Friday, June 11, 2010

 የስብሰባ ጥሪ

በስመ አብወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በአስተዳደር ብቃት አለመኖር ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ ቀደም ሲል በበጎ ፈቃደኝነት በተነሳሱ ሽማግሌዎችና የሰላም ልዑካን አማካኝነት ብዙ ጥረት እንደ ተደረገ ይታወቃል፡፡



ይሁን እንጂ በአስተዳደር ቦርዱ እምቢተኝነት ምክንያት የሰላም ጥረቶቹ ሁሉ ሳይሳኩ ቀርተዋል፡በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችንን ከገጠማት ችግር ለመታደግና አንጻራዊ የሰላም መፍትሄን ለመፈለግ እንዲያስችል በደብራችን የሚገኙ ምእመናን ሁሉ አንድነትና ሕብረት አስፈልጓል፡፡በዚሁም ጉዳይ ለመነጋገርና ወደ አማራጭ የመፍትሄ መንገድ ለመምጣት እንዲረዳ ቅዳሜ JUNE 26 2010 ታላቅ የሕዝብ ስብሰባ ተዘጋጅቷል፡፡
ስለዚህ እርሶም በቤተ ክርስቲያን ጅነቶ በዚሁ ስብሰባ ላይ በመገኘት የሰላም መፍትሄው ፈላጊ አንዱ አካል እንዲሆኑ አስተባባሪው ኮሚቴ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ማሳሰቢያ
- የስብሰባ ቦታው CROWN PLAZA 7800 ALPHA ROAD , DALLAS , TX, 75240 ሰዓቱ 3:30 Pm ነው፡፡
-ይህን ማስታወቂያ በዚህ ብሎግ ላይ ለማንበብ አጋጣሚው ለሌላችው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የቻሉትን ያህል በማባዛት እንዲያድሉና መልእክቱን ላልሰሙት ሁሉ እንዲያደርሱ በአክብሮት ይጠየቃሉ፡፡


No comments:

Post a Comment

አስተያየት