Thursday, October 29, 2009

ገንዘብ ያዡና የሂሳብ ሹሙ በቤተክርስቲያኑዋ ገንዘብ የያዙት ጨዋታ !

በሦስት ቡድን መከፋፈሉ የሚነገርለት የአስተዳደር ቦርድ ከመካካሉ የወላጅ ኮሚቴ አባላትን ደጋፊ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው የሂሳብ ሹሙና የገንዘብ ያዡ ቡድን በገንዘብ ቅሌት ውስጥ መግባቱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጡ ፡፡

Tuesday, October 27, 2009

የአስተዳደር ቦርዱ ያወጣው አዲሱ ባይሎው የእምቧይ ካብ ሆነ !

የአስተዳደር ቦርዱን የሥልጣን ዘመን እንደ ማቱሳላ እድሜ እንዲያራዝምና የሥልጣን ቅብበሎሹ ከቤተሰብና ከደኛ እጅ እንዳይወጣ ወይም የዘር ሐረግን ብቻ እየቆጠረ እንዲሄድ ተደርጎ የተዘጋጀው የቦርዱ ባይሎ ባለፈው ሳምንት እንደ እምይ ካብ መናዱ ተነገረ፡፡ይህ የአስተዳደሩን የሥልጣን እርከን ጣራ የሚያስነካና የምእመናን መብት የሚገፍፍ ሕግ የወጣው የአስተዳደር ዘመናቸውን በጨረሱ ሦስት አባላት ምትክ አዲስ ምርጫ እክንዲካሄድ በአባላት በመጠየቁ ምክንያት ነበር፡፡ያለ ሕዝብ ፈቀድና ተሳትፎ <የአስተዳደር ቦርዱ በራሱ ሕግ እዲያወጣና እዲያጸድቅ የቀድሞው ባይሎው ይፈቅድለታል> በሚል ሰበብ አምባ ገነነዊ የሆነ አዲስ ሕግ በራሳቸው ደንግገው ሕገ ወጥ ሥራ ሲሠሩበት ከርመዋል ፡፡ የአስተዳደር ቦርድን የከሰሰ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤተክርስቲያኑ አባልነት ይባረራል፡፡ › በሚለውና ሕዝቡን ለማስፈራራት ሲሉ በሕጋቸው ውስጥ በጨመሩት የማስፈራሪያ አንቀጽ በመጠቀም ብዙ የማይፈልቸውን አባላት ከአባልነት መዝገብ ሠርዘዋል፡፡ በሕግ ፊትም የከሰሱን የቤተክርስቲያናችን አባላት ስላልሆኑ ክቡር ፍርድ ቤቱ ክሱን ውድቅ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን፡፡ › በማለት በለመዱት የማጭበርበር ዘዴያቸው ክቡር ፍርድ ቤቱንም ለመፈታተን ሞክረዋል ፡፡ ‹ በቆፈሩት ጉድድ ይገቡበታል ፡፡ › እንዲሉ እንኩዋን ክሱ ውድቅ ሊሆን ይቅርና አዲሱ ሕጋቸውን ያለ ሕዝብ ፈቃድ ለብቻቸው ሕግ አውጥተው ከሳሾችን ከቤተ ክርስቲያን እንዲያባርሩ ሊያደርጉ የቻሉበትንና ይህን ተግባራቸውን ሊደግፍላቸው የሚያስችላቸውን ማስረጃ እስካላቀረቡ ድረስ ሕጋቸውን ተግባራዊ ማድረግ እንደማይችሉ በሕግ አስከባሪው አካል የተነገራቸው መሆኑን ለማወቅ ተችል፡፡

መንግሥት ለዜጎቹ- እራሳቸውን ፤ ቤሰባቸውን ፤ንብረቶቻቸውንና ሀገራቸውን ጭምር በአግባቡ ለመጠበቅ እንዲችሉበት በየደረጃው ሊሚቀርብለት የመሣሪያ ፈቃድ ጥያቄ እንደ ጥያቄው ትክክለኛነትና በሕግ በተቀመጠው መመዘኛና መስፈርት መሠረት ፈቃዱን እንደሚሠጥ ይታወቃል፡፡ነገር ግን እገሌ ጠላቴ ስለሆነ መሣሪያውን እንድገዛና እርሱን እንድገድልበት የመሣሪያ ፈቀድ ይሠጠኝ› ብሎ የሚጠይቅን ሰው መንግሥት ምን ያደርገዋል ? መልሱ ለማናችንም ግልጽ ነው፡፡ይህ ሰው በመጀመሪያ የጠየቀው ፈቃድ ይነፈገዋል፡፡ሁለተኛም ባይገድልም አስልና በታሰበ የነፍስ ግድያ ወንጀል በሕግ ይጠየቅበታል፡፡ እንደዚሁም የአስተዳደር ቦርዱ በራሱ ያወጣው ሕግም አባላትን የሚገድል መሣሪያ ነው ፡፡ ክቡር ፍርድ ቤቱን ‹እኛ የቦርድ ባለሥልጣናት ነንና ተራ ምዕመናንን ግን እንደፈለገን እያስወጣን እያባረር እንኖር ዘንድ ሙሉ ፍቃድ ይሠጠን › ብሎ እንደ መጠየቅ ይቆጠራልና ከተጠያቂነት አያድንም !

ክርክር

እውነት ከወደ ዳውን ታውን ፍረድ ቤት ተነስታ የደብራችንን ቦርድ አባለት ለማነጋገር ኖርዝ ጁፒተርን ይዛ ሽቅብ ወደ ጋርላንድ ጉዞዋን ጀመረች ፡፡ ጉዞዋ ዝግ ያለ ነበርና በራሰዋ ጊዜ ደረሰች ፡፡ የቦርድ አባላቱን የመሰብሰቢያ ቀን ታውቅ ነበርና በሩን አንÎኩታ ጤና ይስጥልኝ ብላ እቢሮአቸው ገባች ፡፡ ከዚያስ ? ከዚያ በâላ ያለውንማ ትዝብት ‹ ክርክር › በሚል ርዕስ የዘገበችውን ትተርክላችሁ::

በዚህ ርዕስ የቀረበውን ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ሁሉ ለቀልድ ወይም በሳቅ ለማዝናናት እንደተዘጋጀ ብቻ አደርጋቸው እንዳትቆጥሩት በቅድያ አሳስባለሁ፡፡ ክርክሩ የተካካሄደው በእውነትና በአምባገነኖቹ የአስተዳደር ቦርድ አባለት መካከል ነው፡፡

ትዝብት› ክርክር በሚል ዓምድ ሥር የያዘችው መልዕክት በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲን የአስተዳደር ወንበር ላይ የተቀመጡ እያንዳንዳቸው የቦርድ አባላት በእውነት ላይ ያላቸውን ጥላቻና የተሳሳተ አመለካከት በአጭሩ የሚስገነዝብ ነው ፡፡ ክርክር በሚል ርዕስ የቀረበበትም ምክንያት እውነት ህልውናዋን ለማሳወቅ ያደረገቸውን ጥረትና ከአስተዳደሩ ጋር የገጠማትን ሙግት ስለሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ትዝብትም› የታካሄደውን ክርክር በመሃል ተገኝታ በማድመጥ ብዙ ነገር ታዝባለች ፡፡ እንድናነብ የምትጋብዘንም እርሱዋ ናት፡፡ እንግዲህ በማስተዋል አንቡቡት፡፡

እውነት- ብዙ ጌዜ ወደ እኔ መጥታችው እንድንወያይ ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጌ ባለመምጣታችሁ ዛሬ እናንተ ካላችሁበት ቦታ ድረስ መጥቼ እዳነጋግራችሁ ተገድጃለሁ ፡፡

የቦርድ ሊቀ መንበር - ማን ልበል አንቺን

እውነት - በእርግጥ አታውቁኝም ! ስሜ ግን ‹እውነት› ይባላል፡፡

የቦርድ ሊቀ መንበር - ኮስተር ብለው ‹ታዲ ምን ፈለግሽ ዚህ› ፡፡

እውነት - ህልውናዬን በተመለከተ ከእናንተ ከቦርድ አባላቱ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፡፡

የቦርድ ሊቀ መንበር - ይቅርታ አድርጊልኝና እኛ ከአንቺ ጋር ለመነጋገር ፈቀደኞችም በአጠቃላይ ደስተኞችም አይደለንም ፡፡ ብንነጋገርም መግባባት የምንችል አይመስለኝም ፡፡

እውነት - ከተነጋገርን እንዴት ነው የማንግባበው ?

የቦርድ ሊቀ መንበር - አንግባባማ ! አንቺ የካሳሾቹ ደጋፊ እንደሆንሽ እናውቃለን ፡፡ ስለዚህ ክሱ እስካላቆመ ድረስ በምንም ጉዳይ ላይ መነጋገር አንችልም ፡፡በቃ አለቀ፡፡

የቦርድ ሕዝብ ግንኙነት - እስቲ መጀመሪያ ለምን እንደመጣች ምክንያቱን ከእረሱዋ እንስማና ከዚያ በâላ መልስ መስጠት ካስፈለገ መልስ ልንሰጥበት እንችላለን፡፡

የቦርድ ሊቀመንበር - Ok ! ለመሆኑ ጉዳይሽ ምንድነው ፡፡በንዴት መንፈስ

ውነት - እኔ ዛሬ እዚህ የመጣሁት ፤ የምትሰሙኝ ከሆነ የደረሰብኝን በደል አቤት ለማለት ነው ፡፡

የቦርድ ሊቀመንበር - አቤት ባዩ በዛ እኮ ባከችሁ ! የምን አቤቱታ ነው ያንቺ ደግሞ ? አሉ በምጸት ቃል፡፡

ትዝብት -

እዚህ ላይ ሊቀመንበሩ በደንበኞች አገልግሎት (customer service) ዜሮ መሆናቻውንና ስብሰባን ገና ሳይጀመር ኃይለ ቃል በመናገር ለመዝጋት መሞከራቸውን ታዘብኩ፡፡ ይህ ደግሞ የአንድን ሰብሳቢ quality ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱና ዋናው ነው፡፡

እውነት - ከቤተ መቅደሱ ጀምሮ በዚህ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ክፍሎች በሙሉ የእኔ ቤቶች ናቸው፡፡ እንደ ሕጉማ ቢሆን ኑሮ በተለይ ቤተ መቅደሱና ይሄ የቦርድ ቢሮ ነው ብላችሁ የምትሰበሰቡበት ቤት ዋና መኖሪ ክፍሎቼ ነበሩ፡፡

የቦርዱ ሂሳብ ሹም - እና ምን ይጠበስ ታዲያ ? አሉ በንዴት ድንገት ጣልቃ ገብተው፡፡

እውነት - እናማ በዚህ አላኖር አላችሁኛ ! መብቴ ይከበር እንጂ ! ቤቱ እኮ የኔ ነው፡፡በገዛ ቤቴ እንዴት እንደ ጎደና ተዳዳሪ እደጅ አድራለሁ ? ¨ረ ተዉ እናንተ ሰዎች ተዉ !

በቦርድ የመንፈሳዊ ክፍል ተወካይ - እውነቱዋን እኮ ነው ! አንድ መላ ይፈለግ እንጂ !

በቦርድ የእቃ ግዢ - እኛም እኮ ተቸገረን ነው ፡፡ ቤቱን አንድ ጊዜ ለውሸት በከፍተኛ ዋጋ ስላከራየነው እሱን አሁን ውጣ ማለት ደግሞ ሌላ ችግር ማምጣት ነው፡፡

እውነት - እና እኔ ከገዛ ቤቴ ወጥቼ እየተንገላታሁ መኖር አለብኝ ማለት ነው ? እደጅ ኑሪ ነው የምትሉኝ ?

የቦርድ ምክትል ሊቀመንበር - ¨ረ እንደሱ ማለታችን አይደለም ፡፡ደንገጥ ብለው

እውነት - እና ምን እያላችሁኝ ነው ታዲያ ! ኮስተር ብላ

የቦርድ ምክትል ሊቀመንበር - ውሸትን አነጋግረን በአጭር ጊዜ ውስጥ መልቀቅ አለመልቀቁን እናሳውቅሻለን ለማለት ነው፡፡

የሂሳብ ሹም - ምክትል ሊቀመንበር አሁን በተናገርከው ላይ ተቃውሞ አለኝ ፡፡ እኛ በህዝብ ተመርጠን ይህን ቢሮና ሥልጣኑን ስንረከብ በባለቤትነት ያገኘነው ውሸትን ስለሆነ አሁንም እኛ የምናውቀው እርሱን ብቻ ነው፡፡ (ወደሌሎቹ የቦርድአባላት እየተመለከቱ) ‹የሌሎቻችሁን አላውቅም እኔ ግን በበኩሌ ስለ ‹እውነት› የዚህ ቤት ባለቤትነት ምንም የሰማሁትም የማውቀውም ነገር የለም፡፡›አሉ ( በግንባራቸው እንደማየትና መነጽራችውን ከዓይናቸው ላይ ወጣ ገባ እያደረጉ)

ትዝብት-

ይህን የሂሳብ ሹሙን ንግግር ስሰማ አንዳች ነገር ሰውነቴን ውርር አደረገው፡፡ ትንፋሼንም ዋጥ አደረኩና ‹ አበስ ገበረኩ › አልኩ ለራሴ፡፡ ታዲያ እዚህ ላይ ሂሳብ ሹሙን አንድ ነገር ታዘብኩ፡፡ ምነው እኚህ ሰው ተምረው የለም እንዴ ! የሚባል ነገር አለ እኮ ፡፡ እንደምሁርነታቸው በሃቅ ከመስራት ይልቅ ውሸታም መሆን ለምን መረጡ ? › በውሸትና በማጭበርበር ከዚህ ቤተክርስቲያን ሊያገኙ የሚፈልጉት ነገር አለ እንዴ ብዬም አሰብኩ፡፡እንግዲህ እሱን አንድዬ ይመርምረው፡፡

የቦርድ ሊቀ መንበር - እጃቸውን ወዳልተናገሩት ሰዎች እያመለከቱ ‹በሉዋ ሌሎቻችሁም ሃሳብ ስጡበት ! እሰቲ ክቡር ገንዘብ ያዥ እረሶ ይናገሩ !

የቦረድ ገንዘብ ያዥ - < it is confusing > ፣ በእርግጥም ደግሞ ሂሳብ ሹሙም ያሉት ትክክል ነው፡፡ I mean ሴትዮዋም (እውነትን ማለታቸው ነው) የምትለው sense ይሰጣል፡፡ አሉ ግራ በተጋባ አስተያት፡፡

የቦርድ ጸሐፊ - እኛ ለማንኛውንም ለምንሠራውን ሥራ ሁሉ መሠረት የምናደርገው መተዳደሪያ ደንባችንን ወይም ,By-lawn ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ የራሱ አማካሪ ኮሚቴ አለው ፤ የሚሠራውንም እነሱን እያማከረ ይሠራል ፡፡ ከመመሪያው ውጪ ግን ምን የምንሠ ራው የለም ፡፡ ወደ እውነት ዘወር ብለው አሁን አንቺ እየጠየቅሽ ያለሽው ጥያቄ ግን ከ By-law ውጭ ስለሆነ ቦርዱ ሊቀበለው ይከብደዋል ፡፡ እስካሁንም ቢሆን የተሠራው ሁሉ ትክክል ነው ብሎ ቦርዱ ያምናል፡፡

ትዝብት -

የባሰ አታምጣ ! አልኩ አሁንም በልቤ ፡፡ ጸሐፊው ምን ነካቸው ፡፡ እውነት ጨርሶውኑ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የለችም ማለት ነው ? ብዬ እራሴን ጠየኩ ፡፡ አ« ! አሁን ገባኝ ፡፡ ለካ አዲስ ያወጡትንና ባለፈው ኮረም ሳይሞላ ቀርቶ ሕዝብ ያላጸደቀውን By-law ማለታቸው ነው ? አልኩና ጸሐፊውን ታዘብኩ ፡፡

ተቆጣጣሪዋ - እኔ እንኩዋን እንደ መፍትሄ ይሆናታል ብዬ የምናገረው ፡ - ይሄ ቢሮ እንደምታይው ሁላችንም የየግል ጉዳያችንና ሥራችንን እየተውን እዚህ እየመጣን የምንውልበትና የምናመሽበት መደበሪያችን ነው፡፡ ውሸትንም ቢሆን እዚህ እንዲኖር የፈለግንበት ምክንያት ክሱን ለመከላከል እንጂ እኛም ተመችቶን አይደለም፡፡ በቤተ መቅደሱ እንዳትኖሪ ግን የከለከለሽ ሰው ያለ አይመስለኚም ፡፡

የቦርድ ሊቀ መንበር- እንዴ ! እሱም እኮ ቢሆን የቦረዱን ውሣኔና የሥራ ውጤቶቻችንን ለህዝቡ የምናሳውቅበት መድረክ ነው፡፡ ባይሆን Share ልናደርግ እንችላለን እንጂ ሙሉ ለሙሉ ጠቅልለሽ እዛው ግቢ ማለትማ አንችልም ፡፡ By-law ውም አይፈቅድም ፡፡ አሉ ሁሉንም የቦር አባላት በዓናቸው እየማተሩ ፡፡

እውነት - በዚህ ጊዜ በኃይል ተነፈሰች ፡፡ እሺ ! እግዜር ይስጥልኝ ፡፡ ሁላችሁንም ሰማሁ ፡፡ በርቱ ! ቀጥሉ ! እድሜ ይስጠን እንጂ ሁሉንም በቅርብ እናየዋለን ! ‹ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል ! ተብላል› ፡፡ እማያልፍ ግን የለም ! ሁሉም ያልፋል ! ግን እስኪያልፍ ያለፋል ፡፡ብላ ፊቱዋን አዙራ ወጥታ ሄደች ፡፡ የተከተላትም አልነበረም፡፡

ትዝብት

እኔም ባየሁትና በሰማሁት ነገር ሁሉ እጅግ ተገርሜ ብዙም ሳልቆይ ወጣሁ፡፡ የቦርድ አባላቱ ስብሰባቸውን እስኪጨርሱ ድረስ በፊት ለፊቱ የቤተክርስቲያኑ ታዛ ሥር ቁጭ አልኩ ፡፡ በግምት ከሁለት ሰዓት በâላ ስብሰባቸው ማለቁን ስረዳ አንዳንድ የቦርድ አባላትን ስለ አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኑ ሁኔታ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ መቅረጸ ድምጼን ይዤ ተመልሼ እቢሮአቸው ገባሁ፡፡ማንነቴን ብገልጽ ፈቃደኞች እንደማይሆኑ ስለተረዳሁ እንደ አንድ የኮሚኒቲው ጋዜጠኛ ሆኜ ቀረብኩ፡፡ የመጣሁበትን ጉዳይ ተናግሬ ሦስቱ የቦርድ አባላት ለቃለ መጠይቁ ፈቃደኝነታቸውን ስለገለጹልኝ ከእነርሱ ጋር ሁለት ሰዓት የፈጀ ቃለ መጠይቅ አድርገን ተለያየን ፡፡ ይህን አስደናቂና አስቂኝ ቃለ መጠይቅ በትኩረት ቁጥር 3 ቃለመጠይቅ ዓምድ ይጠብቁ !

ቀበሮ ቀበሮ ቀበሮ ብልጢቱ

የሰውን ብልጣ ብልጥ አረገችው ከንቱ፡፡

አዬ ሰው ! አዬ ሰው ! አለችና ወን

ሳትቀደም ቀድማ ገባች ከጉድጉዋ !

ቸር ይግጠመን !

ትኩረት ይሠጥበት !


በአስተዳደር ቦርዱ እልከኝነትና አምባ ገነንነት ምክንያት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተደቀነው አደጋ በቀላሉና በዝምታ የሚታይ ጉዳይ አይደለም' እንደኔ ምኞትና ፍላጎት ቢሆን ጉዳዩ ፍርድ ቤት ባይደርስ ጥሩ ነበር' ነገር ግን አስተዳደሩ ወገናዊ ሆኖ አንዱን ወገን የሚሰማና ሌላውን ወገን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት የሚደክምና ጽንፈኝነት የተጠናወተው ስለሆነ መፍትሔው የግድ ይህን ክፉ ምግባሩን በሕግ አስከባሪዎች በኩል እንዲያቆም ማድረግ ብቻ ነበር 'ይህም እየተደረገ ነው'

የሚገርመኝ ነገር የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ምእመናን መሥራቾቹንና አዲሱን ትውልድ ጨምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተፈቃቅረንና ተከባብረን የምንኖር አንድ ቤተሰብ ነበርን'አለመግባባት በመሃላችን ቢከሰትም እንኩዋን ሊጊዜው ተ¯¨ንና ተተራምሰን ሁሉን በመተው ለጋራ አገልግሎት ተቻችለን በሰላም እንኖር ነበር'ቀደም ሲልም በተለያዩ ጊዜያት የነበሩት የአስተዳደር ቦርድ አባላትም ቢሆኑ ጥሩ የማስተዳደር ችሎታ ነበራቸው ባይባልም እንደነዚህ ግን መረን የለቀቁና አይናውጣዎች አልነበሩም'

ለመሆኑ እንዲህ ለሰው ክብር የለሾች እንዲሆኑና ከልማት ይልቅ ለጥፋት እንዲሰለፉ ያደረጋቸው ምንድነው ብዬ በማገኘው የጨዋታ አጋጣሚ ሁሉ አንዳንዶችን ስጠይቅ በአብዛኛው የሰጡኝ መልስ ግን ተቀራራቢ ነበር'ይኸውም ‹ ምንነቱ የማይታወቅና ባለጌ ሰው በመካከላቸው በመግባቱ ነው ›የሚል ነበር'.

ይህ ሰው ደህናዎቹንና ጥሩዎቹን ሰዎች ሁሉ በአንድ ጊዜ በተንኮልና በነገር አባልጎ መረን ለቀቃቸው 'ተው ሲባል የማይሰማ ፤ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ፤ እኔን ብቻ ስሙኝ የሚል በመሆኑ በጽኑ ዓላማ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመኖር ወደ አለመኖር ለማድረስ ያቅሙን ያህል እየጣረ ነው'ቤተክርስቲያኒቱ ብትፈርስ ባትፈርስ ፤ ሕዝቡ ቢበተን ባይበተን ለእርሱ ጉዳዩ አይደለም'ይህንንም ሳያስበው ለሰው በጨዋታ መልክ ተናግሮታል ' በሃይማኖቱም ቢሆን ከነባለቤቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ሳይሆን ሌላ ነው' ሌላ ነው ስል ፤ ምንድነው ግን አትበሉኝ' ሰውየው ሃይማኖቱም ሆነ እምነቱ ሆዱና ጥቅሙ ብቻ ነው'ለዚህ በቅርብ የሚያውቁትና ገና ዳለስ ሲመጣ ጀምሮ በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ሊመሰክሩ የሚችሉት ሃቅ ነው'.

ገና ወደ ቦርድ ሲገባ ይዞ የገባው ከውጭ ሆነው ፍትፍት የሚያጎረሱትንና ጠጅ የሚያጠጡትን አፍረራሽ ተልኮ ያላቸውን የነቡክሪን እኩይ ሃሳብ ነው'ሴት የላካው ሞት አይፈራም እንዲሉ እረሱዋም ከደጅ ሆና የምታሰማው ቀረርቶና ፉከራ ሁሉ ይህንኑ የሚያሳይ ነው'

ሰውዬው ሌሎቹን የቦርድ አባላት እንዳልተማሩ ወይም ምንም እንደማያውቁ ፤ በመካከላቸውም ከእርሱና ከአቶ አበራ ፊጣ በቀር የተሻለ ሃሳብ ማውጣት የማይችሉ መሃይምናን እንደሆኑ አድርጎ የሚመለከትና የሚንቅ ነው' ይህ ጉዳይ ቀሪዎቹን የቦርድ አባላትን የሚመለከት ሰለሆነ እነርሱ ይጨነቁበት '

ለመሆኑ ይህ ዶክተር ነኝ ተብዬ ሰው በዚች ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው የወደፊት ምኞትና ዓላማ ምንድነው

ይህንን ግን ልብ ያለው ሁሉ ልብ ይበል !

የዶክተር ነኝ ተብዬው ሰው ዋና ዓላማማ

1.‹ አላዋቂና አØመ ቢሰ በመባል ዘወትር በህዝብ ዘንድ የሚተቸውንና የቤተክርስቲያኑን ገንዘብ ለግሉ ተጠቅሞ ሂሳቡን ሳወራርድ የሰነድ ማስረጃ በዶክተሩ ተግኝቶበታል የሚባለውንና ቤተ ክርስቲያኑዋን በአመራር ችሎታ እጦት ምክንያት እዚህ ማጥ ውስጥ የከተታትን የቦረዱን ሊቀመንበር በማስፈራት ከሥልጣን አውርዶ በመሪነት ቦታ ላይ መቀመጥ የዶክተሩ ተቀዳሚ አላማ ነው' › ይህን ለማሳካት ደግሞ ሰብሳቢው በሌለበት ሌሎቹን የቦርድ አባላት ለብቻ በመሰብሰብ አልተሳካም እንጂ የመፈንቅለ ሥልጣን አይነት ሙከራዎችን ዶል'

2. ሰውዬው ውስጣዊ የሥልጣን ፍላጎቱ በግልጽ ገንፍሎ ወጥቶአል ' ‹ እኔ ዶክተሩ እያለሁ እንዴት ከእኔ በታች የሆነ አላዋቂ ሰው ከእኔ በላይ ሆኖ ይመራኛል› በሚል የትዕቢት መንፈስ ስሜቱ እየታመሰ ስለሆነ ፤ ወይ ሊቀመንበር መሆን አለበት፤ አሊያም ይህ ካልተሳካ ደግሞ እውነት እንጂ ውሸት የማይስማማትን ቤተ ክርስቲያን ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን በሕግ ፊት አቁሞ ሀሰተኛ አድርገው ለማሳጣትና ካልሆንም አፈራርሶና አበለሻሽቶ ለመሄድ ነው' ለዚህም የሕግ የበላይነት ከምንም በላይ የነገሠበትን የአሜሪካንን ፍርድ ቤት በተራ የዱርዬ ሥራና የተጭበረበረ ሰነድ እንዲሁም ክህደት ለማታለል በመሪነት እየሞከረ ነው' ታዲያ ይህ ሰው በእውነት ተምሮአል ወይ የሚያሰኝ ነው' ዶክትሬቱስ የተገኘው በምንድን ነው ? የሚለውን ጥያቄ በሰው ሁሉ ዘንድ እየፈጠረ ነው ' ዶክተሬቱን በውሸትና በክደት ከሆነ የሠራው ‹ይገባዋል› ብለናል '

በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትና ከበሬታ የነበራቸውን እንደነ አቶ ሠይፉ ይገዙንና ፣ እነአቶ ዳኜን የሌሎችንም ትልልቅ ሰዎች አንገት ያስደፋና በብልግናው ያሰፈረ ይህ ሰው ለቤተክስቲያኑዋ ዋና ጠንቅና ወደፊትም ለሚገጥማት ችግር ሁሉ መሪና ዋና ተዋናይ ሆኖ እየሠራ ስለሆነ ህዝበ ክርስቲያኑ በአንክሮ እንዲረዳውና እንዲያጤነው ያስፍልጋል ' '

ወደፊት ይህን ሰው ሳታውቁት ቦርድ የከተታችሁት ሰዎች ይህንን ሙሾ ታወርዳላችሁ !

እኔው በገዛ እጄ የጫርኩት እረመጥ

መች ይፈËž ነበር አርፌ ብቀመጥ '

ኸረ የሕግ ያለህ እያላችሁ የምትጮሁ ሰዎች ደግሞ እንዲህ እያላችሁ ትተርታላችሁ !

በፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ

አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ'