Tuesday, April 13, 2010

ቦርድና ወታደራዊ መግለጫው !

የውብ እንጀራ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፤
በሰሜን አሜሪካ የቴክሳስና አካባቢዋ የኢህአፓ አባላት ሰብሳቢ
የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ ዋና ጸሐፊ ወዘተ… አቶ አበበ ጤፉ ወታደራዊ መግጫ ሰጡ፡፡

በትንሳኤ ዋዜማ ምሽት በተአምረ ማርያም ምንባብ ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ መምሬ ሞገስ ያሰሙት ጩኸት ሕዝበ ክርስቲያኑን ማስደንገጡና አንዳንዶችንም አዝነው ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ብዙውን ሕዝብ ያሳዘነውንና መምሬ ሞገስንም በምእመናን ዘንድ የበለጠ እንዲጠሉ ያደረጋቸውን ይህን ጉዳይ የአስተዳደር ቦርዱ በተቃራኒ ሁኔታ ተመልክቶታል፡፡

የአስተዳደር ቦርድ ቀኝ ሲሉት ግራ ፤ ሃይማኖት ሲሉት ክህደት ፤ እውነት ሲሉት ውሸት ፤ ፍት ሲሉት ፍርድ ማጣመም ወዘተ… የሚቀናውና አሠራሩ ሁሉ የበጎ ነገር ተቃራኒ በመሆኑ ይህን ጉዳይ በትክክለኛ ዳኝነት ከማየት ይልቅ በተገላቢጦሽ ለማየት ወስኗል፡፡

በእውቀት ማነስና ጠይቆ ባለመረዳት ምክንያት ስህተቱን 100% የፈጸሙት መምሬ ሞገስ ሆነው ሳለ መልአከ ሣህል አወቀን እንደ ጥፋተኛ በመቁጠር ‹ጉዳዩን አጣርተን እርምጃ እንወስድባቸዋለን› በማለት የቦርዱ ጸሐፊ አቶ አበበ ጤፉ በዳግም ትንሳኤ እሁድ ከቅዳሴው በኋላ ለምእመናኑ ያሰሙት እጃዙርና ወታደራዊ መግለጫ ብዙውን ሕዝብ አስቆጥቷል ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ‹እርምጃ› የሚለው ቃል በወታደራዊና በፖለቲካዊ ትግል ውስጥ ያሉ ታጋዮች ቃል እንጂ መንፈሳዊት የሆነችውን የእግዚአብሔርን ቤት አስተዳድራለሁ ከሚል ሰው ጨርሶ የማይጠበቅ ግድፈት ያለበትና ያለቦታው የገባ ቃል በመሆኑ ሊታረም የሚገባው ነው፡፡

በፖለቲካው ትግል የቴክሳስና የአካባቢዋ የኢህአፓ አባላት ሰብሳቢ ነኝ የሚሉት የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጸሐፊ አቶ አበበ ጤፉ የያዙት ሁለት አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ኃላፊነቶች በቋንቋ አጠቃቀምም ረገድ እንኳ ችግር እየፈጠረባቸው እንደመጣ ከወዲሁ መረዳት ይቻላል፡፡

በይግባኝ ክስ ፤ በሂሳብ መዛባት ፤ በሕዝብ ተቃውሞ ወዘተ…መከራውን እያየ ያለው ቦርድ ይህ አልበቃ ብሎት በጭላንጭል ያለውን የቤተክርስቲያኑን ሰላም ጨርሶውኑ ለማጥፋትና ቦታውን ባድማ ለማድረግ ያለ ጥፋታቸው መልአከ ሣህል አወቀን ከሥራ አሰናብታለሁ ብሎ መነሳቱ አርፎ የተቀመጠውን ምእመን ሁሉ በቦርድ ላይ የበለጠ እንዲነሣ የሚያደርግ እኩይ ተግባር እንደሆነ ቦርድ የተረዳው አይመስልም፡፡

እንደ ቦርድ እቅድ ካህንን ከሥራ ማሰናበት ሰላምን የሚያመጣ ሳይሆን ይልቁንም የህዝቡን ቁጣ በይበልጥ አገንፍሎ የቦርድን ስልጣን ወደ መቃብር የሚያወርድ ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ሲከሰት የምናየው ሐቅ ይሆናል፡፡ ‹ቁጭ ብለው የሰቀሉትን በኋላ ቆሞ ለማውረድ ያስቸግራል › እንደሚባለው ቦርድ ያለማስተዋል በስሜት የሚወስናቸው ነገሮች መልሰው እራሱን ችግር ውስጥ እንደሚከተውና መውጫ ቀዳዳ እንደሚያሳጡት በርቀት አልተመለከተውም ፡፡

መጥፎ ሥራ በመሥራት የጠላትንና የተቃዋሚ ቁጥርን እየጨመሩ ከመሄድ ይልቅ ለሰላም ጥረቶችን በማድረግና ሽማግሌች ያቀረቡትን የዕርቅ ሀሳብ መቀበል አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነበር፡፡ እንዲሁም ተቃዋሚዎችን ሳይንቁ ጊዜ ወስዶ በማነጋገር የእርቅና ይቅርታን መድረክ ማመቻቸት የቦርድ ተቀዳሚ ተግባሩ ነበር ፡፡ ግን የደብራችን ቦርድ ለዚህ አዕምሮው ስለተዘጋ ሲበጠብጥና ሲበጠበጥ ይኖራል፡፡

በአንጻሩም ደግሞ አቶ ዮሴፍ ረታ ቀደም ሲል ከነበሩት የቦርድ አባላት ጋር ሆነው በክሱ ዙሪያ በስማቸው ተጽፎ እንዲገባ በፈቀዱት ከክሱ ጋር የማይሄድ መሠረተ ቢስ ጽሑፍ ምክንያት በሕዝብ ዘንድ እንዲጠሉ እንዳደረጋቸውና በእርሱ ምክንያት ብዙም እንደተተቹ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን የቦርድ ሰብሳቢ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ግን ከሌሎቹ የቦርድ አባላት ለየት ባለ መልኩ ለሰላም የሚያደርጉት ጥረት እታየና እየተሰማ በመምጣቱ ይበል የሚያሰኝና የሚያስመሰግናቸው ነው፡፡ ጥሩ የሚሠራ ይመሰገናል ፤ የሚያጠፋና የሚያበላሽ ደግሞ ይወቀሳል፡፡ ከዚህ አንጻር ለደብሩ ሰላም በግላቸው ጥረት እያደረጉ ያሉትን አቶ ዮሴፍ ረታን ሰላም ተዋሕዶ ከልብ እያደነቀች በዚሁ ጉዞዋቸው ከቀጠሉ የሚደርስባቸውን ፈተናና ሊያገኙ የሚችሉትንም ትርፍ ከነባራዊው ሁኔታ ጋር በማገናዝብ በቀጣዩ ዘገባ ሰላም ተዋሕዶ የምትዘግብ መሆኗን ትገልጣለች፡፡

በሌላም በኩል ባለፈው እሁድ የአስተዳደር ቦርዱ ሁለቱን ካህናት ማለት መምሬ ሞገስንና መልአከ ሣህል አወቀን ለየብቻቸው እንዳነጋገረ ለማወቅ ተችሏል፡፡በመጀመሪያ መምሬ ሞገስን ቀጥሎም መልአከ ሣህልን ለብቻቸው ቢያነጋግርም በእለቱ መምሬ ሞገስ በጩኸታቸው ምክንያት ያደረጉት ረብሻ ቀኖና ቤተክርስቲያንን ያልጠበቀ መሆኑን በማመመን ከመቀመጫቸው ተነስተው አንገታቸውን ዝቅ በማድረግ ቦርዱን ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ አልቦ መቅድም ወአልቦ መልክአ ስዕል› ማለት ‹ በፋሲካው ምሽት የተአምረ ማርያምን መቅድምና መልክአ ሥዕል የሚባለው የዜማ ጸሎት በሌሎች በዓሉን በሚመለከቱ ማኅሌታዊ የዜማ ሥርዓቶች እንደሚተካና ይህም በቅዱስ ያሬድ የድጓ መጽሐፍ የተጻፈ መሆኑን መልአከ ሣህል በማስረጃ አቅርበዋል ፡፡ ከሊቀ መንበሩ በስተቀር ሌሎቹ የቦርድ አባላት ማለት አቶ ሙሉአለም ፤ወ/ሮ ሶሎሜ፤አቶ አበራ ፊጣ፤ ዶክተር ግረማና አቶ አበበ ጤፉ አዕምሮአቸውን አንድ ጊዜ ለበቀል ዘግተው የመጡ በመሆናቸው በጥሩ መንፈስ ውስጥ እንዳልነበሩ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን የውይይቱ አጠቃላይ መንፈስ ግን አስደሳች እንዳልነበረም ተረጋጧል፡፡



2 comments:

  1. Melake Sahil yewunetegna astemari nachew. Ende kidus Gibrel wunetun kuch new.
    Besachew yemetama nebs yewadekal.
    Sile wunet meskariwa,
    Ehite mariam!

    ReplyDelete
  2. kies Sidell is a goner.He is histry. When his service is terminated, he will be deported to his Woyane root>

    ReplyDelete

አስተያየት