በኢኮኖሚክስ እንጀራ ያልተበላበት ዶክትሬት ያላቸው ዶክተር ግርማና በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ባለሙያ የነበሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ ዙሪያሽ በሙያቸው ከሚሠሩበት ካምፓኒ ከተባረሩ ከራርመዋል ፡፡ ዶክተሩም ባለባቸው በወዝ ሠርቶ የማግኘት ስንፍና ምክንያት የጀመሩትን የታክሲ ሥራ እንጀራዬ ብለው ጠንክረው መሥራት አልቻሉም፡፡ስለዚህ ችግር በቤታቸው ውስጥ ዘመድ ሆኖ መኖር ከጀመረም ሰነባብቷል፡፡ በዚህ የተነሣ የቅርብ የሆኑ ወዳጆቻቸው ገንዘብ በማዋጣት ቢደጉሟቸውም ዘለቄታዊ አይደለምና ኑሮ እጅግ ከብዶባቸዋል፡፡
ደካማ ጎናቸውን በማየት ያላሳለሰ የእንጀራ ድጎማ የምታደርግላቸው የእንጀራ ቤቷ ወ/ሮ ቡክሪም እንደ ነቀርሣ በሽታ የተጠናወታትን የአባ ወልደ ትንሣኤን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የማስመጣት አጀንዳ ሥራቸው አድርጋ ከእንጀራው ጋር ሰታቸዋለች፡፡ ውሻ በበላበት ይጮሃል እንዲሉ ስለሳቸው መምጣት እንደሞኝ ለቅሶ ማታና ጠዋት በመደጋገም አጀንዳ እያደረጉ የሚያነሱትም እኒሁ ባልና ሚስት ናቸው፡፡
ታዲያ እነዚህ ባልና ሚስት ወደዚህ ቤተክርስቲያን የመጡት ለአገልግሎት ነው ወይስ ለዘረፋ ? ይሄ የሁላችንም ጥያቄ ይሁን፡፡ በቅርብ ዶክተሩና ገንዘብ ያዡ በቅንጅት በቤተ ክርስቲያኑ ገንዘብ ላይ ይጫወቱ የነበረውን ቁማርና ዘረፋ የሂሳቡ ሪፖርት ይፋ እንዳደረገው ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደም ደግሞ የዶክተሩ ባለቤት ወ/ሮ ዙሪያሽ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ስለወደኩ መታከሚያ ካሣ ገንዘብ ይሠጠኝ ብለው ቤተ ክርስቲያኑን $ 800 ሲያስከፍሉ ብዙ ሰው ባይሰማውም የሰማ ሁሉ ግን አጉረምርሞ ነበር፡፡ ምስጢሩ ግን መታከሚያ ገንዘብ ወይም ኢሹራንስ ስለሌላቸውና ችግር ላይ ስለነበሩ ነው፡፡ ያ ይሁን ግድ የለም ! ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የፈሰሰ ደሜን ቤተ ክርስቲያን በገንዘቧ ትግዛው ስላሉ ጉዳዩ በዛ መልኩ አልፏል፡፡ ቁም ነገሩ ግን እንዲህ የተራበንና የተቸገረን ቤተሰብ በቤተክርስቲያኗ ገንዘብ ላይ አለቃ አድርጎ ማስቀመጥና ገንዘቡን ማዘረፍ ተገቢ ነው ወይ የሚለው ነው ፡፡
ወገን ሲቸገር መርዳት ተገቢ ነው ፡፡ ግን እነዚህ ሰዎች ስለተቸገሩ ዶክተርም በሂሳብ ሹምነታቸው እያምታቱና ገንዘብ እየዘረፉ ይኑሩ ብለን ዝም ማለት ግን ተገቢ አይመስለንም ፡፡ ለምን ? ገንዘቡ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነውና፡፡ እነርሱ ግን ለወደፊት ገንዘብ እያገኙ የሚኖሩበትን አዲስ ዘዴ ቀድመው አመቻችተዋል፡፡ በተለይ ዶክተሩ ለዘረፋ የሚመቻቸው ትክክለኛ ቦታ ላይ እንደተቀመጡ በቅርብ የሚያውቋቸወ ሁሉ ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ሕዘበ ክርስቲያኑ ግን አሁን በትክክል መንቃት ያለበት ይመስለናል፡፡
