Friday, October 15, 2010



የልጄ ተንኮል ቢያናድደኝም መልሶ ደግሞ አሳቀኝ !
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው ሲል ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ መዝ ፡፡የሰው ልጆችም ይህንን አምላካዊ ቃል ትርጉሙን በትክክል የሚረዱት ባልና ሚስት ሆነው በሚኖሩበት ቤታቸው ውሰጥ ከአብራካቸው የወጣ ህጻን ልጅ ሲያገኙ ነው፡፡ በምጥና በጋር ልጇን ለመወለድ የቀረበች ነፈሰ ጡር ሴት ልጇን በወለደች ጊዜ ምጥና ጋሯን በመርሳት በደስታ ትዋጣለች፡፡ አባትም እንደዚሁ፡፡
የተወለዱ ልጆች ከእንጭጭነት አልፈው ሲፋፉና ድክ ድክ እያሉ ሲወድቁ ሲነሱ ማየት ትልቅ የኅሊና ደስታን ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ ልጆች በሁለትና በሶስት ዐመት እድሜ ላይ ሲደርሱ በአእምሮ፤ በአካልና በቋንቋ እድገት ቢያሳዩም ለጫወታ እያሉ የሚሠሯቸው አንዳንድ ሥራዎቻቸው የሚያስገረሙና የሚያስቁ ናቸው፡፡ በዚህ እድሜ ደግሞ የወላጆች ጥብቅ ክትትልም እጅጉን ያስፈልጋል፡፡ ልጆች በተለይ ዘወትር ከሚጫወቱበት የቤት ውስጥ ሥፍራ ሰወር ሲሉና ድምጻቸው ሲጠፋ በመጠራጠር የት እንዳሉና ምን እየሠሩ እንደሆነ በቅርብ መከታተል ተገቢ ነው፡፡ ዛሬ ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነን < Family Fun > በመባል በእንግሊዘኛ እየታተመ በሚወጣው የቤተሰብ መጽሔት ላይ ያገኘው የአንድ ቤተ ሰብ ገጠመኝ ነው፡፡ ድርጊቱ እንዲህ ነው፡፡

የሦስት ዓመት ልጅ ያላቸው ባልና ሚስት ልጁን እራሱን ችሎ እንዲጸዳዳ በተላያየ ዘዴ ያስተምሩታል (patty training) ፡፡ ለዚያ ተብሎ የተዘጋጀውን የዲቪዲ ካሴት እየከፈቱም ያሳዩታል፡፡ ልጁ ግን ያን በቶሎ ለመቀበል ይከብደዋል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን  LUSTRINR WHITENING ; በመባል የሚታወቀውን የአፍ መጉመጥመጫ ሳሙናው ያለቀና በቆሻሻ መጣያ ላስቲክ ውስጥ የተጣለ ባለ ነጭ ቀለም መካከላኛ የላስቲክ ብልቃት ያገኝና ያን አውጥቶ ወላጆቹ ሳያዩት ወደ መኝታ ክፍሉ ይገባል፡፡ሲጫወትበት ቆይቶ ፒፒው (ሽንቱ) ይመጣና ሱሪውንና ዳያፐሩን አውልቆ ሲጫወትበት በቆየበት የጥርስ ማጽጃ ሳሙና ፕላስቲክ ብልቃጥ ውስጥ ይሸናና ክድን አድርጎ በመውሰድ ወላጆቹ መታጠቢያ ቤት ቀድሞ ባየበት ቦታ ላይ ያስቀምጠውና ወደ ጫወታው ይመለሳል፡፡
በማግስቱ ሥራ ለመሔድ ከእንቅልፍ የተነሣ አባት የ LUSTRINR WHITENING አፍ መጉመጥመጫውን እቃ ሲያይ ባለቀው ምትክ ባለቤቱ አዲስ የተካች መስሎት ባለማስተዋል ወደ አፉ አስጠግቶ ያንደቀድቀዋል፡፡ወደ አፉ የገባው ጥርስ ሳሙና አለመሆኑን በሽታው የተረዳው አባት ደንግጦ በኃይለኛ ቋቅታ የተጎነጨውን ሽንት በመታጠቢያ ሲንኩ ላይ ይተፋዋል፡፡ ቋቅታውን ሰምታ ያመውና ያስመለሰው መስሏት ሚስት በፍጥነት ወደ መታጠቢያ ቤት ተመጣለች፡፡ ባል ስላጋጠመው ሁኔታ ያስረዳትና ማን ይህን እንዳደረገ ይጠይቃታል፡፡ ሚስትም የምታውቀው ነገር እንደሌለ በማስረዳት ይህን ተንኮል ማን እንደፈጠመው በመገረም የሦስት አመቱን ሕጻን ከእንቅልፉ ቀስቅሰው ይጠይቁታል፡፡ልጁም እርሱ እዳደረገው በግልጽ ይነግራቸዋል፡፡ አባት ይህ አግባብ አለመሆኑንና ሁለተኛ እንዲህ አይነቱን ድርጊት እንዳይደግም ያስጠነቅቀዋል፡፡ ልጁም በአጭር ቃል ሁለተኛ እንደሱ አላደርግም ፤ እናንተም እዚያ ውስጥ እንደማይሸና አልነገራችሁኝም አላቸው፡፡ ይህን ጊዜ ባልና ሚስት በልጁ አነጋገር ተደንቀው ሆዳቸው እስኪቆስል ሣቁ ፡፡ ልጁም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዳይፕሩን በመጣል አራሱን ችሎ በአግባቡ የሚጸዳዳ ሆነ ፡፡የአባትም ድንገተኛ ንዴት ወደ መገረምና ሣቅ ተቀየረ፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት