Friday, July 22, 2011

‹ ማኅበረ ቅዱሳን ይውጣ ! 
ሃይማኖተ አበው ይግባ ! ›


ይህ ከላይ የምናነበውን አፍራሽ መፈክር አንግበው ባይሳካላቸውም ተግባራዊ ለማድረግ ቀን ከሌሊት በትጋት እየደከሙ ያሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊዎች ነን የሚሉት ጥቂት ቅጥረኞችና አጋሮቻቸው ናቸው፡፡ማኅበረ ቅዱሳንንም ለማፍረስ ያልተፈነቀለ ድንጋይ፤ ያልተለመነ ዛር የለም ፡፡በማኅበረ ቅዱሳንም መቃብር ላይ የሃይማኖተ አበውን ባንዲራ ተክሎ ለማውለብለብ ያልታለመ ሕልም፤ ያልተቃዠ ቅዠት የለም ፡፡መታወቅ ያለብት አንድ ሃቅ ግን ማኅበረ ቅዱሳን በእንሽላሊት እግር የሚርስ የእንቧይ ካብ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ወደ ቤተ ክህነቱ ይግባ እየተባለ ዘወትር ከበሮ የሚደለቅለትና የመቀበያ ቄጤማ በማደራጃው የሚታጨድለት ይህ ሃይማኖተ አበው ማነው ? ‹ የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በቤተክርስቲያን ላይ › ከሚለውና የማኅበረ ቅዱሳን ዶክመነቴሽን ክፍል ካሳተመው አዲስ የመረጃ መጽሐፍ ላይ ያገኘነውን ቆንጽለን እንደሚከተለው አቅርበነዋል ፡፡መልካም ንባብ !


ሃይማኖተ አበው ‹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር› በሚለው መጠሪያው ተቋቁሞ የነበረው በ1951 ዓ.ም ነበር፡፡ ማኅበሩ እስከ 1963 ዓ.ም ድረስ ለተቋቋመለት ዓላማው በመጋደል በተለይም በወቅቱ በዩኒቨርሲቲዎችና በኮሌጆች አካባቢ መናፍቃን ያካሂዱት የነበረውን የመናፍቅነት ሤራ በመቃወምና በዚያ አካባቢ ያሉትን ተማሪዎች የሃይማኖት ትምህርት በማስተማር በጥሩ መንገድ መጓዝ ጀምሮ ነበር፡፡


ይህን መልካም ጅምሩን ያዩ የቤተክርስቲያኒቱ ጠላቶች ግን ዝም ብለው አልተመለከቱትም ፡፡እንዴት አድርገው እንደሚያጠምዱት ስልታቸውን ቀይሰው የዓለም ክርስቲያን ተማሪዎች ፌዴሬሽን( World Christian Students Federation ) አባል እንዲሆን አደረጉት፡፡ይህ ማኅበር በዓለም ያሉትን ክርስቲያኖች አንድ ለማድረግ በሚል ሰበብ ዓላማው ተሐድሶ(Reform) ማካሄድ የነበረ ሲሆን ወደ እርሱ እንዲጠጉለትና አባላቱም እንዲበዙለት አንድነትን በልዩነት በሚል መርኅ የሚያባብል ነበር ፡፡ከገቡለት በኋላ ግን ለሁሉም አንድ የሆነ ሁሉን አቀፍ የሆነ የእምነት መግለጫ( Universalism ) ያስፈልጋል ባይ ሆነ፡፡


ከዚህ በኋላ ሃይማኖተ አበው ወደ ስህተት አዘቅት ጭልጥ ብሎ ገባ ፤ በዚሁም መንገድ መንጎድ ጀመረ፡፡ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ‹ ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባል ያልሆነ ለክርስትና እምነት ደንታ ያለው ከሆነ በተባባሪ አባልነት በሃይማኖተ አበው ማኅበር ውስጥ ገብቶ አብሮ ማገልገል ይችላል ፤ የሚል የማሻሻያ አንቀጽን አስገባ ፡፡ በዚህ አንቀጽ መሠረት ብዙ መናፍቃን ተቀላቀሉት፡፡ እነዚህ ከፕሮቴስታንት የመጡ ሃሳባቸውን መስጠትና ሥራቸውን መሥራት ቀጠሉ፡፡ሃይማኖተ አበው በዚህ የስህተት ጎዳና እየቀጠለ በመሄድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ አሉታዊ ትችቶችንና ነቀፋዎችን በተለያዩ መልኮች ማቅረብ ጀመረ፡፡ በዚህም ቅዳሴው ስለረዘመ ይጠር ፡፡ የመዝሙር መሣሪዎች ከከበሮና ከጸናጽል ይልቅ ጊታር፤ ፒያኖና ኦርጋን ይሁኑ ፤ ወዘተ...፡፡ የሚሉ ሃሳቦችን በይፋ መናገር ጀመረ፡፡ከዚያ እየለየለት ሔደ፡፡ ግልጥ የሆነ ፕሮቴስታንታዊ ትምህርቶችን በይፋ ማስተማር ጀመረ፡፡በአጠቃላይ ዓላማውና አሠራሩ ሁሉ ፕሮቴስታነታዊ ሆነ፡፡

በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ሠርጎ በመግባት ብዙ የሰንበት ትቤቶችን ተቆጣጠረ ፤ የሰንበት ት/ቤት አባላትን እያስኮበለለ ለፕሮቴስታንቱ መገበርን ሥራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡በተለይም በድሬዳው ( በ1985-86 ) በሐረር፤ በናዝሬት በአዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ መንበረ ጸባኦት ካቴድራል፤በቅድስት ልደታ ለማርያም በደብረ ብርሃን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ችግር በመፍጠር ብዙዎችን ወደ መናፍቃኑ ሄደው እንዲቀላቀሉና የፕሮቴስታንት ሲሳይ እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል፡፡


ብዙ ጥፋት ካደረሱ በኋላ የካቲት 11 1980 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ በታላቁና በመንፈሳዊው አባት በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሰብሳቢነት ተሰብስቦ በተረጋገጠ ማስረጃ ማኅበሩን ዘጋው፡፡በ1983 ዓም የአብዮት ለውጡን ተከትሎ በድፍረት ዘው ብሎ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ፡፡ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ቆራጥ ውሣኔ የተዘጋ ሆኖ ሳለ ቅዱስ ሲኖዶስ ሳይፈቅድለት ተመልሶ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመግባቱ ጥያቄ ሲጠየቅም ‹ ችግሬን አስተካክያለሁ › በማለት ሲሽሎኮለክና ሲያታልል ቆየ፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ ያወገዘው ማንም ቢሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘቱን እሰካላነሳለት ድረስ ወደ ቤተክርስቲያን ተመልሶ መግባት አይችልም ፡፡አባቶችም ችግሩን እንዳላስተካከለ ሲረዱ በ 1984 ዓም በቅዱስ ሲኖዶስ አሁንም በድጋሚ አውግዘው ለዩት ፡፡ ይህ የተሐድሶ ማኅበር የተለያዩ ደጋፊዎችን ይዞ የአዲስ አበባ አድባራትንና ሰንበት ት/ቤቶችን ሃምሳ በመቶ (50) ያህል ለመቆጣጠር ችሎ ነበር፡፡ ዛሬስ ?


በቅዱስ ሲኖዶስ ሁለት ጊዜ የተወገዘው ይህ ማኅበር አሁንም እንደበፊቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔውን ሳያነሳለት የተለያዩ የተንኮል ዘዴዎችንና በቤተ ክህነት ውስጥ ባሉ አንዳንድ ደጋፊዎቹ አይዞህ ባይነት ተመልሶ ለመግባትና ቤተክርስቲያንን የማድማትና የፕሮቴስታንት ቀለብ የማድረግ ሥራውን ለመቀጠል ጥረት እያደረገ ነው፡፡በቤተ ቤተክህነቱ ልሳን በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የሃይማኖተ አበው ማኅበር ቢሮ ሊሠጠው እንደተፈቀደለትም ተዘግቧል፡፡ በሐምሌ ወር 2000 ዓም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ 50ኛ ዓመት በዓሉን እንዲያከብር አዳራሽ ተፈቅዶለት አባቶች በተገኙበት ተከብሯል፡፡ በዜና ቤተክርስቲያንም የሜዲያ ሽፋን እንዲያገኝም ተደርጓል ፡፡ 


አሁንም በመንፈሳዊ ኮሌጆችና በቤተክርቲያን ዙሪያ ዓይኑን በጨው ታጥቦ ሁለት ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘውን ድርብ ውግዘቱን እንደለበሰ ደቀመዛሙርትንና ምእመናንን ፣ለማጥመድ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል፡፡በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ያወገዘውን ግለሰብም ይሁን ቡድን ከራሱ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውጭ ሌላ ማንኛውም አካል ሊፈታውና ግዝቱን ሊያነሣለት አይችልም፡፡ 


የዚህ መርዘኛ ማኅበር ሽፋንና አይዞህ ባይ የማደራጃ መምሪያው አበጋዞች በመሆናቸው ጥቂት ጊዜ ሊወስድ ይችል ይሆናል እንጂ በአጥፊነት ከጠያቂነት የሚያመልጡ አይሆንም ፡፡ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ቁጣና ተቃውሞ የሌላውን እውነተኛ ሕዝበ ክርስቲያንን ሁሉ ሃይማኖታዊ ስሜት እየጫረ ተቃውሞውን ሀገር አቀፋዊ ያድረገዋል የሚል ከፍተኛ ተስፋ አለ፡፡ ይህም የተጀመረውን የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ሥርዓት የመጠበቅና አጽራረ ቤተክርስቲያንን የመከላከል አቅምን የሚያሳድግ ይሆናል፡፡

7 comments:

  1. what is maheber kidusan? is it a cult, a religion or a maheber?

    ReplyDelete
  2. MK yekenachiwn haymamot endnatsena yitegal! lebetecrstian tifat ketatekut gar demo betekhnet komowal tadiya min yishalal? Amlake Esrael yichin betecrstiyan yitebkln. mkwoch bebzu yifetenalu gn hulum yemimeleket amlak yifredlachew!

    ReplyDelete
  3. አስከዛሬ ድረሰ ለ 19 አመት በጣም ግዙፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረን ማህበር ምንድነው ብለህ የጠየቅከው ከምርሀ አይመስልብህም እንጂ መልስልህ ነበረ ደሞ አጠያየቅህ እራሱ ያሳጣሀል እንዲህ ነው ያልከው ማህበረ ቅዱሳን አምልኮ ነው? ማህበረ ቅዱሳን ሀይማኖት ነው? ማህበረ ቅዱሳን ማህበር ነው? የራስህን ጥያቄ ደግመህ አንብበውና መልሱን ታገኘዋለህ ግን ይሁንና ጥያቄህን በቅንነት ልውሰደውና ልመልስልህ ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ስር ተዋቅሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና ቡራኬ የዛሬ 19 አመት የተመሰረተ የወጣቶች ማህበር ነው። አመሰራረቱ በወቅቱ የነበሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምአራቡ አለም ባህል፣ ሀይማኖትና፣ ፖለቲካ የተጋለጡ ስለነበሩና ወጣቱም ለነዚህ ማንነትን የሚያሳጡ አደጋዎች ግንባር ቀደም ተጠቂ ስለነበረ ይሄንን ትኩስ ሀይል የባእድ አስተሳሰብ ተምሮ ሀገሩን እና ቤተክርስቲያኑን ከመጉዳቱ በፊት ከክህደትና ከአለማዊነት ለመጠበቅ መጽሀፍ ቅዱስን እንዲያውቅ ስርአተ ቤተክርስቲያንን እንዲማር ለማድረግ መሰባሰቢያ ይሆን ዘንድ የተቋቋመ ማህበር ነው። ማህበሩ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ እሰካሁን በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች በሙሉ የጊቢ ጉባያትን እያዘጋጀ ከአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመቀናጀት በሊቃውንተ ቤተክርስቲአን፣ በየሰነበት ት/ቤቱ መምህራንና በራሱ በማህበሩም መምህራንም ጭምር የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ፣ ቀኖና፣...ባጠቃላይ የቤተክርስቲያኗን ትምህርቶች በየተቋማቱ ለሚቆዩባቸው ጊዜያት ያህል አስተማሮ ባባቶች ቡራኬ አስመርቆ ለአገልግሎት የሚያሰማራ ማህበር ነው። ማህበሩ በተጨማሪ ሐመር መጽሄትንና ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣን በማሳተም ወንጌል፣ እምነትንና ስርአትን ዜና ቤተክርሰቲያንን ያሰራጫል ገዳማትን ይረዳል፣ የአብነት መምህራንንና ተማሪዎችን ይደጉማል የገጠር ቤተክርስቲያናትን ይሰራል ያሳድሳል.....ይህ ላለፉት 19 አመት በጽናት ሲፈጸም ያየሁት ምስከርነቴ ነው የማህበሩ ልጆች እኔ ከውጭ ሆኜ የታዘብኩትን የተሳሳትኩትን አርመው የጎደለውን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ ከዚህ በታች ያለው ሊንክ የዛሬ 18 አመት ሐመር መጽሄት መታተም ስትጀምር የወጣውን የማህበሩን መልእክት ያገኙበታል ጥር 1985 ሐመር የመጀመሪያ እትም ቁ.1
    http://hamer.eotc-mkidusan.org/images/stories/pdfs/Y1/1-1.pdf

    ReplyDelete
  4. Response for the message above.......
    Thank you for your kind response and thank you for sharing the link. I have heard about mehabre kidusan before and what an outstanding group it is. But unfortunately, how come they dont do that kind of great work at the city where i live. From our experiance here, they tried to divide our church, they got caught stealing money for our church saying they are helping some gedam in ethiopia, they tried to lecture our 78 year old church father saying he is not following the "rule" that is enforced in ethiopia, they think it is a sin to not cover ur hair when u are inside the church but it is rightous to disrespect elders. And now i hear that the are destroying ethiopia because people and the church is aware of their true colors, which is hunger and thirst for power. So is it mehaber that is trying to be a religion or cult that doesnt know who the living God is? here where i live, people call them "LESEN MEKABEROCH"........remember St. Paul's words.

    so if you know this group well, why do they do such things and why do they live in fear? how come they dont live what they preach? what good would they recieve if they restore gedamat in ethiopia but destroy their church here? what kind of blessing would they recieve if they help students in ethiopia but destroy our teachers here? THEY DONT LOVE THEIR BROTHER WHOM OUR SAVIOUR JESUS CHRIST DIED FOR ON THE CROSS(MANKIND)AND WHOM THEY SEE, BUT THEY CLAIM THAT THEY KNOW AND LOVE OUR ALMIGHTY GOD WHOM THEY HAVE NOT SEEN FOR SURE.

    What do you think wondim/ehet?
    btw i am a female:)

    ReplyDelete
  5. Ehet,
    You said:"From our experiance here, they tried to divide our church, they got caught stealing money for our church saying they are helping some gedam in ethiopia"
    Who caught them, how, when, where? Certainly, if they have been caught, they must have been in prison by now. For those who accuse them falsely, will not sleep to crucify them if these accusations were really true.
    Do you know them? I don't think so. Heed your ears and your heart to the truth before using false accusation to make a false comment.

    ReplyDelete
  6. ሰላም እህቴ የተሰማሽን በውይይት መልክ ማቅረብሽን አደንቃለው ። ተመችቶኝ ቶሎ ስላልተመለስኩኝ ይቅርታ። ሀሳቦችሽን በተመለከተ የመሰለኝን እነሆ የማህበሩ አባል አይደለሁምና ሀሳቡ የግሌ ነው ካጠፋውም እታረማለሁ። ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት የማህበሩ ዋና አላማ ትውልዱ ዘመን እየተከተለ እንዳይጠፋና ከእናት ቤተክርስቲያኑ ተለይቶ የመዳንን መንገድ እንዳይስት ማንነቱንም እንዳያጣ አቅጣጫ አመልካች ከቤተክርስቲያኑ ጋር አቀራራቢ ሆኖ ለማገልገል የተቋቋመ ማህበር ነው። እነሆም እንደታለመው ሲያገለግል 19 አመታት አስቆጠረ። ነገር ግን 19 አመታት እንደው በቀላሉ አልተፈጸሙም በየጊዜው የተለያዩ ፈተናዎችን በማለፍ እንጂ። ችግሮቹን ለመረዳት ሀገራችን በፖለቲካ ትርምስ ወቅት የነበረችበትንና አሁንም ያለችበትን ሁኔታ በደንብ ማየት ይፈልጋል። ችግሮቹ ምንጮቻቸው ብዙ ቢሆንም እኔ የታዩኝን ልጥቀስ፦ 1. የሀገራችን ፖለቲካ የተረጋጋ አለመሆኑን ተከትሎ መንግስታት ሁሉ ክንዳቸውን የሚያሳርፉብን መሆኑ 2. በመንግስት ተጽእኖ ቤተክህነት የሚሾሙ አባቶች ፓትርያርኩን ጨምሮ በዘር፣ በሙስናና፣ በተበላሸ አሰራር የተዘፈቁ መሆናቸው 3. ቤተክህነት ዘመናዊ አሰራር የማይከተል መሆኑ የተቀናጀ የስብከት ዘዴ በመከተልም ምእመኑ በሁሉም አካባቢ ቃለ እግዚአብሄር እኩል እንዲደርሰው ያልተደረገ መሆኑ 4. ምእመኑም በሀገር ቤትም ሆነ በውጪ የምንገኝ /በተለይ በውጪ/ የፖለቲካ አመለካከታችንን እንዳለ ይዘን በዛ መሰረትም ቤተክርስቲያንዋን መምራት መፈለጋችን እና…..በሌሎችም በርካታ ችግሮች ቤተክርስቲያናችን የታጠረች መሆንዋ በተለያዩ ቦታዎች የምናያቸው ችግሮች የእነዚህ መነሻ ምክንያቶች ውጤቶች እየሆኑ ይታያሉ። ጥያቄዎችሽን ለመመለስ ለምን እንደሀገር ቤት እዚህም አይሰሩም ላልሺው የሀገር ቤትንና የውጭሀገርን ቤተክርስቲያናትንና ምእመኑን ማወዳደር ያስፈልጋል ሀገር ቤት የማህበረ ቅዱሳን አገልጋዮች ማለት የሁሉም ሰው ልጆች የሁሉም ሰው እህት ወንድሞች ማለት ናቸው። እነማን እነደሆኑ የሚታወቁ ማህበሩ እየታየ ተፈጥሮ እየታየ ያደገ የሚታወቅ የሚሰራው የሚታይ በሰፊው ተቀባይነት ያለው ማህበር ነው። በምእራቡ አለም ግን በተለይ አቡነ ጳውሎስ ስልጣን ከያዙ በሁዋላ በተፈጠረው ያባቶች ልዩነት ሳቢያ ከሀገር ውጪ የወጡት አባቶች እልህኞች በመሆን በሀገር ቤቷ ቤተክርስቲያን ስርአት ሳይሆን የፈለጉትን ስርአት መከተል በመጀመራቸው ለምሳሌ፦በኦርጋን መዘመርን መፍቀድ፣ ለብዙ ስርአተ ቤተክርስቲያናት ግድየለሽ መሆንና ፣ አገር ቤት እያሉ የእምነት ችግር የነበረባቸው አገልጋዮችን ያለ ስርአተ ቤተክርስቲያን በማን አለብኝነት ወደ አገልግሎት መመለስ …...የሀሳብ ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት የሆኑ ሲሆን እንደሚታወቀው እዚህ ምእራቡ አለም ያለው ህዝብ ባብዛኛው የኢህአዴግ ተቃዋሚ በመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ ከቆመለት ስርአተ ቤተክርስቲያንን ጠብቆ የማስጠበቅ አላማ አንጻር በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ስር ባሉቱ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ሚያገለግል /ሚደግፍ/ በመሆኑ ይሄን ሀሳብ በማይደግፉ ሰዎች ዘንድ የመንግስትና ያቡነ ጳውሎስ ታማኝ ተደርጎ ስለታየ ፀቡን አጠነከረውና ተቀባይ እንደሀገር ቤቱ ሊያገኙ ስላልቻሉ እንደሀገር ቤቱ ሲሰሩ ላይታዩ ይችላሉ፡ ይሁንና ሁኔታው በየከተማው ባሉ ልጆች አክቲቪቲ ቢወሰንም በዚህ ሁሉ ትንቅንቅ ውስጥ ሆነውም የተወሰነ እየሰሩ ይገኛሉ ። ሌላው እኔ እራሴ ሁሌ የሚቆጨኝ አባቶች በመለያየታቸው ምክንያት ሌላ አጀንዳ ያላቸው ፖለቲከኞችና መናፍቃን አገር ቤት ያጧትን ቤተክርስቲያን እዚህ ሲሽለኮለኩባት ሳይ ያቃጥለኛል። ይህች ቤተክርስቲያን እኮ በነብያት ተተንብያ፣ በጌታ ደም ተመስርታ፣ በሐዋርያት ሰማእትነት የፀናች የሰማየ ደጅ የተባለች የራሷ መታወቂያ የራሷህግ ያላት ጥንታዊት ብሄራዊትና አለማቀፋዊት ቤተክርስቲያን ነች። በህጓ መተዳደር የማይፈልጉ ሰዎች ለምን በስሟ ይጠቀማሉ፣ ከክርስትና መሰረታዊ አላማ አንጻር ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ቀጥሎም የሐዋርያት እና አሁንም በሐዋርያት እግር የተተኩ የካህናት ስትሆን በካህናት የበላይነት፣ ባለቤትነትና አባትነት መተዳደር ሲገባት አባቶች እንደሌሏት ስልጣንዋ በጥቅመኞች ተነጥቆ ለምን ያለ ህጓ አለማውያን እራሳቸው ተመራርጠው ባወጡት ህግ ፈላጭ ቆራጭ የሚሆኑባት። እንደሚታወቀው በቤተክርስቲያን ፍትሀ ነገስት የሚባል የስርአት መጽሀፍ አለ ሁለት ክፍል ሲኖረው ፍትህ መንፈሳዊና ፍትህ ስጋዊ ይባላሉ በፍትህ መንፈሳዊው ቤተክርስቲያን ስትመራ/ቃለ ዓዋዲ/ በፍትህ ስጋዊው ደግሞ ሀገር ትተዳደራለች ለምሳሌ በሀይለ ስላሴ ጊዜ የሀገራችን ህገ መንግስት ከፍትህ ስጋዊ የተውጣጣ እንደነበር ሰምቻለው/ እስካሁን ያሉ መንግስታትም አንዳንድ ነገር ወስደው የሚጠቀሙ ይመስለኛል/ ታዲያ እንዲህ ለሀገሪቱ እንኳ መተዳደሪያ ህግ የሰጠች ቤተክርስቲያን እንዴት በራሷ ህግ እንዳትተዳደር ትደረጋለች። እንዴት ጳጳሳትና ሲኖዶስ ያላት ቤተክርስቲያን በአቶዎችና እራሳቸው በጻፉት ህግ ትመራለች። ከጳጳሳትና ከሲኖዶስ የተለየች ቤተክርስቲያን እንዴት በጳጳሳት ብቻ የሚፈጸሙ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያናትን ለምሳሌ ካህናትን መሾም ቤተክርስቲያናትን መባረክ…..መፈጸም ትችላለች እስከመቼስ ለጥቅምና አማራጭ ያጡ ካህናትን በገንዘብ በመቅጠርና ሲበቋቸውም በየጊዜው እንደሚታየውም በፈለጉበት ሰአት እንደ ውሻ አባቶቻችንን ገፍትሮ ማስወጣት የመቻል ትምክህት ይዘለቃል ። እነዚህና የመሳሰሉት ሁኔታዎች እንደቤተክርስቲያን ልጅነቴ ሁሉም የምጨነቅባቸው ጉዳዮች ሲሆኑ ይሄንን ማስተካከልም የሁሉም ከቤተክርስቲያን መንፈሳዊ በረከት ብቻ የሚፈልጉ የቤተክርስቲያን ልጆች እዳ ነው። እነዚህና የመሳሰሉት ኮንሰርኖች ናቸው እንግዲህ አንቺ የታዘብሻቸውን ነገሮች ያስከተሉት። to be continued

    ReplyDelete
  7. ሰላም እህቴ........እነዚህና የመሳሰሉት ኮንሰርኖች ናቸው እንግዲህ አንቺ የታዘብሻቸውን ነገሮች ያስከተሉት። እንግዲህ የችግሩን ስፋት ተመልከቺና በሎካል ሳትወስኚው በጥቅሉ በመመልከት ለመፍረድ ሞክሪ ምክንያቱም ማህበሩ ቤተክርስቲያንን እንደተቋም እንዳለች ማቆየት ተቃዋሚዎች ደግሞ እምነትንና ስርአትን መሸራረፍና በሁዋላም በሂደት ማንነታችንን ማጥፋት በመሆኑ አላማቸው። ብር ስለመብላት ላልሺው የተፈጠረ አለመግባባት ይኖር ይሆናል ግን ማህበረ ቅዱሳንን በብር መስረቅ ለመጠርጠር የ19 አመት ሪከርዱ አያግዝም እና ይሄንን እንጃ አንዳንድ ሰው ፎቃቸውን መስሪያ አደረጉት ይላል ግን ይሄም አሉባልታ ነው ብዬ ባልፍ ይሻለኛል ልጆቹ አብዛኛዎቹ የከፍተኛ ትምህርት ምሩቃን ሲሆኑ ነጋ ጠባ ሳይሉ ሌት ተቀን በጉልበት፣ በጊዜ፣ በእውቀት/ባስተዳደር፣ በምህንድስና፣ በጤና፣ በመምህርነት፣በእርሻ ባለሙያነት ነጻ አገልግሎት በመስጠት….በገንዘባቸውም አስራት በኩራት በማውጣት ከልብ ገዳማትን፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችን፣ አባቶችንና ቤተክርስያናችንን እየረዱ የኖሩና የሚኖሩም ግዙፍ ባለ ራእይ ማህበርና ልጆች በመሆናቸው ባልተረጋገጠ ነገር ለመጠርጠር ያስቸግራል። ሌላው ጸጉርን መሸፈን በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ያለ ቅዱስ ጳውሎስ ያዘዘው የቤተክርስቲያናችንም ስርአት በመሆኑ ከሌላ ነገር ጋር ማነፃፀሪያ ተደርጎ መቅረብ የለበትም። ስርአተ ቤተክርስቲያንም መጠበቅ አለበት አባትም መከበር አለባቸው/ ምንም አባት ቢሆኑ ያጠፉት የቤተክርስቲያን ስርአት ካለ መታረም እንደሚገባቸው እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ማንም ይሁን ማን ከስርአተ ቤተክርስቲያን በታች ስለሆነ ማለቴ ነው/። እንዲህ ከማድረግ እንዲህ ያለውን የቤተክርስቲያን ስርአት ማፍረስ ይሻላል የምትል የአንዳንድ ሰባኪዎችን ሀሳብ ትመስላለችና ስርአተ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ምንም ኤክስኪውዝ መቅረብ የለበትም ስርአትን ብናከብር የምንጠቀም እኛው ነንና። አባቶች ስርአተ ቤተክርስቲያን የጠበቃትን እርሷም እንዲሁ በጸጋ ትጠብቀዋለች እንዲሉ። እንዲሁም ስርአት ለእምነት እንደ አጥር እንደ ቅጥር ነው ብለው ይላሉ ለምሳሌ ሌባ በደንብ የታጠረን አጥር አልፎ ቤቱን እንደማይዘርፍ ሁሉ ስርአተ ቤተክርስቲያንን የምታከብር የምእመን ልብም እምነቷን አክብራ ትይዛለች ይላሉ። በተረፈ ማህበር ቅዱሳንን ጠልተው ስሙን የሚያጠፉት 1. በአስተዳደር ከቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ሰዎች ሲሆኑ እኒህ ሰዎች ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶቸ የቤተክርስቲያን አደጋዎች ስለሆኑ የቤተክርስቲያን ክብር የሚያስጨንቀው ሁሉ እነሱን ከመተባበር መቆጠብና እንዲሁም ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ ለመፈለግ መተባበር ይገባል አለበለዚያ ለሚቀጥለው ትውልድ ስርአተ ቤተክርስቲያን፣ ካህን፣ ሲኖዶስ የሚንቅ ኦርቶዶክስነትን እያስረከብን መሆናችን መታወቅ፡አለበት።2. የምንፍቅና ችግር ያለባቸው ቤተክርስቲያንዋ እንድትታደስ የሚፈልጉ ክፍሎች ሲሆኑ እነዚህ ደግሞ የከፉ የጥፋት መልእክተኞች መሆናቸውን ማህበሩ በተጨባጭ ስሚያውቅ እየተከታተለ ስራቸውን የሚየከሽፍ በመሆኑ ቀንደኞቹ የማህበሩ ስም አጥፊዎች በመሆናቸው እነዚህንም ከመስማትና የቤተክርስቲያን ጠላቶችን ከመተባበር መጠንቀቅ ጥሩ ነው። እንደምሰማው አገር ቤትም እየረበሹ ላልሺው ስህተት እንደሆነ እነግርሻለሁኝ ለምን መሰለሽ ባሁኑ ሰአት ተሀድሶ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከፍቶ በመንቀሳቀስ ላይ ያለበት ጊዜ ሲሆን ማህበሩ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ወጣቱ ከምንጊዜውም በላይ በህብረት ተነስቶ ተሀድሶዎችን እየተከላከለ ባለበት ሰአት ህዝቡን ለማዘናጋት የሚወሩ ወሬዎች ናቸው። ለራስሽ ለማረጋገጥ አገርቤት ደውለሽ ወይም በሌላ መንገድ ቀረብ ካሉ አገልጋዮች ማረጋገጥ ትችያለሽ ግብ ግቡ ሀይማኖታችንን በመጠበቅና በተሀድሶነት፣ ስርአትን በመጠበቅና በግል ጥቅም መካከል ያለ ችግር ነው። በአጠቃላይ ምንም እንኳን ሰዎች ናቸውና የአሰራር ድክመት ቢኖርባቸውም ለቤተክርስቲያናቸው ለስርአታቸው የሚቆረቆሩ በመሆናቸው ከሁሉም በላይ ደግሞ ቤተክርስቲያናችን እንደተረከብናት ለዘላለም ትኑር ትቀጥል ስለሚሉ ከማንም ይሻላሉ ባይ ነኝ። ከዚህ ያጠረ ማድረግ ባለመቻሌ ቅርታ። ሰላም ሁኚ ወንድምሽ።

    ReplyDelete

አስተያየት