Tuesday, October 27, 2009

የአስተዳደር ቦርዱ ያወጣው አዲሱ ባይሎው የእምቧይ ካብ ሆነ !

የአስተዳደር ቦርዱን የሥልጣን ዘመን እንደ ማቱሳላ እድሜ እንዲያራዝምና የሥልጣን ቅብበሎሹ ከቤተሰብና ከደኛ እጅ እንዳይወጣ ወይም የዘር ሐረግን ብቻ እየቆጠረ እንዲሄድ ተደርጎ የተዘጋጀው የቦርዱ ባይሎ ባለፈው ሳምንት እንደ እምይ ካብ መናዱ ተነገረ፡፡ይህ የአስተዳደሩን የሥልጣን እርከን ጣራ የሚያስነካና የምእመናን መብት የሚገፍፍ ሕግ የወጣው የአስተዳደር ዘመናቸውን በጨረሱ ሦስት አባላት ምትክ አዲስ ምርጫ እክንዲካሄድ በአባላት በመጠየቁ ምክንያት ነበር፡፡ያለ ሕዝብ ፈቀድና ተሳትፎ <የአስተዳደር ቦርዱ በራሱ ሕግ እዲያወጣና እዲያጸድቅ የቀድሞው ባይሎው ይፈቅድለታል> በሚል ሰበብ አምባ ገነነዊ የሆነ አዲስ ሕግ በራሳቸው ደንግገው ሕገ ወጥ ሥራ ሲሠሩበት ከርመዋል ፡፡ የአስተዳደር ቦርድን የከሰሰ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤተክርስቲያኑ አባልነት ይባረራል፡፡ › በሚለውና ሕዝቡን ለማስፈራራት ሲሉ በሕጋቸው ውስጥ በጨመሩት የማስፈራሪያ አንቀጽ በመጠቀም ብዙ የማይፈልቸውን አባላት ከአባልነት መዝገብ ሠርዘዋል፡፡ በሕግ ፊትም የከሰሱን የቤተክርስቲያናችን አባላት ስላልሆኑ ክቡር ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን፡፡ › በማለት በለመዱት የማጭበርበር ዘዴያቸው ክቡር ፍርድ ቤቱንም ለመፈታተን ሞክረዋል ፡፡ ‹ በቆፈሩት ጉድድ ይገቡበታል ፡፡ › እንዲሉ እንኩዋን ክሱ ውድቅ ሊሆን ይቅርና አዲሱ ሕጋቸውን ያለ ሕዝብ ፈቃድ ለብቻቸው ሕግ አውጥተው ከሳሾችን ከቤተ ክርስቲያን እንዲያባርሩ ሊያደርጉ የቻሉበትንና ይህን ተግባራቸውን ሊደግፍላቸው የሚያስችላቸውን ማስረጃ እስካላቀረቡ ድረስ ሕጋቸውን ተግባራዊ ማድረግ እንደማይችሉ በሕግ አስከባሪው አካል የተነገራቸው መሆኑን ለማወቅ ተችል፡፡

መንግሥት ለዜጎቹ- እራሳቸውን ፤ ቤሰባቸውን ፤ንብረቶቻቸውንና ሀገራቸውን ጭምር በአግባቡ ለመጠበቅ እንዲችሉበት በየደረጃው ሊሚቀርብለት የመሣሪያ ፈቃድ ጥያቄ እንደ ጥያቄው ትክክለኛነትና በሕግ በተቀመጠው መመዘኛና መስፈርት መሠረት ፈቃዱን እንደሚሠጥ ይታወቃል፡፡ነገር ግን እገሌ ጠላቴ ስለሆነ መሣሪያውን እንድገዛና እርሱን እንድገድልበት የመሣሪያ ፈቀድ ይሠጠኝ› ብሎ የሚጠይቅን ሰው መንግሥት ምን ያደርገዋል ? መልሱ ለማናችንም ግልጽ ነው፡፡ይህ ሰው በመጀመሪያ የጠየቀው ፈቃድ ይነፈገዋል፡፡ሁለተኛም ባይገድልም አስልና በታሰበ የነፍስ ግድያ ወንጀል በሕግ ይጠየቅበታል፡፡ እንደዚሁም የአስተዳደር ቦርዱ በራሱ ያወጣው ሕግም አባላትን የሚገድል መሣሪያ ነው ፡፡ ክቡር ፍርድ ቤቱን ‹እኛ የቦርድ ባለሥልጣናት ነንና ተራ ምዕመናንን ግን እንደፈለገን እያስወጣን እያባረር እንኖር ዘንድ ሙሉ ፍቃድ ይሠጠን › ብሎ እንደ መጠየቅ ይቆጠራልና ከተጠያቂነት አያድንም !

No comments:

Post a Comment

አስተያየት