የዓርብ ጉባዔ በአዲስ መልክ ተጀመረ፡፡
ቀደም ሲል በሃይማኖት አባቶች በመልአከ ሣህል አወቀ ተሰማና በቀሲስ መስፍን ደምሴ ይሰይጥ የነበረው የዓርብ ጉባዔ ካለፈው ዓርብ June 18 2010 ዓ.ም ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ መጀመሩን ለማወቅ ተችሏል ፡፡ይህ በደብሩ በተከሠተው ችግር ምክንያት የተበተኑትንና አዝነው በየቤታቸው የተቀመጡትን ምእመናን ሁሉ በማሰባሰብና አንድ ቤተ ሰብእ ለማድረግ የተጀመረው ጉባዔ በእለቱ በርካታ ምእመናን የተገኙበት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡
የጉባዔው እንደገና መጀመር ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚረቆሩ ምእመናንን ሁሉ ከልብ ያስደሠተ ጉዳይ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ የተበላሸ አስተዳደር ምክንያት በተከሠተው ችግር ልባቸው በኃዘን የተጎዳ ክርስቲያኖችን ሁሉ ልብ የሚጠግንና በቃለ ወንጌል የሚያጽናና ጉባዔ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡
በዚሁ ጉባዔ ላይ ወቅታዊ የወንጌል ትምህርት በቀሲስ መስፍን ደምሴ የተሠጠ ሲሆን የቅዱስ ሚካኤልን አመታዊ ክብረ በዓል በአትላንታ ጆርጂያ ለማክበር ተጋብዘው የሄዱት መልአከ ሣህል አወቀ ተሰማም ካሉበት ቦታ በመሆን ቡራኬያቸውንና መንፈሳዊ መልዕክታቸውን በስልክ ለጉባዔው አሰተላልፈዋል፡፡
በተጨማሪም በአስተዳደር ቦርዱ የአስተዳደር እውቀት እጦት ምክንያት የተናጋውን የቤተክርስቲያኒቱን ሰላም ወደ ቀድሞው ቦታው ለመመለስ በቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በኩል በሕግ የተጀመረው መልካም ሂደት እልባት እስኪያገኝ ድረስ ጉባኤውን በተሸለ መልኩ ለመቀጠልና ለማሳደግ እንዲረዳ ከፍተኛ የገንዘብ መዋጮ የተደረገ ሲሆን ይህም የሕዝቡን ሞራልና ስሜት ምን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ የሚያሳይ ጥሩ ጅምር እንደሆነም ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
የጉባኤው መጀመር በጣም የሚያስደስት ነውና ጥረቱ ይቀጥል፡፡ ለዚህ የሚያስፈልገውን ሁሉ መስዋእትነት ሕዝቡ ይከፍላል ብዬ አምናለሁ ፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ጉባኤውን ያስፋ!
ReplyDeleteይበል ያሰኛል!!
The truth will set you free. Keep up the true Orthodox Religion alive. Also, to hear more about the concern of our church (TALAK MENFESAWE TEREY QUTER 2), come to the meeting on Saturday, 26th June, 2010, at 3:30 pm sharp on time to attend at Crowne Plaza, on I-635 & Coit on Alpha Rd. This is a good blog. Keep up the good job. Support is on your side. URC Member.
ReplyDeleteRight side color page is hard to read the writing. Cna you use a little bright color on the background or change the color of the writing to brighter color. Thanks
ReplyDelete