Monday, March 14, 2011

ደስ ቢለኝም እጅግ አዝኛለሁ
ከወላጆቹ ጋር ቤተክርስቲያን መሄድ የሚያዘወትር አንድ የሰባት አመት ሕጻን ልጅ ካህኑ ‹ እሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኃል፡፡ ከእግዚአብሔር የሚለምን ሁሉ ይሠጠዋል፡፡ › እያሉ ሲያስተምሩ ይሰማል፡፡ ይህን በልጅ አዕምሮው እያሰላሰለ ይሰነብታል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን መቶ ዶላር እንዲኖረው በመመኘት እግዚአብሔር ቢሰጠኝ ብሎ አሰበና እንዲህ ብሎ ደብዳቤ ጻፈ፡፡ይድረስ በሰማይ ለምትኖር አምላኬ እግዚአብሔር ፤ስሜ እገሌ ይባላል፡፡ዕድሜዬም ሰባት ዓመት ነው፡፡ ለአንድ ጉዳይ አንድ መቶ ዶላር አስፈልጎኛልና በአስቸኳይ እንድትልክልኝ በአክብሮት እጠይቅሀለሁ ፡፡ በማለት በሚላክለት ሰው አድራሻ ቦታ የእግዚአብሔርን ስም በላኪው አድራሻ ቦታ ደግሞ የራሱን ስም በመጻፍ የወላጆቹን ቤት አድራሻ ያስገባና ደብዳቤውን በፖስታ አሽጎ ያስቀምጠዋል፡፡አንድ ቀን ፖስተኛው ሰው ሲመጣ ይጠብቅና ደብዳቤውን ወደ እግዚአብሔር እንዲልክለት በአደራ ይሰጠዋል፡፡



ፖስተኛውም በልጁ ሁኔታ እጅግ በመደነቅ ደብዳቤውን ተቀብሎ በመሄድ ጉዳዩን ለፖስታ ቤቱ ኃላፊ ያስረዳል፡፡ የፖስታ ቤቱ ኃላፊም ደብዳቤውን በማየት ይገረሙና በፕሮቶኮል ደረጃ ወደ አሜሪካን ፐሬዚደንት እንዲላክለት መመሪያ ለሠራተኞች ይሠጣሉ፡፡ በዚህ መሠረት የልጁ ደብዳቤ ፐሬዘዳንቱ ቢሮ ይደርሳል፡፡ ፕሬዘዳንቱም በደብዳቤው ይገረሙና ‹ ይህ ልጅ ዕድሜው ገና ሰባት ነው ፡፡ ለምን በዚህ እድሜው ከወላጆቹ ተደብቆ ይህንን ያህል ገንዘብ ሊፈልግ ቻለ ? መጠየቁ ስህተት ባይሆንም መቶ ብር ለህጻን መስጠቱ ግን ሊያመጣበት ከሚችለው ችግር አንጻር ሲታይ አግባብ አይሆንም በማለት የአምስት ዶላር ቼክ ብቻ እንዲላክለት ትዕዛዝ ይሠጣሉ፡፡ 


በዚህ መሰረት በፕሬዘዳንቱ ቢሮ አድራሻ ለሕጻኑ ልጅ የደብዳቤው ምላሽ ይደርሰውና እጅግ በሞቀ የደስታ ስሜት ፖስታውን ሲከፍተው የአምስት ብር ቼክ ብቻ ያገኛል፡፡ በዚህ ጊዜ በጣም በመናደድ እግዚአብሔር ሆይ አንተን አመስግንሀለሁ ፡፡ የጠየኩህን ገንዘብ አንተ ብትልክልኝም የአሜረካ መንግሥት ግን ዘጠና አምስት ዶላሩን በቀረጥ ስላስቀረብኝ እጅግ አዝኛለሁ፡፡›በማለት ሀዘንና ደስታውን አንድ ላይ ገለጸ ፡፡

3 comments:

  1. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

    መልእክቱ እሚከፋ ባይሆንም ሰላም ተዋህዶ ከስሟ አንጻር ያረጀ ቀልድ ይዛ መውጣት የለባትም ይህን ጆክ በሌላ መልክ አውቀዋለሁ ስለዚህ ብዙም አላስደሰተኝም በዚህ ወቅት ስለ ቤተክርስቲያን እውነታዎች ብዙ የሚጻፍ ነገር አለ ብትጽፉ ደስ ይለኛል አለበለዚያ ስም ብቻ እንዳይሆን

    አምላከ ቅዱሳን ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን

    ReplyDelete
  2. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን።
    ሰላም ተዋህዶ አዘጋጆች ጥሩ ዝግጅት ታቀርባላችሁ አስተያየት የሰጡት እሳቸው ቢያውቁትም
    እኔ ግን ይህ ያቀረባችሁት የልጁ ታሪክ አስተማሪ ሆኖ አግቼዋለሁ።ለብዙ ሰዎችም ነግሬያቸዋለሁ በጣም ደስ ብሎቸው ሰምተውት ሣቅ እንደሰማይ በራቀበት አገር ስቀንበታል
    ተምረንበታል። ሁሌ ድርቅ ያለ ነገር ባለማቅረባችሁ ደስ ትሉኛላችሁ በርቱ።ሁሉንም ሰው ላታሰደስቱ ትችላላችሁ።

    ReplyDelete
  3. NEGERU TIRU NEW GIN YETENEGERE NEGER NEWNA MELKITU YIKEREWAL YEMTTSIFUT NEGER MELKAM TIMHURT YALEW BIHON MELKAM NEW BERTU MENFESAW NEGER MENAGERNA METSAF GIRUM NEWNA LEHULACHINIM TSELYU

    ReplyDelete

አስተያየት