በሦስት ቡድን መከፋፈሉ የሚነገርለት የአስተዳደር ቦርድ ከመካካሉ የወላጅ ኮሚቴ አባላትን ደጋፊ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የሂሳብ ሹሙና የገንዘብ ያዡ ቡድን በገንዘብ ቅሌት ውስጥ መግባቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጡ ፡፡
የገንዘብ ያዡና የሂሳብ ሹሙ ፍቅር በቤተ ክርስቲያኑ ገንዘብ የጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ በመሆኑ የቤተክርስቲያኑዋን ገንዘብ ያለ አስተዳደር ቦርዱ ፈቃድና ውሳኔ እያወጡ ለግላቸው እየተጠቀሙበት መልስው እንደሚያስገቡ በቦርድ ተቆጣጣሪና በደብሩ ተቀጣሪ የሂሳብ ሠራተኛ የተደረሰበት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል፡፡ የቤተክርስቲያኑዋ ገቢ ከእለት ወደ እለት እየቀነሰ መምጣቱን ሳያሰልሱ የሚናገሩት ገንዘብ ያዢና ሂሳብ ሹም በምን ዓይነት መንገድ ገንዘቡን አውጥተው እንደተቀሙበት ገና የምርመራው ውጤት ይፋ ያልወጣው ሲሆን አሥር ሺህ ዶላር( $10,000 ) ግን ሳይታወቅ ገብቶ መገኘቱንና የተለመደውን የሂሳብ አሠራር መንገድ አለመከተሉን የሂሳብ ሠራተኛው ቀድመው ያሳወቁ ቢሆንም ሂሳብ ሹሙና ገንዝብ ያዡ ግን ጉዳዩን አፍነው መሰንበታቸው ታውቆአል፡፡ ይሁን እንጂ ከሦስቱ ቡድን የአንደኛው ወገን መሆናቸው የሚነገርላቸው ተቆጣጣሪዋ ለጉዳዩ ትኩረት በመሥጠት ምርመራውን አድርገው እንደደረሱበትና አስቸÎይ የቦርድ አባላት ስብሰባ ላለፈው እሁድ ማታ እንዲጠራ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሎአል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሂሳብ ሹሙና የገንዘብ ያዡ በምርጫው ዙሪያ የሚስቶቻቸው ጓደኛ የሆኑትንና ቀደም ሲል በወላጅ ኮሚቴ ውስጥ ሰብሳቢ ሆነው ይሠሩ የነበሩትንና አንዴ ንግግር ከጀመሩ ማቆሚያ የሌላቸውን ወይዘሮ ሶሎሜን የቦርዱ ጸሐፊ አድርገው ለማስመረጥና በቤተክርስቲያኑዋ ገንዘብ ላይ ያላቸውን ሥውር ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እየታገሉ እንደሆነም ለማወቅ ተችሎአል፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት