ዓለም በቴክኖሎጂው ስልጣኔ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሳለች ፡፡ብዙም ነገር ከሰው አእምሮና ጉልበት አሠራር ወደ ኮምፒውተር ሥራ እየተቀየረ ነው፡፡ ሥራ ፈትነትን ከማስፋፋት አንጻር ደግሞ ይህ ሁኔታ በሰው ልጅ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እራሱን የቻለ ችግር ቢኖረውም ሥራን ከማቀላጠፍና በጥራት ከመሥራት አንጻር ደግሞ ኮምፒውተር የሚሠጠው ጥቅም ቀላል ግምት የሚሠጠው አይደለም ፡፡ይሁን እንጂ ይህንኑ መልካም ሥራውን ለማደናቀፍ የኮምፒውተርን ውስጣዊ አካል እንደ ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ጠንቅቀው የሚያውቁ ባለሙያዎች በኢንተርኔቱ መረብ በኮምፒውተር ውስጣዊ የመረጃ ክፍል ላይ የኤሌክትሪ መርዝ በመልቀቅ የኮምፒውተሩን መዝገብ ቤት ፋሎች በመደመስስ ከፍተኛ ጉዳትና ኪሣራን በኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ላይ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡
ይህ ዓይነቱ ጥፋት ተጭኖ የሚመጣው በምናውቃቸውና በኢሜል ፋይሎቻችን ውስጥ ባሉ ሰዎች ስም ወይም በተለምዶ አጠራር በጃንክ ሜይሎች በኩል ሲሆን በርእሳቸው መልካም መልዕክት የያዙ በሚመስሉ መርዝ ረጪ ፋይሎች አማካኝነት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታና ዓይነት ብዙዎች ባለማወቅ ብዙ ቁምነገሮችን ያስቀመጡባቸውን የኮምፒውተር ፋይሎች ከጥቅም ውጭ ሆነው አግኝተዋቸዋል፡፡
ሰሞኑንም 'Life is Beautiful ' በሚል ርእስ በፖወር ፖይንት ሾው ተዘጋጅቶ የተለቀቀ አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ስላላ መንኛውም የኮምፒውትር ተጠቃሚ ሰው ሁሉ ይህንን ወዲያውኑ እንዳየ ከመክፈቱ በፊት < Delete > በማድረግ ቫይረሱን መግደል ይኖርበታል፡፡ ይህን ባለማድረግ ይህን ቫይረስ የያዘውን ፋይል ለመክፈት ከተሞከረ ግን መጀመሪያ በኮምፒውቱሩ ስክሪን ላይ 'it is too late now; your life is no longer beautiful... .' የሚል አስደንጋጭና ተሥፋ አስቆራጭ የእግሊዘኛ ጽሑፍ ይታያል፡፡ ወዲያውኑ በኮምፒውተሩ ውስጥ ያሉት ፋይሎች በሙሉ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ቫይረሱን የላከው ሰው ካለበት ቦታ ሆኖ ቫይሱ ያጠቃውን ኮምፒውተር ባለቤት < User name እና password > በራሱ ኮምፒውተር ላይ በቀላሉ ለማየት ይቻለዋል፡፡ የኮምፒውተሩ ባለቤት ኮምፒውተሩን ከማጣት ኪሣራ ባሻገር ዩዘር ኔምና ፓስዎርዱን ይዘረፋል፡፡ በዚህ ምክንያት ሰውየው ሳያውቀው በስሙና በኢሜሉ ብዙ ወንጀል ሊፈጸም ይችላልና'Life is Beautiful በሚል ርዕስ የሚመጣውን የፖውር ፖይን ሾው በምንም ዓይነት እንዳትከፍቱት በማለት በኮምፒተሮች ላይ ዘብ ሆኖ የቆመው የ Microsoft እና Norton.ዘ ካምፓኒ በጥብቅ እያሳሰበ ቫይረሱን ለመከላከል ከአቅሙ በላይ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
ግርማ ሞገስ እባላለሁ ነዋሪነቴ ኦሰትን ቴክሳስ ነው፡፡የብሎጋችሁ ደንበኛ ነኝ፡፡ ይህቺን ጽሑፍ ሳነብ ባለማወቅ ምክንያት አዲስ ኮምፒውትሬን ያጣሁበትን የዛሬ አራት አመቱን ታሪኬን አስታወሰችኝ፡፡ አዲስ ኮምፒውተር በገዘሁ ከሰባት ወር በኋላ አንድ በሟቹ ማይክል ጃክሰን የዘፍን ስም ተዘጋጀ የቫይረስ ፋይል ባለማውቅ ከፍቼ አዲሱ ከምፒውተሬ ከጥቅም ውጭ ሆነ ፡፡ይህ ጽሑፍ እንደኔ ያሉ ብዙ ሰዎች ባለማውቅ ምክንያት ኮምፒውተራቸውን እናዳያጡ ይጠቅማልና መልካም ነው ቀጥሉበት እላለሁ ፡፡
ReplyDelete