Monday, April 19, 2010

የሂሳብ መርማሪና አጣሪ ኮሚቴ የሥራውን ውጤት አቀረበ !

ሰላም ተዋህዶ ቅዳሜ April 17 2010 በተደረገው ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ ያልተካፈለች ብትሆንም ስብሰባውን የተካፈሉ አንዳንድ ሰዎችን በማነጋገር ያገኘችውን ዘገባ በአጭሩ እንደሚከተለው ዘግባዋለች፡፡
በአስተዳደር ቦርድ የሂሳብ አያያዝ ዝርክርክነት ምክንያት በገንዘብ ያዥና ሂሳብ ሹሙ የተቀናጀ አሠራር የ11 ሺህ ብር ጉድለት ታይቷል በሚል አጀንዳ ሂሳብ እንዲያጣራ በሕዝብ የተመረጠው ኮሚቴ የምርመራውን ውጤት አጠናቆ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት በቁጥር ወደ ሀምሳ ለሚጠጉ የቤተክርስቲያኑ አባላት ዘገባውን አቅርቧል፡፡
የአስተዳደር ቦርድ የአሠራር ዝርክርክነት የሚታይበት እንጂ የጎደለ ገንዘብ እንደሌለ በሪፖርቱ የተገለጠ ሲሆን ነገር ግን ከህዝብ ተሰብሰቦ ወደ ባንክ መግባት ከሚገባው ገንዘብ በየጊዜው እየተቀነሰና እየዘገየ በሌሎች ጊዜያት እየተቆጠረ ከሚገባው ገንዘብ ጋረ እየተደመረ ይገባም እንደነበር ሪፖርቱ በመግለጽ ለዚህ ‹ገንዘብ እየተቀነሰና እየዘገየ ለምን ይገባል?› ብሎ የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴው ገንዘብ ያዡንና ሂሳብ ሹምን በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ከእነዚህ ግለሰቦች የሚደርሠው ምላሽ ግን ስድብና ቁጣ እንደሆነ ኮሚቴው ለሕዝቡ ብሶቱን ገልጧል ፡፡ በአንጻሩም ‹ይህ ለምን ሆነ ገንዘቡስ ለምን በወቅቱ መግባት ሲገባው እየዘገየ ይገባል? › ተብሎ ከሕዝብ ለተጠየቀ ተደጋጋሚ ጥያቄም ከሂሳብ ሹሙም ሆነ ከገንዘብ ያዡ ምንም ዓይነት መልስ ሳይሰጥበት ተድበስብሶ ታልፎአል፡፡
ምንም እንኳን የሂሳብ ሪፖርት አጣሪ ኮሚቴው የጎደለ ገንዘብ የለም በሚል ማጠቃለያ ሪፖርቱን ቢያቀርብም የ computer Visual አሠራሮችን ሁኔታ ለማየትና ሂሳቡን ለማመሳካር ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢቀርቡም ሂሳብ ሹሙ የ computer በሩን ዘግተው መርማሪዎቹ እንዳያዩ ማድረጋቸውን ኮሚቴው በቅሬታ መልክ ገልጧል፡፡ 
በሌላም በኩል ደግሞ በዚሁ የሂሳቡን ሪፖርትን ለማዳመጥ በመጣው ሕዝብ ፊት የቀድሞ ቦርድ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ኢዩኤል ነጋ ‹ ሃያ አምስት አመት ሙሉ የደከምኩለትን ቤተክርስቲያን አዲሱ የአስተዳደር ቦርድ 4000 ዶላር ወጪ አድርጎ የቤተክርሰቲያኑን ቁልፎች ሁሉ በመቀየር እኔን ወደ ቢሮ እንዳልገባ ከልክሎኛል በዚህም ምክንያት እጅግ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ እዚህ ቤተ ክርስቲያን አልደሰርስም› በማለት ጉባኤውን ተሰናብተውና አቋርጠው ዳግም ላይመለሱ በመናገር የእጃቸውን አውራ ጣት በመቀሠር የሰላምታ ምልክት ለወዳጆቻቸው በማሳየት ከስብሰባው ወጥተው ሄደዋል፡፡
በሰፈሩት ቁና ይሰፈራል እንደተባለው የዛሬ ዓመት የቤተክርስቲያኒቱ የቢሮ አስተዳደር ሠራተኛ የነበሩትንና በፈቃዳቸው ከሥራቸው የለቀቁትን ዲያቆን ዓለማየሁን አቶ ኢዩኤል ነጋ በፖሊስ አስጎትተው ከስብሰባ ማስወጣታቸው ይታወሳል፡፡ ዛሬ ግን እሳቸው ዶክተር ግርማ ፖሊስ ጠርተው ሳያስጎትቱዋቸውና በኃይል ሳያሶጡአቸው ይህንኑ ፈርተው በጊዜ መውጣታቸው አቶ ኢዩኤልን ብልጥ ቢያስመስላቸው ለዚህ ሁሉ የተመሰቃቀለ የቤተክርስቲያኒቱ ችግሮች ግንባር ቀደም ተጠያቂው እሳቸው መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ‹በወቅቱ በስልጣናቸው ላይ በነበሩበት ጊዜ የአስተዳደር ቦርዱን አማካሪዎችና አንዳንድ የችግሩን መድረሻ ቀድመው የተረዱ ሰዎችን ጠቃሚ ምክሮች ቢሰሙና በትክክለኛ የአቋም መሥመር ላይ ቆመው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ያለንበት ችግር ላይ አንደርስም ነበር› በማለት ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
የአቶ ኢዩኤልን መውጣት ተከትለው በሂሳብ ሹሙና ገንዘብ ያዡ ከሂሳብ አጀንዳ ውጭ በሆኑ ትምክታዊ ንግግሮች በመበሳጨት አንጋፋ የሆኑ የቤተክርስቲያኑ አባላት አንዳንድ እያሉ ጥለው በመውጣት የስብሰባውን አዳራሽ ባዶ ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ገንዘብ አለማጉደላቸው በአጣሪ ኮሚቴው የተመሰከረላቸው ሂሰብ ሹምና ገንዘብ ያዥ ደግሞ ከቀሪዎቹ አዳዲስ ቦርድ አባላትና ሚስቶቻቸው ጋር በደስታ እንዳመሹ ለማወቅ ተችሏል፡፡

1 comment:

  1. I like some of your bog. Some time you need to watch your language. As we all come from different back ground, we have some common culture and same origin. We have to be faire for one each other as a Christian. Some of us we hear what we want and when we want, and we support or do what we want which we can’t handle the consequence we brought. I do not know why we are unruly among our self as if we brought from back home. “To be a good leader, you got be a good follower”.

    I think giving a free service for a church is to get blessed, not make a sine. Our church is been teaching the religion and the congregation must fully believe on God and must be committed. What we see is very shameful from the Priests to the followers.

    I have also noticed, one of the Priest is openly started it campaign to divide the member of our church and the elected board members in the past two Sunday. If he could to take control the church if not to open his own church, which I do not have a problem in fact I will help what I can as a Christian of same faith for the Glory of God. But this person motive is not for the Glory of God, it is self motivated $. One thing he never realized is he is just an employee and his immigration status might be jeopardized. The church has more power than him to put him on the plane back to where belongs.

    ReplyDelete

አስተያየት