ይህ ትምህርት የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋርያዊው የወንጌል አገልግሎት ጉዞው ብዙ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ብዙ ተሰድቧል፤ ብዙ ተገርፏል፤ ብዙ ጊዜ ታሥሯል፤ በሥጋው ብዙም የግድያ ሙከራዎችም ተደርገውበታል፡፡ ይሄ ሁሉ ፈተና ግን ሳይበግረው ‹ ዓለም ሲፈልግ እብድ ነው ይበለኝ እንጂ ሰለ ቤተ ክርስቲያን እንደ አበደ ሰው ሆኜ እናገራለሁ› ይል ነበር፡፡
የቅዱስ ጳውሎስ የመከራ ምንጮች አይሁድ፤አሕዛብ፤የገዛ ወገኖቹና እርሱ ሐሰተኞች ወንድሞች እያለ የሚጠራቸው መናፍቃን ነበሩ፡፡ እርሱ ያስተማረውን የወንጌል ትምህርትና የሚያቋቁማትን ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በእርሱ ትምህርት ላይ ኑፋቄ እየቀላቀሉ ቤተክርስቲያኒቱን ከመንገድ ለማውጣት የሚታገሉት ሐሰተኞች ወንድሞች( መናፍቃን ) ስለነበሩ በእነዚህ ሰዎች ብዙ ችግር እንደረሰበት በትምህርቱ ውስጥ ጠቅሶታል፡፡ ይሁን እንጂ ቅዱስ ጳውሎስ የደረሰበትን መከራና ችግር ሁሉ ግምት ውስጥ ሳይከት እለት እለት ያሳስበው የነበረው የቤተክርስቲያኒቱ ነገር እንደነበር በመልእክቱ ውስጥ አጠንሮ ገልጧል፡፡
ዛሬም ቢሆን የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች በአገልግሎት እየገጠማቸው ያለው ይኸው ቅዱስ ጳውሎስን የገጠመው የትናንቱ ችግር ነው፡፡ ይህም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በፕሮቴስታን አስተምህሮ እየተሟሸ መቅረቡ ፤ የዛፍ ግንዱ እንጂ ቅርንጫፎቹ አያስፈልጉም ( ኢየሱስ ብቻ እንጂ ቅዱሳን አያስፈልጉም) ወ.ዘ.ተ... የሚሉት እንግዳ ትምሕርቶች በሐሰተኞች ወንድሞችና መምህራን እየተስተጋቡ በመምጣታቸው ለቤተክርስቲያኒቱ ትልቅና አደገኛ ችግር ሆኗል ፡፡ ወደድንም ጠላንም ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ፕሮቴስታንት እምነት ለመቀየር ጦርነቱ በግልጽ ተከፍቶብናል፡፡
ስለዚህ በቤተክርስቲያን ላይ የተከፈተውን ይህን አደገኛ ጦርነት አባቶችና ሕዝቡ ሁሉ በግልጽ እስኪረዱትና እስኪያውቁት ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆችና ማኅበረ ቅዱሳን እንደ አበደ ሰው ኖነው ስለ ቤተክርስቲያን ከመናገርና የመናቃንን ሥውር ሤራ ከማጋለጥ አይቦዝኑም፡፡ ይህም ሐሰተኞች ወንዶሞችና የቤተክርስቲያን ጠላቶችን እንዲሁም ደጋፊዎቻቸውን ሁሉ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያበሳጭና የሚያናድዳቸው ቢሆንም በቤተክርስቲያናችን ላይ የተጀመረው ይህ አደገኛ ጥቃት እስኪቆምና ጨርሶውኑ እስኪጠፋ ድረስ ማኅበሩም ኖነ ሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች እንደ አበደ ሰው ከመናገርና የክርስትና ሃማኖታቸው የሚጠይቀውን ማንኛውንም መስዋዕትነት ከመክፈል ወደ ኋላ የሚሉ አይመስለንም፡፡
ይህ ሐዋርያም ስለ ወንድሞች መዋደድ ደግሞ በደንብ አድርጎ አሳስቧል። (ቆሮ. 13) በጣም የሚገርመው እንደ እናንተ አይነት ሰዎች ነበሩ የሚስቸግሩት የነበር። አሁንም እላለሁ ፍቅርን ለበሱ በፍቅር ተመላለሱ እግዚአብሔር ቤተክርሰትያንን ይጠብቃል እርሱ ከእኛ የሚፈልገው ፈቅርን ብቻ ነው። እግዚአብሔር ፈቅርን ይስጠን አሜን። ዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDeleteዲያቆን ወንደዬ የአብዬን ወደ እምዬ አታምጣ፡፡ አንተም ገና የቤተክርስቲያኒቱ ችግር የገባህ አይመስለኝ፡፡ ባህታውያን የሚይዙትን ከላይ መስቀል ከታች ደግሞ የጦር ቅርጽ ያለውን ዘንግ አላየኽም ፡፡ ዘንጉ እኮ መስቀልና ጦር እንዲኖረው ተደርጎ የተሠራው በሰላምና በፍቅር የሚመጣውን እንዲባርኩባት ፤ ሊያጠቃ ሊበላቸው የሚመጣውን አውሬ ደግሞ ሊያስታግሡበት ነው፡፡ ስለዚህ አንዲቷን ቤተ ክርስቲያንና አንዲቷን ሃይማኖት ለመጠበቅ በጋራ የሚያገለግሉ ሁሉ በፍቅርና በሰላም አንድ ሆነው ይሠራሉ ፤ ይኖራሉ፡፡ እንዳንተና እንደ አስተማሪዎችህ አይነት ባንዳዎች ደግሞ ቤተክርስቲያኗን የፕሮቴስታንት ለማድረግ ያም ካልሆነ ደግሞ ለመሠንጠቅና ......ለማድረግ የምትደክሙ ባንዳዎች ናችሁ ስለዚህ እንዴት ነው እናንተ ጋር በፍቅር የሚኖረው ? መልስልኝ እስቲ ! ዘኦርቶዶክ ተዋህዶ ነኝ ፡፡ ከቶሮን ካናዳ ፡፡
ReplyDeleteየእኔ ወንድም ስድቡን ተወው እባከህ ስለ እግዚአብሔር በለህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጥቅስ አመልከተኝ ወንድምህን ስደብ ወይም ወንድምህን ግደል የሚል ወይም ሐዋርያት ሲገርፏቸሁ ተጋረፉ ሲሰድቧቸሁ ተሳደቡ በለው የጻፉት መጽሐፍ ካለ ነገረኝና ላነበው። እኔ ግን የማውቀው ፍቅር ከሁሉ በላይ እንደ ሚበልጥ ያሰተማሩበትን ነው። ስምህን ደግሞ ግለጽ የፈለከውን ብትልና ወይም ብትመታኝ እወድሀለው አይሁድ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲሰድቡት ሲደበድቡትና ሲሰቅሉት አባት ሆይ የሚደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እንዳለው እኔም ይቅር ይበለህ እላለው። ባህታውያን የሚይዙትን ከላይ መስቀል ከታች ደግሞ የጦር ቅርጽ ያለውን ዘንግ ነው ላልከው ለእኔ እደገባኝ ከሆነ ጦሩ የፍቅር ምልከት እንደሆነ መስቀሉ ደግሞ የመከራ እንደሆነ ነው የማውቀው። አንበህው ከሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር የሚወደኝ መስቀሌን ይዞ ይከተለኝ ያለው እንድንዋጋበት አይደለም መስቀሉን ስናይ ለእኛ የተቀበለውን መከራ እንድናስተውስ ነው። ዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDeleteወንድዬ ስለማውቅህ ተወው፡፡ ይሄ ብሎግ ለእኔ ጥሩ ኢንፎረሜሽን የማገኝበት ምስኮቴ ነውና በዚህ አንተራረብ፡፡ አንድ ቀን እዛው ካለንበት ቦታ በአካል ተገናኝተን እድሜ ይስጠን እንጂ አንተ በግራ እኔ በቀኝ በኩል ተቀምጠን እንነጋገራለን፡፡አንተ እራስህ ፍቅር ሳይኖርህ ፍቅር አከፋፋይ ለመምሰል ግን አትሞክር፡፡ በወረቀት ላይ ወይም በብሎግ ላይ የሚለጠፍ ፍቅር ደግሞ በልብ ያለውን ፍቅር የሚገልጥ አይደለም፡፡እርሱ አርተፊሻል ነው፡፡ ይህን ስል ደግሞ ያንተን እንጂ ሌላውንም አጠቃልዬ አይደለም፡፡
ReplyDeleteወንድመዬ ለምን ስምህን አትነገረኝም እንገናኝ እና አስተምረኝ ፍቅርም ከለለኝ እንገናኝና ፍቅር እንዴት እንደሆነ አስተምረኝ እንነጋገር ወንድምህ ነኝ ሰው ሳያውቅ ያጠፋልና። እኔ ደግሞ አልተረብኩም እኔም እንዳነተ ብሎጉን እወደዋለሁ ያልኩት ግን እግዚአብሔር ይሰበክበት ነው። አሁንም ቤሆን ይህ ነው። ካጠፈው ይቅርታ። ያንተው ወንድም ዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDelete