ሰሞኑን በአቶ ኢዩኤል ነጋና በዶክተር ግርማ ደጋፊዎች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው የምርጫ ውድድርና ፉክክር በዶክተር ግርማ ቲፎዞዎች አሸናፊነት መጠናቀቁን ከአስመራጭ ኮሚቴ አባላት የሾለከው ዜና ያስረዳል፡፡
በዚህ ውድድር ወ/ሮ ሰሎሜ ፤ አቶ አበበ ጤፉና አቶ ሙሉ ዓለም አብላጫ ድምጥ በማግኘት ለቀጣዩ ሶስት ዓመታት የቦርድ አባልነት የተመረጡ ሲሆን ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ፤አቶ ተፈራ ወርቅና አቶ አምሃ ደግሞ አነስተኛ ድምጽ በማምጣት ሳይመረጡ መቅረታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዶክተር ግርማ በዚህ የቦርድ አስተዳደር ውስጥ እርሳቸውን ሳይጨምር አምስት ደጋፊ አባላት ያላቸው ሲሆን በአዲሱ የስልጣን ድልድል ወቅት የሊቀመንበርነቱን ቦታ በድምጽ ብልጫ ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህም ለ20 ዓመታት ያህል በሊቀ መንበርነት ቦታ ይመሩ የነበሩትንና ‹ቤተ ክርስቲያኑ የእኛ ነው› እያሉ በእኔነት ስሜት ይመኩ በነበሩት በአቶ ኢዩኤል ነጋ ላይ ከፍተኛ ሃዘንና የሞራል ውድቀትን ሊያስከትል እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ይህ የዘንድሮው አመት የአስተዳደር ምርጫ በ21 አመት የቤተክርስቲያኒቱ ጉዞ ውስጥ አጅግ አደገኛና ለወደፊት የቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና አስጊ እንደሆነም ቀደምትነት ያላቸው መሥራች አባላት ይናገራሉ፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት