Tuesday, October 27, 2009

ትኩረት ይሠጥበት !


በአስተዳደር ቦርዱ እልከኝነትና አምባ ገነንነት ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተደቀነው አደጋ በቀላሉና በዝምታ የሚታይ ጉዳይ አይደለም' እንደኔ ምኞትና ፍላጎት ቢሆን ጉዳዩ ፍርድ ቤት ባይደርስ ጥሩ ነበር' ነገር ግን አስተዳደሩ ወገናዊ ሆኖ አንዱን ወገን የሚሰማና ሌላውን ወገን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት የሚደክምና ጽንፈኝነት የተጠናወተው ስለሆነ መፍትሔው የግድ ይህን ክፉ ምግባሩን በሕግ አስከባሪዎች በኩል እንዲያቆም ማድረግ ብቻ ነበር 'ይህም እየተደረገ ነው'

የሚገርመኝ ነገር የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ምእመናን መሥራቾቹንና አዲሱን ትውልድ ጨምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተፈቃቅረንና ተከባብረን የምንኖር አንድ ቤተሰብ ነበርን'አለመግባባት በመሃላችን ቢከሰትም እንኩዋን ሊጊዜው ተ¯¨ንና ተተራምሰን ሁሉን በመተው ለጋራ አገልግሎት ተቻችለን በሰላም እንኖር ነበር'ቀደም ሲልም በተለያዩ ጊዜያት የነበሩት የአስተዳደር ቦርድ አባላትም ቢሆኑ ጥሩ የማስተዳደር ችሎታ ነበራቸው ባይባልም እንደነዚህ ግን መረን የለቀቁና አይናውጣዎች አልነበሩም'

ለመሆኑ እንዲህ ለሰው ክብር የለሾች እንዲሆኑና ከልማት ይልቅ ለጥፋት እንዲሰለፉ ያደረጋቸው ምንድነው ብዬ በማገኘው የጨዋታ አጋጣሚ ሁሉ አንዳንዶችን ስጠይቅ በአብዛኛው የሰጡኝ መልስ ግን ተቀራራቢ ነበር'ይኸውም ‹ ምንነቱ የማይታወቅና ባለጌ ሰው በመካከላቸው በመግባቱ ነው ›የሚል ነበር'.

ይህ ሰው ደህናዎቹንና ጥሩዎቹን ሰዎች ሁሉ በአንድ ጊዜ በተንኮልና በነገር አባልጎ መረን ለቀቃቸው 'ተው ሲባል የማይሰማ ፤ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ፤ እኔን ብቻ ስሙኝ የሚል በመሆኑ በጽኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመኖር ወደ አለመኖር ለማድረስ ያቅሙን ያህል እየጣረ ነው'ቤተክርስቲያኒቱ ብትፈርስ ባትፈርስ ፤ ሕዝቡ ቢበተን ባይበተን ለእርሱ ጉዳዩ አይደለም'ይህንንም ሳያስበው ለሰው በጨዋታ መልክ ተናግሮታል ' በሃይማኖቱም ቢሆን ከነባለቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ሳይሆን ሌላ ነው' ሌላ ነው ስል ፤ ምንድነው ግን አትበሉኝ' ሰውየው ሃይማኖቱም ሆነ እምነቱ ሆዱና ጥቅሙ ብቻ ነው'ለዚህ በቅርብ የሚያውቁትና ገና ዳለስ ሲመጣ ጀምሮ በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ሊመሰክሩ የሚችሉት ሃቅ ነው'.

ገና ወደ ቦርድ ሲገባ ይዞ የገባው ከውጭ ሆነው ፍትፍት የሚያጎረሱትንና ጠጅ የሚያጠጡትን አፍረራሽ ተልኮ ያላቸውን የነቡክሪን እኩይ ሃሳብ ነው'ሴት የላካው ሞት አይፈራም እንዲሉ እረሱዋም ከደጅ ሆና የምታሰማው ቀረርቶና ፉከራ ሁሉ ይህንኑ የሚያሳይ ነው'

ሰውዬው ሌሎቹን የቦርድ አባላት እንዳልተማሩ ወይም ምንም እንደማያውቁ ፤ በመካከላቸውም ከእርሱና ከአቶ አበራ ፊጣ በቀር የተሻለ ሃሳብ ማውጣት የማይችሉ መሃይምናን እንደሆኑ አድርጎ የሚመለከትና የሚንቅ ነው' ይህ ጉዳይ ቀሪዎቹን የቦርድ አባላትን የሚመለከት ሰለሆነ እነርሱ ይጨነቁበት '

ለመሆኑ ይህ ዶክተር ነኝ ተብዬ ሰው በዚች ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው የወደፊት ምኞትና ዓላማ ምንድነው

ይህንን ግን ልብ ያለው ሁሉ ልብ ይበል !

የዶክተር ነኝ ተብዬው ሰው ዋና ዓላማማ

1.‹ አላዋቂና አØመ ቢሰ በመባል ዘወትር በህዝብ ዘንድ የሚተቸውንና የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ለግሉ ተጠቅሞ ሂሳቡን ሳወራርድ የሰነድ ማስረጃ በዶክተሩ ተግኝቶበታል የሚባለውንና ቤተ ክርስቲያኑዋን በአመራር ችሎታ እጦት ምክንያት እዚህ ማጥ ውስጥ የከተታትን የቦረዱን ሊቀመንበር በማስፈራት ከሥልጣን አውርዶ በመሪነት ቦታ ላይ መቀመጥ የዶክተሩ ተቀዳሚ አላማ ነው' › ይህን ለማሳካት ደግሞ ሰብሳቢው በሌለበት ሌሎቹን የቦርድ አባላት ለብቻ በመሰብሰብ አልተሳካም እንጂ የመፈንቅለ ሥልጣን አይነት ሙከራዎችን ዶል'

2. ሰውዬው ውስጣዊ የሥልጣን ፍላጎቱ በግልጽ ገንፍሎ ወጥቶአል ' ‹ እኔ ዶክተሩ እያለሁ እንዴት ከእኔ በታች የሆነ አላዋቂ ሰው ከእኔ በላይ ሆኖ ይመራኛል› በሚል የትዕቢት መንፈስ ስሜቱ እየታመሰ ስለሆነ ፤ ወይ ሊቀመንበር መሆን አለበት፤ አሊያም ይህ ካልተሳካ ደግሞ እውነት እንጂ ውሸት የማይስማማትን ቤተ ክርስቲያን ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን በሕግ ፊት አቁሞ ሀሰተኛ አድርገው ለማሳጣትና ካልሆንም አፈራርሶና አበለሻሽቶ ለመሄድ ነው' ለዚህም የሕግ የበላይነት ከምንም በላይ የነገሠበትን የአሜሪካንን ፍርድ ቤት በተራ የዱርዬ ሥራና የተጭበረበረ ሰነድ እንዲሁም ክህደት ለማታለል በመሪነት እየሞከረ ነው' ታዲያ ይህ ሰው በእውነት ተምሮአል ወይ የሚያሰኝ ነው' ዶክትሬቱስ የተገኘው በምንድን ነው ? የሚለውን ጥያቄ በሰው ሁሉ ዘንድ እየፈጠረ ነው ' ዶክተሬቱን በውሸትና በክደት ከሆነ የሠራው ‹ይገባዋል› ብለናል '

በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ከበሬታ የነበራቸውን እንደነ አቶ ሠይፉ ይገዙንና ፣ እነአቶ ዳኜን የሌሎችንም ትልልቅ ሰዎች አንገት ያስደፋና በብልግናው ያሰፈረ ይህ ሰው ለቤተክስቲያኑዋ ዋና ጠንቅና ወደፊትም ለሚገጥማት ችግር ሁሉ መሪና ዋና ተዋናይ ሆኖ እየሠራ ስለሆነ ህዝበ ክርስቲያኑ በአንክሮ እንዲረዳውና እንዲያጤነው ያስፍልጋል ' '

ወደፊት ይህን ሰው ሳታውቁት ቦርድ የከተታችሁት ሰዎች ይህንን ሙሾ ታወርዳላችሁ !

እኔው በገዛ እጄ የጫርኩት እረመጥ

መች ይፈËž ነበር አርፌ ብቀመጥ '

ኸረ የሕግ ያለህ እያላችሁ የምትጮሁ ሰዎች ደግሞ እንዲህ እያላችሁ ትተርታላችሁ !

በፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ

አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ'

No comments:

Post a Comment

አስተያየት