Saturday, April 24, 2010

አምባ ገነኑ ቦርድ መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ አሰናበተ !

ትናንት ቅዳሜ ማምሻውን ለስብሰባ ይፈለጋሉ ተብለው በስልክ ተጠርተው ቦርድ ጽ/ቤት ተጠርተው የቀረቡት መልአከ ሣህል በሚያስተምሩት እውነተኛ የወንጌል ትምህርት ምክንያት እንደ ክርስቶስ በሐሰት ተወንጅለው አስተዳደርን በማያውቅ አምባገነን ቦርድ የስንብት ደብዳቤ ተነቦላቸው ሁለተኛ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ በሴት ፖሊስ ተገደው በመፈረም የስንብት ደብዳቤውን ተረክበው መውጣታቸውን ለማውቅ ተችሏል፡፡

ለቤተክርስቲያናችሁ የምትቆረቆሩ ምእመናን በሙሉ ጉዳዩን በእርጋታና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንድትከታተሉ እያሳሰብን የወቅቱን ሁኔታና ሊደረጉ የሚገባቸውን ነገሮች በሙሉ በሰላም ተዋሕዶ የማስታወቂያ ብሎግ ላይ እንድትከታተሉ እያሳሰብን ብሎጉን ለመክፈትና ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች የመክፈትና የማንበብ እድሉ ያላችሁ ሁሉ በማባዛት ለህዝቡ እንድታሠራጩ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

እግዚአብሔር ለሃይማኖት የቆሙ እውነተኛ አባቶቻችንን ይጠብቅልን !

No comments:

Post a Comment

አስተያየት