

ለብዙ ወራት በቦርዱ ቢሮ ታምቆ የኖረው የአስተዳደር ቦርድ አባላት ጠብ ፈንድቶ ዛሬ በሕዝብ ስብሰባ መሃል ተገለጠ፡፡ የሂሳብ ሹሙና የሊቀመንበሩ ቡድን ተብሎ ለሁለት የተሠነጠቀውና ቤተክርስቲያኒቱን ከልማት ይልቅ ወደ ውድቀት እየሳባት ያለው ቦርድ በማስተዳደር ብቃቱ ደካማነት በሕዝብ ሲተች መክረሙ ይታወሳል፡፡

Monday, January 25, 2010

ምርጫውን ለማስቆም ጀንበር ጠልቃለች ወይስ ገና ነች

የዕጩ አስተዳደር ቦርድ አባላት ምርጫ ውጤቱ እንደ ተሰማና የዶክተር ግርማ ደጋፊዎች ማሸነፋቸው እንደታወቀ በእነ አቶ ኢዩኤልና በደጋፊዎቻቸው የቦርድ አባላት መካከል ከፍተኛ መደናገጥና አለመረጋጋትን እንደፈጠረ በቅርብ የነበሩ እማኞች ገለጡ፡

Sunday, January 24, 2010

የአስተዳደር ቦርድ ምርጫው ውጤቱ ይፋ ባይሆንም ታወቀ !

ሰሞኑን በአቶ ኢዩኤል ነጋና በዶክተር ግርማ ደጋፊዎች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው የምርጫ ውድድርና ፉክክር በዶክተር ግርማ ቲፎዞዎች አሸናፊነት መጠናቀቁን ከአስመራጭ ኮሚቴ አባላት የሾለከው ዜና ያስረዳል፡፡

Thursday, January 14, 2010

የቦርድ ጠበቃ ማሳሰቢያ !

የክስ መጓተትና የይግባኝ ክስ መቀጠል የጠበቆች ፍላጎትና እንጀራቸውም እንደሆነ ይታወቃል፡፡በዚህ መሠረት የዳኛው ያልተጠበቀ ፍርድና ውሳኔ ትክክል ባለመሆኑ እኔንም በጣም አናዶኛል የሚለው የከሳሾች ጠበቃ ውሳኔው የኔንም ሪከርድ የሚያበላሽ ስለሆነ በራሴው ኪሣራ የይግባኝ ክሱን እቀጥላለሁ ብሎ ጉዳዩን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ በማለት ማቅረቡን ሰሞኑን መሰማቱ ይታወቃል፡፡

Sunday, January 10, 2010

የይግባኝ ክሱ የአስተዳደር ቦርዱን አስቆጣ !

ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በዋለው ችሎት ሌሎች የክስ ዝርዝሮችን ሳያዩ ዳኛው የሰጡት ብይን ያለግባብባና ፍትህነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹት ከሳሾች ሶስት ዳኞች በሚሰየሙበት ከፍተኛ ችሎት ላይ ጉዳያቸው እንደገና እንዲታይላቸው ይግባኝ ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