አዲሱ ቦርድ የቤተ ክርስቲያኑዋን ሰላምና የሕዝቡን መረጋጋት ለማምጣት በመጀመሪያ ይህንን ለማድረግ አቅደናል ከማለት ይልቅ ቤተ ክርስቲያኒቱን በልማት ለማሳደግ እንዲህ እንዲህ … እናደርጋለን በማለት ገና በአንድ ሳምንቱ ገንዘቡ በስፋት የሚዘረፍበትን በር ወለል አድረጎ ለመክፈት መነሣቱ የቦርዱ አላማ ለልማት ሳይሆን ለላቀ ዘረፋ መዘጋጀቱን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡
ለምሳሌ ለዘረፋ እንዲመቻቸው ብለው ዶክተሩ የቤተክርስቲያኑን የኮምፒውተር ኔት ዎርክ ሲስተምን በሙሉ በጣጥሰውታል፡፡ ሌሎችም ገብተው እንዳያዩ ኮዱን በመቀያየር እርሳቸው ብቻ በገንዘቡ ላይ ዋና አዛዥ እንዲሆኑ አድርገው አዲስ ሲስተም አስቀምጠዋል፡፡ እንደገና በአዲስ መልክ ሊዘርፉ ላቀዱት አዲሱ የሌብነት ሥራቸው አመቺ እንዲሆን ደግሞ ሚስታቸው ወ/ሮ ዙሪያሽን በቤተ ክርስቲያኑ ድኅረ ገጽ ሥራና በአዲሱ የኮምፒውተር ኔት ወርክ መዘርጋት ሥራ ሰበብ ለዚህ ተግባር ዋና ተጠሪና ኃላፊ አድርገው አስቀምጠዋል፡፡ ወይዘሮ ሰሎሜን እንጃ እንጂ ሌሎች የቦርድ አባላት ቀደም ሲል እንደተነገረው ከኮምፒውተሩ ጋር ዝምድና የሌላቸው ባዕዳን ስለሆኑ መመሪያ ተቀባዮች እንጂ አዕምሮአቸውን ተጠቅመው የሚሠሩ አይደሉምና የበዪ ተመልካቾች ናቸው ፡፡
ለማንኛውም ሕዝበ ክርስቲያኑ እኒህ ባልና ሚስት ተርበውና ገንዘብ ፈልገው ለዘረፋ የመጡ መሆናቸውን በሚገባ ተገንዝቦ በኢትዮጵያዊነቱና በወገንነቱ
1.ኛ ሥራ ፈልጎ እንዲያስገባቸው
2.ኛ ሳይቀሰፉና በሕዝብ ፊት ሳይዋረዱ ከዚህ ቦታ ቀስ ብሎ አንስቶ አስቀድሠውና ተምረው ብቻ የሚሄዱ ምእመናን አድርጎ እንዲያስቀምጣቸው ይህን እንደመፍትሄ እንጠቁማለን፡፡
ይህ ሁሉ ችግር የመጣውና ሰላምም በቤተ ክርስቲያናችን የጠፋው እነዚህ ሰዎች ከመጡ ጀምሮ እንደሆነ ከማንም አዕምሮ የማይሠወር ሃቅ ነው ፡፡ የቅዳሜው የተቆርቋሪ አባላት ሰብሳበባም ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት ስለ ቤተክርስቲያኑዋ የወደፊት ሕልውና የጠነከረ አቋም እንደሚወስድ እንገምታለን፡፡
አንዲትም ነፍስ በሰው ስራ ባትሰናከል፤ ከቤተ-እግዚአብሔርም ባትርቅ…..
ReplyDeleteፈጣሪአችን እግዚአብሔርም ይበልጥ እንዳያዝን ቢሆን፤…
…ብሎም፣ ከዚህ ‘አንዴ ተመርጫለው’ ከሚል ፖለቲካዊ መንፈስና አሰራር ማንም ቢላቀቅ /በተለይ በእግዚአብሔር ቤት/ ምንኛ መልካም በሆነ! በማንስ ቤት ማንን እያገለገልን ነውና?
ግድ የለም በእግዚአብሔር ቤት ‘ተሸነፉ’!