Thursday, April 8, 2010

የአስተዳደር ቦርዱ ለአዲስ በቀል እየተዘጋጀ ነው፡፡

ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የትንሳኤ ዋዜማ በተአምረ ማርያም መቅድም ንባባ ምክንያት መምሬ ሞገስ ከቤተ መቅደሱ በኃይለኛ የቁጣ መንፈስ ተሞልተው በመውጣት‹ በሕግ አምላክ ፤ በሕግ አምላክ ፤ ሃይማኖት ነው … › እያሉ እንደ አበደ ሰው ደጋግመው በመጮኸቸው ምክንያት ሕዝበ ክርስቲያኑንና የበዓሉን ታዳሚዎች በሙሉ ማስደንገጣቸውና ማሳዘናቸው ይታወቃል፡፡ በአንጻሩም ደግሞ መልአከ ሣህል አወቀ ትዕግሥት በሞላበትና በተረጋጋ መንፈስ ያደረጉት የማረጋጊያ ንግግርና ሲመሩት የነበረው መንፈሳዊ የማሕሌት አገልግሎት ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማማስመሰል ሊበላሽ የነበረውን በዓል በቦታው እንዲመለስ አድርገውታል፡፡
ይህ መምሬ ሞገስ የፈጠሩት አግባባነት የሌለው ሁካታና ችግር አንድምታው ሁለት ነው፡፡

1ኛ.ተአምር አንባቢ የነበሩትን ካህን ቄስ የማነን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ ለማድረግና ስለጠሏቸው ከአይናቸው ሥር ለማራቅ ሲሆን

2ኛ.በተለመደው የውንጀላ በሕዪርያቸው መልአከ ሣህል አወቀን በሕዝብ ፊት ለማሳጣትና ‹ መምሬ ሞገስ ሃይማኖተኛ፤ ለሃይማኖታቸው የሚሞቱ ጅግና ሰው ናቸው› ተብለው እንዲመሰገኑና ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ቦርድ ላይ ለመክሰስና ቦርዱን እንዲበቀል ለማድረግ ነው፡፡

የቦርዱን ሊቀመንበር ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕዝበ ክርስቲያን ያዩትን ይህንኑ ገሃድ ሐቅ አቶ አበራ ፊጣና ዶክተር ተብዬው እንዲሁም አዲስ የገቡት የቦርድ አባላት በጭፍን አስተሳሰባቸውና ፍትህን ጨርሶ በማየውቅ ዝግ አዕምሮአቸው ፍርድ ለማዛባትና ወገናዊ ሥራ ለመሥራት እንዲሁም ይህቺን አጋጣሚ በመጠቀም መልአከ ሣህል አወቀን ለመበቀል እየተዘጋጁ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መልአከ ሣህል በአስተዳደር ቦርዱ የተጠሉበት ምክንያት ለቦርድ የስህተት ሥራ እንደ መምሬ ሞገስ ተባባሪ ባለመሆናቸውና ወንጌሉን ከነባራዊው እውነታ ጋር አያይዘው በማስተማራቸውና በሕዝብ በመወደዳቸው ምክንያት ነው፡፡

የአስተዳደር ቦርዱ ባለፈው ማክሰኞ ባደረገው ኢመርጀንሲ ስብሰባ ላይ የመመሬ ሞገስን ከባድ ወንጀልና ጥፋት ወደጎን በመተው ‹ጸረ ማርያም ሁሉ› ተብለው በመምሬ ሞገስ ሲሰደቡ የነበሩትን መልአከ ሣህልን ግን ጥፋተኛ በማድረግ ሲወነጅሉ ማምሸታቸው ተረጋግጧል፡፡ በአንጻሩም የቦርድን የበላይነት ሲያሞካሹና ካህናት ቅጥረኞች እንጂ በለመብቶች እንዳልሆኑ ሲፎክሩም ተሰምተዋል፡፡

ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መቀንጠሷ እንደተባለው አዲስ የገቡት የቦርድ አባላት የሚያሰሙት ዛቻና ቀረርቶ የዶክተሩና የአበራ ፊጣ ያደረ ተንኮል ነጸብራቅ በመሆኑ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡

የአስተዳደር ቦርዱ የእነሱው ቢጤ የሆኑትን የመምሬ ሞገስንና የካህን ልጃቸውን ነገረ ሠሪ ወሬ እያደመጠ በአሉባልታ የሚሄድ ስለሆነ ከጥቂት ደጋፊዎቹ በቀር በብዙኃኑ ሕዝብ ዘንድ ሥራው የተጠላና የተነቀፈ ነው፡፡ አሁንም ከስህተቱ አልማር በማለት በክህነት ሥራ ውስጥ ገብቶ ለመዳኘትና ፍርደ ገምድላዊ ውሳኔውን በመልአከ ሣህል ላይ ለመስጠት ለፊታችን እሁድ ለዳግም ትንሣኤ ቀጠሮ የየዙ መሆኑ ቢታወቅም አበራ ፊጣና ዶክተሩ እንዲሁም አዲሶቹ ተመራጮች በማያውቁትና ባልኖሩበት የቤተክርስቲያን ሥርዓት ውስጥ ገብተው አዛዥ ለመሆን ደፍረዋልና እግዚአብሔር እንደሚያሳፍራቸው አያጠራጥርም ፡፡ እንዲህ አይነት የቤተ መቅደስ ችግሮች የሚፈቱት በሊቃነ ጳጳሳት እንጂ በእነ አበራ ፊጣና በእነ ሙሉ ዓለም ሸንጎ አይደለም ፡፡

ለማንኛውም ለእውነትና ለሐቅ የቆማችሁ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት በሙሉ ጉዳዩን ትኩረት በመስጠት እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡

1 comment:

  1. Melake Sahil yewunetegna astemari nachew. Ende kidus Gibrel wunetun kuch new.
    Besachew yemetama nebs yewadekal.
    Sile wunet meskariwa,
    Ehite mariam!

    ReplyDelete

አስተያየት