በዚህ ዓለም የምናየው ከፍተኛውና አስገራሚው የቴክኖሎጂ ውጤት ሁሉ የእግዚአብሔር ፈቃድና ስጦታ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ሲፈጥረው በመልካም ሁኔታና በምቾት እርሱን እያመሰገነው እንዲኖር ነበር፡፡ ለዚህም አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ቀድመው ለሰው ልጅ የምቾት ኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ መፈጠራቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ሰው እንዳይራብና እንዳይጠማ አስቀድሞ ምግብንና መጠጥን እግዚአብሔር ፈጥሮ አዘጋጀለት፡፡ እንዲሁም የሰው ልጅ በተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻቹለት፡፡ይህም እግዚአብሔር ሰውን ደስ እያለው እንዲሮር መፍጠሩን ያስገነዝበናል፡፡ ነገር ግን ስው ከተፈቀደለት የኑሮ አጥር ዘሎ ባልተፈቀደለት የሕግ ማፍረስ ኑሮ ውስጥ ሲገባ ፤ ሁኔታዎች ሁሉ ተለዋውጠው ተገላቢጦሽ ሆኑበት ፡፡ በፈጸመው ስህተት የሰው ልጅ ተፈጥሮን በራሱ ጥረትና ወዝ እየታገለና እያቀና እንዲኖር በፈጣሪ ተወሰነበት ፡፡
እግዚአብሔርም በየዘመኑ ለተነሣው ትውልድ ሁሉ በየደረጃው እውቀትንና ጥበብን እየሰጠ አኖረው፡፡አሁንም እያኖረው ነው፡፡ይህች ዓለም አረፍተ ዘመን እስኪገታትና ዕድሜዋ እስኪያልቅ ድረስ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ያልተደረሰበትን ጥበብና ምስጢር ሁሉ ለሰው እየገለጠና በጥበብ እያራቀቀ ወደፊትም ያኖረዋል፡፡ ስለዚህ ይህ በዓለም የምናየው የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤት ሁሉ የእግዚአብሔር ስጦታና በእርሱ ፈቃድ የሚገለጥ እንጂ የሰው ልጅ ብቸኛ የአዕምሮ ውጤት አለመሆኑን በሚገባ ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል፡፡
የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓለማ ቴክኖሎጂው በእለት ተእለት የሥራ፤የግልና ማኅበራዊ ኑሮአችን ውስጥ የሚጫወተውን ዐቢይ ሚና ለማሳየትና ተገቢ የሆነ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ነው ፡፡
ዘመኑ የመረጃ ዘመን በመሆኑ ለሌላ አገልግሎት የሚፈበረኩ አንዳንድ የፋብሪካ ውጤቶች በዋናነት ከሚያበረክቱት መደበኛ አገልግሎታቸው በተጨማሪ ዋና መረጃ ሰብሳቢ መሣሪያ በመሆን እንዲያገለግሉ እየተደረገ ነው፡፡በዚህም የምናየውን እቃ ሁሉ እንድንጠራጠርና እንድንጠነቀቅ እያደረገን ነው፡፡
ከላይ በርእሱና በምስሉ እንደምንመለከተው ሰላዩ ብእር (Spy Pen) በሰው ግምትና ሀሳብ የቀድሞ አገልግሎቱ በሰው እጅ ጣቶች ተጨብጦ ሹል በሆነ ጫፉ ቀለም እየተፋ መጻፍ ነበረ ፡፡ ዛሬ ግን ቴክኖሎጂው በሰጠው ጥበብና አዲስ ሥራ ከደረት የሱፍ ኮት ኪስ ውስጥ ብእር መስሎ በመንጠልጠል በአናቱ ጫፍ ላይ ያለውን በተን ሲጫኑት በፊት ለፊቱ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ምስልና ድምጽ አቀናብሮና ጥርት አድርጎ በመቅሰጽ ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ሰላዩ ብዕር እንደተመሠረተ በመንግስት ደረጃ ፖሊሶችና የደኅንነት ሠራተኞች በከፈተኛ ሁኔታ በመረጃ መሰብሰቢያነት የተጠቀሙበት ሲሆን ዛሬም ቢሆን ባላደጉ ሃገሮች መንግስታት ዘንድ ከፍተኛ የሥራ ድርሻ ይዞ ይገኛል፡፡
ይህ እንደ እስፒል ጫፍ ቀዳዳ ያለው ሰላዩ ብዕር 4GB vesion and Memory ወይም ለአንድጊዜ በተሞላ ባትሪ ለ30 ሰዓታት ያክል የመቅረጽ አቅምና ጥራት ያለው ከፍተኛ መሣሪያ ነው፡፡ ሴልፎንን ጨምሮ እስካሁን በልዩ ልዩ መልክ የቪዲዮ መቅረጫ መሣሪያ የተገጠመላቸው ብዙ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ቢኖሩም በአለም የመጀመሪያ ትንሹ ምስልና ድምጽ መቅረጫ መሣሪያ ሰላዩ ብዕር ሲሆን በምስሉም ጥራት ከሌሎችም ከሜራዎች የማያንስ መሆኑ ተረግግጧል፡፡ያለኤሌክትሪክ ገመድ የተቀረጸውን ምስል ለማየት የሚያስችል የራሱ የሆነ mini DVR Screen አለው፡፡ በተጨማሪም የቀረጸውን ምስል ለማየት በቀጥታ ከኮምቲውተር ጋር በማገናኘት መረጃውን በዋና ኮምፒውተር ማስተላለፍና መመልከት የሚቻል ሲሆን Windows 98ን ጨምሮ ከዚያ በላይ ባሉ ዓመታት በተመረቱ የኮምፒውተር መሣሪያዎች ሁሉ መጠቀም ይቻላል፡፡
ቀደም ሲል ከላይ እንደተገለጸው ሰላዩ ብዕር በሰው ልጆች በግልና በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ የመግባት ዕዱሉ እጅግ ሰፊ በመሆኑ ከዚህ አንጻር በአንድ ባልና ሚስት የትዳር ሕይወት ውስጥ የተጫወተውን ሚና በቀጣዩ ጽሑፋችን የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት