በዚህ ርዕስ የቀረበውን ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ሁሉ ለቀልድ ወይም በሳቅ ለማዝናናት እንደተዘጋጀ ብቻ አደርጋቸው እንዳትቆጥሩት በቅድያ አሳስባለሁ፡፡ ክርክሩ የተካካሄደው በእውነትና በአምባገነኖቹ የአስተዳደር ቦርድ አባለት መካከል ነው፡፡
‹ትዝብት› ክርክር በሚል ዓምድ ሥር የያዘችው መልዕክት በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲን የአስተዳደር ወንበር ላይ የተቀመጡ እያንዳንዳቸው የቦርድ አባላት በእውነት ላይ ያላቸውን ጥላቻና የተሳሳተ አመለካከት በአጭሩ የሚስገነዝብ ነው ፡፡ ክርክር በሚል ርዕስ የቀረበበትም ምክንያት እውነት ህልውናዋን ለማሳወቅ ያደረገቸውን ጥረትና ከአስተዳደሩ ጋር የገጠማትን ሙግት ስለሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ‹ትዝብትም› የታካሄደውን ክርክር በመሃል ተገኝታ በማድመጥ ብዙ ነገር ታዝባለች ፡፡ እንድናነብ የምትጋብዘንም እርሱዋ ናት፡፡ እንግዲህ በማስተዋል አንቡቡት፡፡
እውነት- ብዙ ጌዜ ወደ እኔ መጥታችው እንድንወያይ ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጌ ባለመምጣታችሁ ዛሬ እናንተ ካላችሁበት ቦታ ድረስ መጥቼ እዳነጋግራችሁ ተገድጃለሁ ፡፡
የቦርድ ሊቀ መንበር - ማን ልበል አንቺን
እውነት - በእርግጥ አታውቁኝም ! ስሜ ግን ‹እውነት› ይባላል፡፡
የቦርድ ሊቀ መንበር - ኮስተር ብለው ‹ታዲ ምን ፈለግሽ እዚህ› ፡፡
እውነት - ህልውናዬን በተመለከተ ከእናንተ ከቦርድ አባላቱ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፡፡
የቦርድ ሊቀ መንበር - ይቅርታ አድርጊልኝና እኛ ከአንቺ ጋር ለመነጋገር ፈቀደኞችም በአጠቃላይ ደስተኞችም አይደለንም ፡፡ ብንነጋገርም መግባባት የምንችል አይመስለኝም ፡፡
እውነት - ከተነጋገርን እንዴት ነው የማንግባበው ?
የቦርድ ሊቀ መንበር - አንግባባማ ! አንቺ የካሳሾቹ ደጋፊ እንደሆንሽ እናውቃለን ፡፡ ስለዚህ ክሱ እስካላቆመ ድረስ በምንም ጉዳይ ላይ መነጋገር አንችልም ፡፡በቃ አለቀ፡፡
የቦርድ ሕዝብ ግንኙነት - እስቲ መጀመሪያ ለምን እንደመጣች ምክንያቱን ከእረሱዋ እንስማና ከዚያ በâላ መልስ መስጠት ካስፈለገ መልስ ልንሰጥበት እንችላለን፡፡
የቦርድ ሊቀመንበር - Ok ! ለመሆኑ ጉዳይሽ ምንድነው ፡፡በንዴት መንፈስ
እውነት - እኔ ዛሬ እዚህ የመጣሁት ፤ የምትሰሙኝ ከሆነ የደረሰብኝን በደል አቤት ለማለት ነው ፡፡
የቦርድ ሊቀመንበር - አቤት ባዩ በዛ እኮ ባከችሁ ! የምን አቤቱታ ነው ያንቺ ደግሞ ? አሉ በምጸት ቃል፡፡
ትዝብት -
እዚህ ላይ ሊቀመንበሩ በደንበኞች አገልግሎት (customer service) ዜሮ መሆናቻውንና ስብሰባን ገና ሳይጀመር ኃይለ ቃል በመናገር ለመዝጋት መሞከራቸውን ታዘብኩ፡፡ ይህ ደግሞ የአንድን ሰብሳቢ quality ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱና ዋናው ነው፡፡
እውነት - ከቤተ መቅደሱ ጀምሮ በዚህ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ክፍሎች በሙሉ የእኔ ቤቶች ናቸው፡፡ እንደ ሕጉማ ቢሆን ኑሮ በተለይ ቤተ መቅደሱና ይሄ የቦርድ ቢሮ ነው ብላችሁ የምትሰበሰቡበት ቤት ዋና መኖሪ ክፍሎቼ ነበሩ፡፡
የቦርዱ ሂሳብ ሹም - እና ምን ይጠበስ ታዲያ ? አሉ በንዴት ድንገት ጣልቃ ገብተው፡፡
እውነት - እናማ በዚህ አላኖር አላችሁኛ ! መብቴ ይከበር እንጂ ! ቤቱ እኮ የኔ ነው፡፡በገዛ ቤቴ እንዴት እንደ ጎደና ተዳዳሪ እደጅ አድራለሁ ? ¨ረ ተዉ እናንተ ሰዎች ተዉ !
በቦርድ የመንፈሳዊ ክፍል ተወካይ - እውነቱዋን እኮ ነው ! አንድ መላ ይፈለግ እንጂ !
በቦርድ የእቃ ግዢ - እኛም እኮ ተቸገረን ነው ፡፡ ቤቱን አንድ ጊዜ ለውሸት በከፍተኛ ዋጋ ስላከራየነው እሱን አሁን ውጣ ማለት ደግሞ ሌላ ችግር ማምጣት ነው፡፡
እውነት - እና እኔ ከገዛ ቤቴ ወጥቼ እየተንገላታሁ መኖር አለብኝ ማለት ነው ? እደጅ ኑሪ ነው የምትሉኝ ?
የቦርድ ምክትል ሊቀመንበር - ¨ረ እንደሱ ማለታችን አይደለም ፡፡ደንገጥ ብለው
እውነት - እና ምን እያላችሁኝ ነው ታዲያ ! ኮስተር ብላ
የቦርድ ምክትል ሊቀመንበር - ውሸትን አነጋግረን በአጭር ጊዜ ውስጥ መልቀቅ አለመልቀቁን እናሳውቅሻለን ለማለት ነው፡፡
የሂሳብ ሹም - ምክትል ሊቀመንበር አሁን በተናገርከው ላይ ተቃውሞ አለኝ ፡፡ እኛ በህዝብ ተመርጠን ይህን ቢሮና ሥልጣኑን ስንረከብ በባለቤትነት ያገኘነው ውሸትን ስለሆነ አሁንም እኛ የምናውቀው እርሱን ብቻ ነው፡፡ (ወደሌሎቹ የቦርድአባላት እየተመለከቱ) ‹የሌሎቻችሁን አላውቅም እኔ ግን በበኩሌ ስለ ‹እውነት› የዚህ ቤት ባለቤትነት ምንም የሰማሁትም የማውቀውም ነገር የለም፡፡›አሉ ( በግንባራቸው እንደማየትና መነጽራችውን ከዓይናቸው ላይ ወጣ ገባ እያደረጉ)
ትዝብት-
ይህን የሂሳብ ሹሙን ንግግር ስሰማ አንዳች ነገር ሰውነቴን ውርር አደረገው፡፡ ትንፋሼንም ዋጥ አደረኩና ‹ አበስ ገበረኩ › አልኩ ለራሴ፡፡ ታዲያ እዚህ ላይ ሂሳብ ሹሙን አንድ ነገር ታዘብኩ፡፡ ምነው እኚህ ሰው ተምረው የለም እንዴ !
የቦርድ ሊቀ መንበር - እጃቸውን ወዳልተናገሩት ሰዎች እያመለከቱ ‹በሉዋ ሌሎቻችሁም ሃሳብ ስጡበት ! እሰቲ ክቡር ገንዘብ ያዥ እረሶ ይናገሩ !
የቦረድ ገንዘብ ያዥ - < it is confusing > ፣ በእርግጥም ደግሞ ሂሳብ ሹሙም ያሉት ትክክል ነው፡፡ I mean ሴትዮዋም (እውነትን ማለታቸው ነው) የምትለው sense ይሰጣል፡፡ አሉ ግራ በተጋባ አስተያት፡፡
የቦርድ ጸሐፊ - እኛ ለማንኛውንም ለምንሠራውን ሥራ ሁሉ መሠረት የምናደርገው መተዳደሪያ ደንባችንን ወይም ,By-lawn ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ የራሱ አማካሪ ኮሚቴ አለው ፤ የሚሠራውንም እነሱን እያማከረ ይሠራል ፡፡ ከመመሪያው ውጪ ግን ምን የምንሠ ራው የለም ፡፡ ወደ እውነት ዘወር ብለው ‹ አሁን አንቺ እየጠየቅሽ ያለሽው ጥያቄ ግን ከ By-law ውጭ ስለሆነ ቦርዱ ሊቀበለው ይከብደዋል ፡፡ እስካሁንም ቢሆን የተሠራው ሁሉ ትክክል ነው ብሎ ቦርዱ ያምናል፡፡
ትዝብት -
የባሰ አታምጣ ! አልኩ አሁንም በልቤ ፡፡ ጸሐፊው ምን ነካቸው ፡፡ እውነት ጨርሶውኑ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የለችም ማለት ነው ? › ብዬ እራሴን ጠየኩ ፡፡ አ« ! አሁን ገባኝ ፡፡ ለካ አዲስ ያወጡትንና ባለፈው ኮረም ሳይሞላ ቀርቶ ሕዝብ ያላጸደቀውን By-law ማለታቸው ነው ? አልኩና ጸሐፊውን ታዘብኩ ፡፡
ተቆጣጣሪዋ - እኔ እንኩዋን እንደ መፍትሄ ይሆናታል ብዬ የምናገረው ፡ - ይሄ ቢሮ እንደምታይው ሁላችንም የየግል ጉዳያችንና ሥራችንን እየተውን እዚህ እየመጣን የምንውልበትና የምናመሽበት መደበሪያችን ነው፡፡ ውሸትንም ቢሆን እዚህ እንዲኖር የፈለግንበት ምክንያት ክሱን ለመከላከል እንጂ እኛም ተመችቶን አይደለም፡፡ በቤተ መቅደሱ እንዳትኖሪ ግን የከለከለሽ ሰው ያለ አይመስለኚም ፡፡
የቦርድ ሊቀ መንበር- እንዴ ! እሱም እኮ ቢሆን የቦረዱን ውሣኔና የሥራ ውጤቶቻችንን ለህዝቡ የምናሳውቅበት መድረክ ነው፡፡ ባይሆን Share ልናደርግ እንችላለን እንጂ ሙሉ ለሙሉ ጠቅልለሽ እዛው ግቢ ማለትማ አንችልም ፡፡ By-law ውም አይፈቅድም ፡፡ አሉ ሁሉንም የቦር አባላት በዓናቸው እየማተሩ ፡፡
እውነት - በዚህ ጊዜ በኃይል ተነፈሰች ፡፡ እሺ ! እግዜር ይስጥልኝ ፡፡ ሁላችሁንም ሰማሁ ፡፡ በርቱ ! ቀጥሉ ! እድሜ ይስጠን እንጂ ሁሉንም በቅርብ እናየዋለን ! ‹ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ! ተብላል› ፡፡ እማያልፍ ግን የለም ! ሁሉም ያልፋል ! ግን እስኪያልፍ ያለፋል ፡፡ › ብላ ፊቱዋን አዙራ ወጥታ ሄደች ፡፡ የተከተላትም አልነበረም፡፡
ትዝብት
እኔም ባየሁትና በሰማሁት ነገር ሁሉ እጅግ ተገርሜ ብዙም ሳልቆይ ወጣሁ፡፡ የቦርድ አባላቱ ስብሰባቸውን እስኪጨርሱ ድረስ በፊት ለፊቱ የቤተክርስቲያኑ ታዛ ሥር ቁጭ አልኩ ፡፡ በግምት ከሁለት ሰዓት በâላ ስብሰባቸው ማለቁን ስረዳ አንዳንድ የቦርድ አባላትን ስለ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኑ ሁኔታ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ መቅረጸ ድምጼን ይዤ ተመልሼ እቢሮአቸው ገባሁ፡፡ማንነቴን ብገልጽ ፈቃደኞች እንደማይሆኑ ስለተረዳሁ እንደ አንድ የኮሚኒቲው ጋዜጠኛ ሆኜ ቀረብኩ፡፡ የመጣሁበትን ጉዳይ ተናግሬ ሦስቱ የቦርድ አባላት ለቃለ መጠይቁ ፈቃደኝነታቸውን ስለገለጹልኝ ከእነርሱ ጋር ሁለት ሰዓት የፈጀ ቃለ መጠይቅ አድርገን ተለያየን ፡፡ ይህን አስደናቂና አስቂኝ ቃለ መጠይቅ በትኩረት ቁጥር 3 ቃለመጠይቅ ዓምድ ይጠብቁ !
ቀበሮ ቀበሮ ቀበሮ ብልጢቱ
የሰውን ብልጣ ብልጥ አረገችው ከንቱ፡፡
አዬ ሰው ! አዬ ሰው ! አለችና ወን›
ሳትቀደም ቀድማ ገባች ከጉድጉዋ› !
ቸር ይግጠመን !
No comments:
Post a Comment
አስተያየት