ሂሳብ ሹሙ ሊቀመንበር ለመሆን ያደረጉትን የትግል መሥመር ቀይረው በቦታቸው ላይ ለመቆየት መወሳነቸው ሁለት ነገሮችን ያመላክታል፡፡
1.ቦታውን ለማገኘት ያደርጉ የነበረው ትግል በአደባባይ ተደጋግሞ በመነገሩና ምሥጢሩ በብሎግም ላይ በመውጣቱ የዚህን እውነታ መንገድ ለማስቀየርና የተባለው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ተብሎ እንዲነገር ለማድረግ ነው፡፡( ይህ አይነቱ ዘዴ ደግሞ ከፖለቲካዊ ጫወታዎች አንዱ ነው፡፡)
2.እርሳቸው የተማሩና የከተማ ልጅ (አራዳ) በመሆናቸው በዋና ዋናዎቹ የሥልጣን ቦታዎች ላይ የገጠር ሰዎችንና ያልተማሩ ሰዎችን በማስቀመጥ ቦርዱን ባሉበት ቦታ ላይ ሆነው እንደፈለጉ ለማሽከርከርና የገንዘብ ጥማታቸውን በዘዴ ለማርካት ነው፡፡
(ይህም ሌለኛው የፖለቲካ ቁማርተኞች ብልሃት ነው)፡፡ ለዚሁ እዲመች ማንበብና መጻፍ እንኩዋን የማይሆንላቸውን አቶ ዮሴፍን ሊቀመንበር አቶ ሙሉዓለምን ምክትል አቶ አበበን ጸሐፊ አድርገዋል ፡፡ በፖለቲካው አለም ‹የተባበሩት መንግስታት ጸሐፊ › መባል ለስም ያህል ትልቅ ነው፡፡ ሥልጣኑና አመራሩ ግን በእጅ አዙር ያለው በአሜሪካን መንግስት እጅ ነው፡፡ ለሊቀ መንበሩ ለአቶ ዮሴፍና ለሌሎቹም የተረፈው ስም ብቻ ነው፡፡ ‹ የአሸንጉሊት ንጉሥ› እንደማለት ነው፡፡ ምሳሌ-የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት፡፡
ሂሳብ ሹሙ የኢኮኖሚ ዶክትሬት ያላቸው ናቸው ተብሏል፡፡ ግን የግል ሕይወት ታሪካቸው እንደሚያስረዳው ከገንዘብ አበዳሪ ድርጅቶች ብዙ ገንዘብ ተበድረው አልከፍልም በማለት BANKRUPSY DECLARE አድረገዋል፡፡በዚህ ምክንያት በ Background Check እና በ Bad Credit History በሙያቸው ሥራ ይዘው መሥራት አልቻሉም፡፡ ስለዚህ በታክሲ ሥራ መሠማራት ግድ ሆነባቸው፡፡ ሥራ ክቡር ነው ፡፡በዚህም ሥራ ተሠማርተው ሲሰሩ የታክሲ ሠራተኞችን መብት ለማስጠበቅ ባደረጉት ጥረት በማኅበሩ አባላት ዘንድ ክብርንና ለጊዜው መወደድን አትርፎላቸው ነበር፡፡ በዚህም የማኅበሩ ሰብሳቢ እስከመሆን ደርሰዋል፡፡ ግን ብዙም ሳይቆዩ የከተማ ልጅነታው ጠባይ በገንዘብ ላይ ባመጣባቸው ችግር በማኅበሩ አባላት ተቃውሞ ከሰብሳቢነት ተወግደዋል፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት