Thursday, October 7, 2010

እጅግ አደገኛ ነው !
እለቱ እሁድ ነው፡፡ችግሩም የተከሰተው በሰሜን ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በቅርብ ቀን ነው፡፡ ሴትየዋ በሚዝናኑበት የጀልባ ፍሪጅ ውስጥ ካስቀመጡት በቆርቆሮ የታሸጉ የለስላሳ መጠጦች መካከል ኮካ ኮላን መርጠው ይጠጣሉ ፡፡በማግስቱ ሰኞ በድንገተኛ አምቡላንስ ተወስደው ወደ ሆስፒታል ይገባሉ፡፡በጣም በመድከማቸው ወደ አይሲዩ( Intensive care unit) ይወሰዳሉ፡፡ብዙም ሳይቆዩ ከሁለት ቀናት በኋላ ረቡዕ ዕለት ሕይወታቸው ያልፋል፡፡ ሀኪሞች ለሴትየዋ ሞት ምክንያት የሆነው ‹ሌፕቶስፒሮሲሰ› በመባል የሚታወቀው አደገኛ በሽታ መሆኑን በምርመራ ያረጋግጣሉ፡፡የዚህ በሽታ ምልክት ደግሞ ሴትየዋ ከጠጡት የኮካኮላ ቆርቆሮ መጠጫ ቀዳዳ አካባቢ ባለው የቆርቆሮው አካል ላይ በምርመራው ይገኛል፡፡
የአይጥ ሽንት መርዛማና ሰው ሊገድል የሚችል አደገኛ ‹ሌፕቶስፒሮሲሰ› መርዝ በውስጡ እንደለው የሳንይስ ምርምር ውጤት ያረጋግጣል፡፡በዚህ መሠረት ሴትየዋም የሞቱት በለስላሳ መጠጥ ማመርረቻም ሆነ በማከፋፈያ ትላልቅ መጋዘኖችና በየመሸጫ መደብሮች ውስጥ የሚኖሩ አይጦች በላዩ ላይ በመሄድና በላዩ ላይ በመሽናት የተበከለውን የኮካኮላ ቆርቆሮ ሳያጥቡ ከነመርዙ አፋቸው ላይ ደቅነው በመጠጣታቸው ምክንያት ነው፡፡
ስለዚህ ማንኛውንም በቆርቆሮም ሆነ በጠርሙስ ያሉ መጠጦችን ሳያጸዱ በራሳቻ በእቃዎቹ የመጠጣትን ልምድ ማስወገድ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ መጠጦችን ብቻ ሳይሆን በቆርቆሮና በፕላስቲክ ታሽገው የሚሸጡ ምግቦችንም የውጭ አካላቸውን በሚገባ አጽድቶ መጠቀም ከእንዲህ አይነቱ ድንገተኛ በሽታና ሞት ለመዳን ይጠቅማል ፡፡
በዚህ ዙሪያ በተደረገ ጥናት የጀርምና የባክቴሪያ ከፍተኛ መኖሪያዎች ናቸው ተብለው ከሚገመቱት የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች ይልቅ በቆርቆሮ የሚታሸጉ ለስላሳ መጠጦችና የቆርቆሮ ምግቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጀርምና የባክቴሪያ ክምችት እንዳለ ተረጋግጧል፡፡

1 comment:

  1. በ dallas eotc blog ላይ እንደ ሊዲያ ልባችንን ይክፈትልን ለሚለው ጽሁፍ አስተያየት
    ካህኑ የካህንነታቸውን አስተምረዋል ነገር ግን እናንተ ሁሉን ሰው በናንተ መረዳትና የሀይማኖት እውቀት ልክ መገመትና ለማስፈራራት መሞከር ቂልነት ነው ክሱ እንዲቀር ብቻ የሳቸው ግዝት በጳጳስም አይዳኝ፣ የመጨረሻው ምሁር ናቸው፣ እውቀታቸው ልክ የለውም፣ ስልጣናቸው ልዩ ነው......ምናምን የተባሉት አባባሎች ሁሉ ተራ ዝባዝንኬዎች ናቸው የሳቸውን ግዝት የምትፈሩና ለካህን ስልጣን ክብር የምትሰጡ ቢሆን ገዝቻለሁ ስድብ ይቁም ያሉ እለት አልቅሰህ ንስሀ ገብተህ/ታችሁ/ ስድብህንና የጭቃ ጅራፍህን ታቆም ነበር ይሄ አስመሳይነት ነውና ይቅርብህ/ባችሁ/ የእርቅ ትምህርት በሁለቱም ወገን ላሉ ነው እውነተኝነት ካላችሁ አንተም ተው አንተም ተው ማለት ነው እንጂ በሌለህበት ቦታ በስማ በለውና ባልገባህ የሀይማኖት ትምህርት ትርጓሜ ገብተህ የጅል ማስፈራሪያህን ተው እዚህ ያለነው በህግም፣ በፀሎትም፣ በወንጌል ትምህርትም፣ በባህላችን መሰረት በሽምግልናም አጣማችሁ ያገዘፋችሁትን ነቀርሳ ቆርጠን ለመጣል ጠርዝ ላይ ነንና ተወን ተወደደም ተጠላም ጊዜው የለውጥ ነውና ሁላችንንም/ንፁህ የተዋህዶ ልጆችን ለማለት ነው/በሚያስማማ መልኩ የደስታችን ቀንና የቤተክርስቲያናችን የትንሳኤ ቀን በቅርቡ ይሆናል። ባካችሁ ሚዛን ያለው ያልወረደ ፅሁፍ ፃፉ የሁሉንም አቅም የሚመጥን ፡ይህንን ጽሁፍ በ dallas eotc blog ላይ ለማውጣት ተልኮ ስላላወጡት ለእናንተ ላኩት። አመሰግናለሁኝ።

    ReplyDelete

አስተያየት