Sunday, January 10, 2010

የይግባኝ ክሱ የአስተዳደር ቦርዱን አስቆጣ !

ባለፈው ታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ በዋለው ችሎት ሌሎች የክስ ዝርዝሮችን ሳያዩ ዳኛው የሰጡት ብይን ያለግባብባና ፍትህነት የጎደለው መሆኑን የሚገልጹት ከሳሾች ሶስት ዳኞች በሚሰየሙበት ከፍተኛ ችሎት ላይ ጉዳያቸው እንደገና እንዲታይላቸው ይግባኝ ማለታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህም ጉዳይ የአስተዳደር ቦርዱን በከፍተኛ ሁኔታ አስቆጥቷል፡፡ባለፈው ዓርብ ምሽት በዚሁ አጀንዳ ላይ በከፍተኛ ንዴትና ቁጣ ሲመክር ያመሸው የአስተዳደር ቦርድ ሁለቱ ከሳሾችና አጋሮቻቸው ጨርሶውኑ ከቤተክርቲያን ቅጥር ግቢ እንዳይደርሱ በሚያደርግ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ሲነጋገር ማምሸቱ ታውቋል፡፡

በአስተዳደር ቦርዱ ተሸሽሎ በወጣው አዲሱ ባይሎው መሠረት ቤተክርስቲያንን የከሰሰ አባል ከቤተክርስቲያን እንደሚባረር ያትታል፡፡ በዚሁ መሠርት ከሳሾቹ ቤተክርስቲያንን በመክሰሳቸው ምክንያት ከማስቀደስ በስተቀር ምንም ዓይነት የአባልነት መብት እንዳይኖራቸው ተደርጎ ከአባልነት መሠረዛቸውም ይታወቃል ፡፡ አሁንም ክቡር ፍርድ ቤቱን በይግባኝ በመጠየቃቸው ምክንያት እስከመጨረሻው ከቤተ ክርስቲያን እንዲባረሩና እንዳይገቡም በፖሊስ እንዲታገዱ የውሳኔ ሃሳብ የረቀቀ ሲሆን ይህም አስቸኳይ የአባላት ስብሰባ ለ January 23 2010 ተጠርቶ እርምጃው ተግባራዊ እንዲሆንና በአባላቱ እንዲጸድቅ መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዛሬ January 10 2010 የአስተዳደር ቦርዱ ሰብሳቢ ቁጣና ቁጭት በተመላበት መግለጫቸው ስለ ይግባኙ ክስ ጉዳይ አስቸኩዋይ የአባላት ስብሰባ ለ January 23 2010 መጠራቱን አብሥረዋል፡፡ እግረ መንገዳቸውንም የአባልነት መዋጮዋቸውን ያልከፈሉ አባላት በዚሁ ስብሰባ መገኘት እንደማይችሉም ገልጸዋል፡፡የመግለጫውም ማእከላዊ መልእክት ከቦርዱ ወዳጆችና ደጋፊዎች በስተቀር ሌላው ወገን በስብሰባው ላይ እንዳይገኝ የሚገፋና የሚያበሳጭ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌላም በኩል ዘመናቸውን በጨረሱት ሦስት የበርድ አባላት ምትክ 6 አባላት በእጩነት መጠቆማቸው በአስመራጭ ኮሚቴው ሊቀመንበር ተግልጧል፡፡ እነዚህም

1.አቶ ተፈራ ወርቅ
2.አቶ አምሃ
3.ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ
4.ወ/ሮ ሶሎሜ
5.አቶ አበበ ጤፉ
6.አቶ ሙሉ ዓለም እርጥቡ ናቸው፡፡

እነዚህም እጩዎች ከተራ ቁጥር 1 - 3 ያሉት የሊቀ መንበርነቴን ወምበር እስክሞት ድረስ አለቅም ብለው የሞት የሽረት ትግል የሚያደርጉት የሊቀመንበሩ ደጋፊዎች ሲሆኑ ከተራ ቁጥር 4- 6 ያሉት ደግሞ የሊቀ መንበርነት ሥልጣኑን ቀን ከሌሊት የሚቋምጡት የሂሳብ ሹሙ ደጋፊዎች ናቸው፡፡ ይህ በሁለቱ የሥልጣን ጥመኞች መሃል ያለው ትግል በምርጫውና በቦርዱ ዙሪያ ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሯል፡፡ በእጩዎች ሊስት ውስጥ ለመግባትና በሥልጣናቸው ወንበር ላይ ለመቆየት በየ ቤቱ የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የሰነበቱት የቦርዱ ጸሐፊ ግን ከውድድሩ ያለውጤት በዜሮ መሸነፋቸውም ይፋ ሆኗል ፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት