Saturday, July 30, 2011

ከእንቅልፍ የምተነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ! › ሮሜ 13፡11
ቅዱስ ጳውሎስ እርሱ በሥጋ ከነበረበት ዘመን ጀምሮ ፤ አሁን ያለንበትንም ዘመን ጨምሮ፤ ወደፊት የሚነሳውንምና ዓለም እስከምታልፍበት ዘመን ድረስ ያለውን ትውልድ አካቶ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዘመኑን በመዋጀት ብዙ ድንቅ ነገሮችን ተናግሮአል፡፡ በሥጋው መከራ በመቀበል የሞተልንን አምላክ እንዳንረሣውና በከበረ ደሙ የመሠረታትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑንም በንቃት እንድንጠብቅ ለየአብያተ ክርስቲያናቱ ምዕመናን ከላካቸው የማጽናኛ ፤ የማበረታቻ ፤የማሳሰቢያና የማስጠንቀቂያ አሥራ አራት መልእክቶቹ መረዳት ይቻላል፡፡ 


Monday, July 25, 2011

‹ሰለ ቤተ ክርስቲያን እንደ አበደ ሰው ሆኜ እናገራለሁ›
2ኛ ቆሮ 11፡23
ይህ ትምህርት የቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሐዋርያዊው የወንጌል አገልግሎት ጉዞው ብዙ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ብዙ ተሰድቧል፤ ብዙ ተገርፏል፤ ብዙ ጊዜ ታሥሯል፤ በሥጋው ብዙም የግድያ ሙከራዎችም ተደርገውበታል፡፡ ይሄ ሁሉ ፈተና ግን ሳይበግረው ‹ ዓለም ሲፈልግ እብድ ነው ይበለኝ እንጂ ሰለ ቤተ ክርስቲያን እንደ አበደ ሰው ሆኜ እናገራለሁ› ይል ነበር፡፡

Friday, July 22, 2011

‹ ማኅበረ ቅዱሳን ይውጣ ! 
ሃይማኖተ አበው ይግባ ! ›


ይህ ከላይ የምናነበውን አፍራሽ መፈክር አንግበው ባይሳካላቸውም ተግባራዊ ለማድረግ ቀን ከሌሊት በትጋት እየደከሙ ያሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊዎች ነን የሚሉት ጥቂት ቅጥረኞችና አጋሮቻቸው ናቸው፡፡ማኅበረ ቅዱሳንንም ለማፍረስ ያልተፈነቀለ ድንጋይ፤ ያልተለመነ ዛር የለም ፡፡በማኅበረ ቅዱሳንም መቃብር ላይ የሃይማኖተ አበውን ባንዲራ ተክሎ ለማውለብለብ ያልታለመ ሕልም፤ ያልተቃዠ ቅዠት የለም ፡፡መታወቅ ያለብት አንድ ሃቅ ግን ማኅበረ ቅዱሳን በእንሽላሊት እግር የሚርስ የእንቧይ ካብ አይደለም፡፡ ለመሆኑ ወደ ቤተ ክህነቱ ይግባ እየተባለ ዘወትር ከበሮ የሚደለቅለትና የመቀበያ ቄጤማ በማደራጃው የሚታጨድለት ይህ ሃይማኖተ አበው ማነው ? ‹ የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በቤተክርስቲያን ላይ › ከሚለውና የማኅበረ ቅዱሳን ዶክመነቴሽን ክፍል ካሳተመው አዲስ የመረጃ መጽሐፍ ላይ ያገኘነውን ቆንጽለን እንደሚከተለው አቅርበነዋል ፡፡መልካም ንባብ !

Monday, July 18, 2011

የዳላሱ ዲያቆን አንዱዓለም የሚናገረውንና የሚያደርገውን እየሳተ ነው ! 



ዲያቆን አንዱዓለም የተሐድሶ መናፍቃን ዋና ሽፋንና ጠበቃ እየሆነ የመጣበት ምክንያት ምንድነው ?

ካስተማረውና መንበሩ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ይልቅ ስደተኛ ነኝ ከሚለው የአሜሪካው ሲኖዶስ ጉያ ሥር ተወሽቆ መቆየትን ለምን መረጠ ?

የኢትዮጵያውንና የአሜሪካንን ሲኖዶስ ለማስታረቅ አንድ ወቅት ተነሳስቶ በአበረው ኮሚቴ ውስጥ የመግባቱ ምስጢርስ ምንድን ነበር ?


ገለልተኛ ነው ተብሎ በአፍ እየተጠራ ባላው የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የመቀጠሩስ ተልእኮ ምንድነው ?


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አሣማ መብላት ነውር የለውም እያሉ ማስተማርን ዲያቆን አንዱዓለም ከየት ተማሩት ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ወይስ ከአሜሪካው ሊቃውንት ከእነ አባ ወልደ ትንሣኤ ?

የያሬዳዊውን ዜማ አሰናብተው የፕሮቴስታንትን ቅኝት በፒያኖ ከሚያቀነቅኑ የሎስ አንጀለስ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መዘምራን መካከል አንዷን ማጨቱ የሚነገርለት ይህ ሰው በዚያው ሊቀጠር የተጀመረለት ፕሮሰስ ለምን ተቋረጠ የቀድሞው ፓስትር የአሁኑ ቄስ መላኩስ በዚህ ረገድ እንዳይቀጠር የተጫወተው ሚናስ ምን ነበር ? 


ካላይ በጥያቄ መልክ ለቀረቡት ነጥቦች በቅርብ ዝርዝር ማብራሪያዎች የሚሠጥባቸው ሲሆን በአገር ውስጥ በጠቀናጀ መልኩ የተጀመረው የተሐድሶ መናፍቃንና አቋም የለሽ ሰባኪያንና መዘምራንን ከቤተክርስቲያኒቱ መድረክ የማጥራት ተግባር በመላው ዓለም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን ፡፡ 


ከሃይማኖቱ መጠበቅ ይልቅ ውዳሴ ከንቱንና ገንዘብ ማግበስበስን ሥራዬ ብሎ የተያያዘው ዲያቆን አንዱዓለም የነበረውን የማስመሰል ትህትና ሸጦ በምትኩ ትዕቢትን እንደሸመተበት የሚያውቁት ሁሉ ይናገራሉ፡፡ 


ከሁሉ በላይ ግን ዲያቆን አንዱዓለምና መምህር ልዑለ ቃልን የምታውቁ የቤተክርስቲያኒቱ እውነተኛ ልጆች ሁሉ ይህ ሰው የሰጠውን ይህን ዓይን ያወጣ የሐሰት ምስክርነት በትዝብትና በማስተዋል እንድታደምጡት እየጋበዝን ዲያቆን አንዱዓለም ምን እየሠራ እንዳለና ቀስ እያለ ወዴት እየሄደ እንዳለ እንድታስተውሉ በአንክሮ እናሳስባለን፡፡