Friday, May 14, 2010

የሰሞኑ ዜና

የአስተዳደር ቦርዱ መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ ካሰናበተበትና ቀሲስ መስፍንም የአስተዳደሩን የተባላሸ አሠራር በመጠየፍ ሥራቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁበት ቀን ጀምሮ በአስተዳደሩም ሆነ በአባትና ልጅ ካህናት እንዲሁም በምእመናኑ መካከል ውጥረትና አለመረጋጋት መፈጠሩን ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ ካህናትንና ምእመናንን በማባረር ሰላም አመጣለሁ በማለት ሌት ከቀን ለጥፋት የሚደክመው ቦርድ በስሜትና ባለማስተዋል የፈጸማቸው ከፍተኛ ስህተቶች ከአስተዳደሩ አልፎ በቤተ ክርስቲያኒቱ የወደፊት አገልግሎት ላይ ከባድና አስቸጋሪ ክስተቶች ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ አንዳንድ ሁኔታዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከይግባኝ ቀጠሮውና ከአዲሱ የፍርድ ቤት ክስ በተጨማሪ የጋርላድ ፖሊሰ ጣቢያም ‹በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የወንጀል ምርመራ (Criminal Investigation) ማድረግ እፈልጋላሁ› በማለት ለአስተዳደር ቦርዱ ሰሞኑን ደብዳቤ የላከ ሲሆን ይህም ጉዳዩን ከባድና አደገኛ ያደርገዋል በማለት የሕግ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ የአስተዳደሩን የተበላሸና አምባገነናዊ አሠራር አለም እያየውና እየታዘበው ያለውን ግልጥ ጉዳይ አስተዳደሩ የሠራው ሁሉ ትክክል እንደሆነ ለማስመሰል ፖሊሶች በምእመነናኑ ላይ ያደረሱትን ድብደባ፤ እንግልትና ወከባ ከቪዲዮው ካሜራ ቆርጦ በማውጣት ጣራና ግርግዳ በማሳየት እውነታውን ለመደበቅ ያደረገው ሙከራ ሁሉ አስተዳደሩ በማጭበርበርና በውሸት ሥራዎች የተካነ መሆኑን የሚያሳ እኩይ ተግባር ነው ተብሏል፡፡ 

በሌላም በኩል ከቤታቸው ተቀምጠው የሂሳብ ሹሙን ለጥፋት ሥራ አስታትቀውና ቀብተው የለኩት ወ/ሮ ቡክሪና ባለቤታቸው የአስተዳደሩን ተግባር በመቃውም በደብል ትሪ ሆቴል ተሰብስበው ከነበሩት ምእመናን መካከል ወደ አንዳንዶቹ ቤት በመሄድ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲያደርጉ እንደ ሰነበቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡‹‹ይህ አስተዳደሩ እየሠራ ያለው ተግባር ትክክልና እኔም ማኅበረ ቅዱሳንን ከቤተ ክርስቲያን ለማጠፋት 20 አመት ሙሉ የታገልኩለት አላማ ስለሆነ አርፋችሁ ብትቀመጡ ይሻላል› በማለት የሚዝቱት ወ/ሮ ቡክሪ ያሉበትን አገር ረስተውት በጉልበትና በኃይል ጭምር ምሥዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ባሰሙት ፉከራና ዛቻ መግለጻቸውን ለማወቅ ተችለዋል፡፡

1 comment:

  1. I know this fake doctor is a criminal. I can't wait to see him in jail. This is really a very good news for all people who seek justice. May God protect our church from Menafekan. Amen!

    ReplyDelete

አስተያየት