ለብዙ ወራት በቦርዱ ቢሮ ታምቆ የኖረው የአስተዳደር ቦርድ አባላት ጠብ ፈንድቶ ዛሬ በሕዝብ ስብሰባ መሃል ተገለጠ፡፡ የሂሳብ ሹሙና የሊቀመንበሩ ቡድን ተብሎ ለሁለት የተሠነጠቀውና ቤተክርስቲያኒቱን ከልማት ይልቅ ወደ ውድቀት እየሳባት ያለው ቦርድ በማስተዳደር ብቃቱ ደካማነት በሕዝብ ሲተች መክረሙ ይታወሳል፡፡
ለጀነዋሪ 23 2010 ተጠርቶ የነበርው የሕዝብ ስብሰባ አጀንዳ ከሳሾችና ደጋፊዎቻቸው ጨርሶውኑ ቤተ ክርስቲያን እንዳይደርሱ ለማገድና ይህንንም ለሕዝቡ አቅርቦ ለማስወሰን የታቀደ ቢሆንም በቦርድ አባላቱ በሃሳብ አንደ አለመሆንና ጠብ ምክንያት ስብሰባው ለዛሬ ጃኑአሪ 30 2010 መዛወሩም ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ሊቀመንበሩ ፤ ጸሐፊውና ተቆጣጣሪዋ ሂሳብ ሹሙንና ገንዘብ ያዡን በሂሳብ አያያዝ ዝርክርክነትና በገንዘብ ቅሌት ሲወነጅሏቸው አምሽተዋል፡፡ ሂሳብ ሹምና ገንዘብ ያዡም ይህንኑ በጽኑ ለመከላከልና ሕዝቡን ስለሂሳቡ ትክክለኛነት ለማሳመን ሲጥሩ ታይተዋል፡፡
የስብሰባውን መንፈስ በገንዘብ ቅሌት አጀንዳ ሰበብ ለውጠው ምርጫውን ለማጨናገፍና አሸናፋቹ የሂሳብ ሹም ደጋፊዎች እንዳይገቡ ለማሰናከል ሊቀ መንበሩ የተጠቀሙበት ታክቲክ ሳይሠራ መቅረቱን ለማየት ተቸሏል፡፡ ይህ ደግሞ ሊቀመንበሩና ደጋፊዎቻቸውን ከፍተኛ ውርደትና ጭንቀት ውስጥ እንደጣላቸው የሚያሳይ ነው፡፡
አዲሶቹ ተመራጮ አቶ አበበ ጤፉ አቶ ሙሉዓለም እርጥቡና ወ/ሮ ሶሎሜም ከነገው እሁድ ባልራቀ ጊዜ በትረ ቦርድ ስልጣናቸውን ተረክበው የቤተክርስቲያኒቱን ውድቀት በከፍተኛ ደረጃ የሚያጣድፈውን እኩይ ሥራቸውን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት