የአስተዳደር ቦርድ መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ ካሰናበተበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ ባደረበት የፍርሃት መንፈስ ባልተለመደ ሁኔታና ከወትሮው በተለየ መልኩ በርካታ የፖሊስ ሠራዊትን ከሌሊቱ 3 ጀምሮ በቤተክርስቲያኒቱ ግቢ ውስጥ እንዲሠማሩ ማድረጉ ብዙውን አማኝ ክርስቲያን አሳዝኗል፡፡
በቤተክርስቲያን ዙሪ የሚከትሙ ሰማያውያን መላእክትን አባረው በምትካቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን በምድራውያን የፖሊስ ሠራዊት እንድትከበብ ማድረጋቸው የቦርድ አባላቱ ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ብዙ ሰው ተጠራጥሯል፡፡
በቤተክርስቲያን ዙሪ የሚከትሙ ሰማያውያን መላእክትን አባረው በምትካቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን በምድራውያን የፖሊስ ሠራዊት እንድትከበብ ማድረጋቸው የቦርድ አባላቱ ቤተክርስቲያንን የሚያስተዳድሩ መሆናቸውን ብዙ ሰው ተጠራጥሯል፡፡
ይህ መልካም ያልሆነ ሥራቸው እንቅልፍ የከለከላቸው አንዳንዶቹ የቦርድ አባላት ለቅዳሴ እንኳን ማልደው ለመምጣት እንደሞት የሚከብዳቸው እነ አቶ አበራ ፊጣ ከሌሊቱ 3.00 am ጀምሮ እስረኛ እንዳመለጣቸው ዘበኞች የፎቁን ደረጃ ሲወጡና ሲወርዱ መልአከ ሣህል ቢሮአቸው ውስጥ ገብተው የተቀመጡ እስኪመስል ድረስ በጥርጣሬ አካባቢውን ሁሉ ሲሰልሉ እዳነጉ ድርጊቱን በአድናቆት ይመለከቱ የነበሩ አንድ ግለሰብ ገለጹ፡፡
ከሌሊት ጀምሮ እስከነጋበት ጊዜ ድረስ ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣ የነበርው ሕዝብ የፖሊሱን ብዛት በማየት ግራ እየተጋባና የተፈጠረውን ነገር ለማወቅ እበር ላይ ያገኘውን ሁሉ እየጠየቀ ይገባ እንደነበረም ታውቋል፡፡ በርካታ ሕዝብ የመልአከ ሣህል ከሥራ መሰናበት ከተሰማበት ከቅዳሜ ምሽት 9.00 pm ጀምሮ እርስ በእርሱ በስልክ ሲደዋወል ያደረ ቢሆንም በዚያኑ መጠን ያልሰማው ደግሞ ግራ በመጋባት እስከ ቅዳሴ ማለቂያ ሰዓት ድረስ ሳያውቅ ቆይቷል፡፡
በሌላም መልኩ የቦርድ ከፍተኛ የጥፋት ተባባሪ የሆኑት ቄስ ዮሐንስ ሞገስ በመልአከ ሣህል መባረር የደስታ መግጫ መዝሙራቸውን ከክህነቱ ፐርሰናሊቱ ውጭ በመሆን ከእብደት ባልተናነሰ መልኩ ያሳዩት የነበረው ድርጊት ብዙውን ሕዝብ አበሳጭቷል፡፡ ዝማሬው ይቅረብ የነበረው በምስጋና መልኩ ሳይሆን የማንፈልገው ካህን ተወግዷልና እልል በሉ የሚል መልእክት ያለው መሆኑን የተጠራጠሩ የመልአከ ሣህልን ከሥራ መሰናበት ያላወቁ ብቻ ነበሩ፡፡
በመቀጠልም በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ በትህትናቸውና በእርጋታቸው የሚወደዱት ቀሲስ መስፍን እጅግ በተረጋጋ መንፈስ ሆነው ያስተላለፉት መልዕክትና በመጨረሻም ሲቃ እያነቃቸው ለሕዝቡ ያደረጉት የስንብት ንግግር ብዘውን ሕዝብ አስለቅሷል፤ አሳዝኗል ፡፡ ስለ ቤተክርስቲያናችን ችግርና ስለወገኖቻን ስቃይ ማልቀስና መዘን የሚገባ ነው፡፡
እኛም ደጀ ሰላም የተባለው ድኅረ ገጽ ከዩቲውብ አግኝቶ በአማርኛ ተርጉሞ ያሠራጨውን መልእክት ከቤተክርስቲያናችን ምዕመናን እንባና ኃዘን ጋር አብሮ የሚሄድ ሆኖ ስላገኘነው ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ከዚህ በታች አቅርበነዋል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 26/2010)፦ ቅዱስነታቸው ፖፕ ሽኖዳ 3ኛ 117ኛው የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው። እንደተለመደው ከምእመናን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሚመልሱበት የተለያየ ዝግጅት አላቸው። ከዝግጅቶቻቸው መካከል በየሳምንቱ በካይሮ በመንበረ ማርቆስ የሚያደርጉት አንዱ ነው። እነዚህን የምእመናን ጥያቄዎች So Many Years With The Problems Of People” በሚል ርዕስ እየታተሙ ለንባብ በቅተዋል። ጥያቄዎቹ ዶግማን፣ ሥርዓትን፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የተመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። በእጄ ገብተው ያነበብኳቸው እነዚህ መጻሕፍት ላይ እንደተመለከትኩት ከሆነ መልሶቻቸው የማያወላዱ፣ በአጭር አባባል ብዙ መልስ የሚሰጡ ናቸው። በቅርቡ ለተጠየቁት አንድ ጥያቄ ግን በቃላት መልስ ከመስጠት ይልቅ በእንባና በዝምታ መመለስን መርጠዋል። ከንግግራቸው በአጭሩ እንመልከት።
“በቅርብ ቀናት ስለሆኑ ነገሮች ብዙ ጥያቄዎች (በጽሑፍ) መጥተውልኝ እየተመለከትኩ ነው” ሲሉ ጀመሩ ቅዱስነታቸው። በቅርብ ቀናት ሆነዋል ያሏቸው ነገሮች በአክራሪ ሙስሊሞች በተለያዩ የግብጽ አካባቢዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች እንዲሁም ወጣት ክርስቲያን ሴቶችን በግድ እያገቡ ማስለም እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን ማለታቸው መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ቀጥለውም እንዲህ አሉ።
“ስሙ ወንድሞቼ፤ ልናገረው የምሻው ብዙ ነገር በአእምሮዬ ነበረኝ። በልቤም ውስጥ ከዚያ የሚበልጥ ብዙ ነገር አለ። ይሁን እንጂ ዝም ማለትን እመርጣለሁ። እኔ ዝም ማለትን የመረጥኹት (በምትኩ) እግዚአብሔር እንዲናገር ስለምፈልግ ነው። እመኑ፤ ዝምታችን ከመናገር በላይ ገላጭ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ደግሞ ዝምታችንን እያዳመጠ ነው። እግዚአብሔር ዝምታችንን ይሰማል። የዝምታችንን ትርጉምና እየደረሰብን ያለውን መከራም ያውቃል። መከራ እየተቀበልንበት ስላለው ጉዳይ ነገራችንና ችግራችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር አሳልፈን እንሰጣለን። በእጆቹም ላይ እንተወዋለን። እናም ‘ያንተ ፈቃድ ይሁን/ ወይኩን ፈቃድከ’ እንላለን። (ጌታ ሆይ) ‘ይህንን ችግር መፍታት ከፈለግኽ ፈቃድህ ይሁን፣ የመከራን መስቀል እንድንሸከም ከፈቀድክም… (ካሉ በኋላ እንባቸውን እያፈሰሱ አለቀሱ) “…ችግራችንን ለእግዚአብሔር እንስጥ/ እንተው ያልኩበት ምክንያት እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ/ የሚቆጣጠር ስለሆነ ነው። እርሱ ሁሉን ያያል። ሁሉንም ነገር ይሰማል። ሁሉንም ነገር ያውቃል።”
ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? ስለ ቤተ ክርስቲያን ደኅንነት፣ ስለ ምእመኗ ጤንነት፣ ስለ ልጆቿ ችግር የሚያለቅስ አባት ያላት ቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት። በፈንታው ደግሞ ስለ እርሷ ማልቀስ ሳይሆን የሚያስለቅሷት፣ ስለ እርሷ የሚያዝኑ ሳይሆን የሚያሳዝኗት፣ ልጆቿን በእንባቸውና በትምህርታቸው አጥር መከታ ሆነው ከመጠበቅ ይልቅ ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሊለቀስላት ይገባል።
“ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪን የምትሰጥ” እንዲል ቅዳሴው ለቤተ ክርስቲያኑ የሚያለቅስ በርግጥም ቅን መሪ ነው።
ማስታወሻ፦ ቅዱስነታቸው ሲያለቅሱ የሚያሳየውን የቪዲዮ መልእክት ከዚህ (ቪዲዮ) ተመልከቱ፤ በግርድፉ የተረጎምነውን ንግግራቸውን አድምጡ። www.youtube.com/watch?v=ESG-KO4QX88&feature=relate
ማስታወሻ፦ ቅዱስነታቸው ሲያለቅሱ የሚያሳየውን የቪዲዮ መልእክት ከዚህ (ቪዲዮ) ተመልከቱ፤ በግርድፉ የተረጎምነውን ንግግራቸውን አድምጡ። www.youtube.com/watch?v=ESG-KO4QX88&feature=relate
May God give us a peace.
ReplyDeleteበስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ ኣሀዱ ኣምላክ ኣምላክ ኣሜን። በዚህ በዳላስ የኖርኩት 13ዓመት ነው። አግዚኣብሔ ሐዘናችንን ተመልከት ብለን አናልቅስ ሁላችንም።
ReplyDelete