Monday, May 17, 2010

ሠበር ዜና

ሚያዚያ 24 2002 ( May 2 2010 ) በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ቁጥራቸው ከ20 በላይ የሚሆኑ ወንጀለኛን በውሻ የሚፈልጉና ቦንብ ፈታሽ የሆኑ ልዩ የፖሊስ ሠራዊትን ቀጥሮ በቤተ መቅደስ ውስጥ የፈጸመውን ግፍና ድብደባ በተመለከተ በዩቱብ ለአለም የተሠራጨው የቪዲዮ ፊልም የሜዲያን ትኩረትን ስለሳበ ዛሬ ሰኞ May 17 2010 ከምሽቱ 9.00pm ላይ በቻናል 4 ላይ በቴሌ ቪዥን ይተላለፋል፡፡

የዲሞክራሲ ምንጭና ሀገር በሆነች አሜሪካን ሀገር እንዲህ አይነቱ ኢ-ዲሞክራሲያዊና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ያውም በቤተ መቅደስ ውስጥ መፈጸሙ ብዙውን የዓለም ሕዘብ አስቆጥቷል፡፡ አሳዝኗል፡፡ በዚህ ሀገር እንዲህ ዓይነት የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች አንድ ጊዜ ሜዲያ ላይ ከወጡ ያሉትን ችግሮች በሙሉ እየሠረሰሩ ሳያወጡ አያቆሙምና ጉዳዩ በአንድ ዜና ብቻ ላያቀቆም ይችላል ተብሏል፡፡ ፡፡

ይህን ጉዳይ ለማስቆምና የቤተክርስቲያኒቱ ነባር ውስብስብ ችግሮች በሜዲያ እንዳይገለጡ እንዲሁም በቤተክርስቲያኒቱ የወደፊት ህልውና ላይ ትልቅ ችግር እንዳያስቀምጥ ፍርሃቱ ያደረባቸው አንዳንድ ሰዎች ጉዳዩ የሚመለካታቸውን አንዳንድ ሰዎች ዘንድ እየደወሉ ለማስቆም ቢሞክሩም ያልተሳካ ሞሆኑ ታውቋል፡

1 comment:

  1. Our Ethiopian Orthodox Church must be lead by the church leaders who knows about the "Fitha-Negest", "Degua", "Bible" from A-Z ec. not by the bunch of thives. First of all the present board members must be step down. The present church policy, procedure and regulations must me approved by the whole members of our church. The board members election must be offical not secret. Aba Moges and his son prist Yohanes must be suspended and we need Orthodex educated leader of the church (Yedeber Aleka). He is the one who must lead the board members.
    Thanks,
    May God give us peace for our church!!

    ReplyDelete

አስተያየት