Monday, August 1, 2011

ከተሐድሶ ዓላማዎች አንዱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓውደ ምሕረትና የዘፈን ቤት መድረኮች አንድ ዓይነት ገጽታ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው !
የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሁለ ገብ ተሐድሶ ያስፈልጋታል ብሎ ለጥፋት የተነሣው ኢኦርቶዶክሳዊ ድርጅርት ዓላማውን ለማሳካት በሥውር ከሚንቀሳቀስባቸው ዘዴዎቹ አንዱ ባልነበሩበት መንፈሳዊ ሕይወት መነኩሴ ፤ ቄስና ባሕታዊ እየመሰሉ አስነዋሪ ድርጊቶችን በአደባባይና ሰው በሚታይባቸው ቦታዎች በመፈጸም ሕዝቡ ካህናትንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲጣላ ማድረግ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ‹እኔ ድሮ ቄስ ነበርኩ ፤ መነኩሴ ነበርኩ ፡ አሁን ግን ጌታን ተቀብያለው እያሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ግራ በማጋበት የፕሮቴስታንት መንፈስ ሰለባዎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡

ይህ በፎቶግራፍና በቪዲዮ ምስሉን የምታዩት ዘማሪ ‹ ድሮ በገዳም በቀን አንድ ጊዜ ጥራጥሬና የሻገተ እንጀራ እየበላው በገዳም ውስጥ በጾምና በጸሎት እኖር ነበር፡፡ አሁን ግን ያንን ትቼ ባሻኝ ሰዓት እየበላሁ ለጌታ ዘማሪ ሆኛለሁ › ፤ የሚለው ናትናኤል የተባለው የፐሮቴስታንት ዜማ አቀንቃኝ ነው፡፡
አስቀድሞ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ያከበራቸው ጻድቃን ክብራቸው በሰዎች አንደበት የሚጨመርና የሚቀነስ ባይሆንም መናፍቁ ዘማሪ የጻድቃንን ክብር በዝማሬው ለመቀነስ ሞክሯል፡፡



በፕሮቴስታንት ተከታዮች ዘንድ አባ ናቲ በማባል የሚጠራው ይህ ግለሰብ በአሁኑ ጊዜ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ክራይስት ኢንተርናሽናል ውርክ ሾፕሴንተር(Christ International Work Shop) በሚል መጠሪያ የሚኒስትሪ ፈቃድ አውጥቶ በዚያ እንደሚተዳደር ትሪኒቲ በሚባል ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚታተም ጋዜጣ በሠጠው ቃለ ምልልስ ለመረዳት ተችሏል፡፡

2 comments:

  1. ayi saywashim menor yichala,sewun meshewed yichal yihonal Egziabherinina hilalnin gin meshewed atyichalim,erasun yemiyatalil sewu mechereshaw tsestet new.abam hone daba nebsun yimarew. aatalay sewu kehulet ermija behuala berasu giza yigaletal.

    ReplyDelete
  2. Yemigerm Zefen ayen! Woy meselten!!!!!!!!!!!

    This is not tehadiso it is protestnat.

    My recommendation is if the church makes some corrections on gedilate and but strictly follow its cannons we can save the people from moving to protestant. Otherwise the teamire mariam, seatat and other gedles have problems that make people to move to protestants. The protestants have dogmatic problems our gedeles have also problems. We need to wipe our home to keep the people live in the church.


    Magic

    ReplyDelete

አስተያየት