Monday, June 7, 2010

ሠበር ዜና !

   
አዲስ አበባ

 የዳላሰ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ጸሐፊና የውብ እንጀራ ባለቤት የሆኑት አቶ አበበ ጤፉ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያደረሱት የከፋ የአስተዳደር በደል 90% በሚሆኑ አማንያን ዘንድ እጅግ እንዲጠሉ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ለአካካቢው ነዋሪ በየመደብሩ የሚያስቀምጡት የውብ እንጀራ ገዢ አጥቶ በመበላሸት እየተጣለ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ አቶ አበበና አጋሮቻቸው የቤተክርስቲያኒቱን ካህን ያለአግባብ ከሥራ ያሰናበቱትና ፖሊስ በመቅጥር ሕዝቡን ያስደበደቡት ገና ወደ ቦርድ በገቡ በሦስት ወራቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ 

አቶ አበበ ለኢትዮጵያውን የሚያቀርቡትን እንጀራ የሚያስቀምጡባቸው የአንዳንድ መደብሮች ባለቤቶች የውብ እንጀራ ለሆድ ተስማሚ ያልሆነ ንጥረ ነገር ስላለበት እየታመንን ነው በማለት ብዙ ሰዎች በተደጋጋሚ አቤቱታ እያቀረቡ ስለሆነ ‹ከዛሬ ጀምሮ ይህንን እንጀራ በመደብራችን ልንሸጥ አንችልም፡፡› በማለት ወደ መደብራቸው እንዳይገባ የከለከሉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሣራን በአቶ አበበ ንግድ ላይ እያደረሰ ነው ሲሉ ወስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

ለቤተክርስቲያኗ ሳይሆን ለጥቂት ሰዎች መጠቀሚያ ሆነው በማያውቁት ነገር ውስጥ ገብተው ችግር ላይ የወደቁት አቶ አበበ ጤፉ ከዚህ ችግር ውስጥ ለመውጣት ሲሉ አመለካከታቸውና አካሄዳቸውን ከቀሪዎቹ የቦርድ አባላት ጋር አንድ ባለማድረጋቸውና ልዩነት እያሳዩ በመምጣታቸው ሂሳብ ሹሙና ደጋፊዎቻቸው በዓይነ ቁራኛ እየተመለከቷቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ዮሴፍ ረታም ከሕዝብ በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ዘለፋና ተግሣጽ የተነሣ ከሌሎቹ የቦርድ አባላት ይልቅ ከአቶ አበበ ጋር የመቀራረብ መንፈስ በማሳየታቸው አሳቸውም እንዲሁ በሂሳብ ሹሙና በደጋፊዎቻቸው ቁራኛ ዓይን ውስጥ ገብተዋል ተብሏል፡፡
ይህንኑ መንፈስ በመከተል ወ/ሮ ቡክሪና የሂሳብ ሹሙ ባለቤት ወ/ሮ ዙሪያሽ ቀጣዩ ፕሮጄክታቸው የቦርዱን ሊቀመንበርና ጸሐፊውን ቀስ ብለው ከቦርድ አባልነት ለማሳጣት ምስጢራዊ የሆነ አዲስ እስትራቴጂ እየቀየሱ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

በተመሳሳይ መልኩ ቀደም ሲል ጥሩ የንግድ ተቋማት የነበሩዋቸው እኚሁ ወ/ሮ ቡክሪና ባለቤታቸው በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ከበፊት ጀምሮ የሚያደርጉት ከውጭ ሆኖ የማበጣበጥና የማፈራረስ ተግባር የተነሣ በዳላስ ከተማ በሚኖሩ በአብዛኛው የቤተክርስቲያናችን ሰዎች እንዲጠሉ እዳደረጋቸው ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያውያንን ማእከል ያደረገው ይኸው የንግድ ሥራቸው በዚሁ የአፍራሽነት ተግባራቸው ምክንያት ለኪሣራ እንደዳረጋቸውና አሁን የያዙት የካተሪንግ ሥራም ደንበኞችን እያሳጣቸው እንደመጣ የውስጥ ገባና አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ በመሆኑም ወ/ሮ ቡክሪና ባለቤታቸው ቤተ ክርስቲያኑን ለማፈራረስ ከሂሳብ ሹሙ ጋር በሽርክና የጀመሩትን የጥፋት ተግባር አቁመው አርፈው ሥራቸውን እንዲሠሩና ልጆቻቸውን እንዲሳድጉ ለመምከር ለእሳቸው በጣም ቅርበት ያላቸው ሴቶች ወደ ቤታቸው ለመሄድ ማቀዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንግዲህ ‹ምከረው ምከረው እምቢ ካለ ግን መከራ ይምከረው !› ይላል ይሄ ነው

2 comments:

  1. እንደ ሰንበቴ መሆን አያስፈልግም

    ReplyDelete
  2. Dear editors I appreciate your devotion for the settlement of current conflict around the church. But I am not happy with some part of this article. Because I think as a christian there is no any connection between "web enjera" market and quality to the church administration. please rethink again. Focus on the exact problem issue rather that personalize the problem which may misled people to group conflict. Thank you

    ReplyDelete

አስተያየት