በከሳሾችና በተከሳሹ የአስተዳደር ቦርድ አባላት መካከል የነበረው የፍርድ ቤት ጉዳይ በአስተዳደር ቦርዱ አሸናፊነት መጠናቀቁን ትናንት ታህሳስ 13 2002 ዓም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአስተዳደር ቦርዱ ለፈጸማቸው ጥፋቶች ሁሉ መከላከያ ያደረገው ያለ ሕዝቡ ድጋፍና ተሳትፎ ያወጣው የአባላትን መብት የሚረግጠውና የቦርድን ሥልጣን በከፍተኛ ሆኔታ የሚያጠናክረው አዲሱ ባይሎው ነው፡፡ ይህም በፍርድ ቤቱ ዳኛ በከባድ ሁኔታ የተተቸና የተነቀፈ ቢሆንም በመጨረሻ ላይ ግን በድሮው ባይሎ አንቀጽ 11 ቁጥር 1 ላይ የተቀመጠው የእንግሊዘኛው አረፍተ ነገር ሕግን የማሻሻል መብት ለሕዝብ ቢሰጥም በአንቀጽ 11 ቁጥር 2 ላይ ያለው አረፍተ ነገር ደግሞ ያንኑ የሕዝብ ደንብ የማሻሻል ሥልጣን ለቦርድ እንዲሠጥ ተደርጎ ስለተቀመጠ በዚህ መሠረት ሌሎች የክስ ዝርዝሮችን ሁሉ ባለመቀበል ዳኛው ፍርዱን ለአስተዳደር ቦርዱ ፈርዷል፡፡
እንግዲህ የእሳት ፍም የሚያነደው እንጨት እስከሚያገኝና እሳት ሆኖ እስኪታይ ድረስ በአመድ ውስጥ ተቀብሮና ተዳፍኖ እንደሚቀመጥ ሁሉ እውነትም ለጊዜው ያለአግባብ በሆነ አመድ ፍርድ ውስጥ ተዳፍናለች፡፡ ጊዜዋን ጠብቃ ደግሞ ትወጣለች፡፡ ለማንኛውም ጉዳዩን በይግባኝ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የማቅረብና እውነትን ከአመድ ውስጥ የማውጣት መንገድም እንዳለ ማወቁ ተገቢ ነው፡፡
እስከዚያው ድረስ ግን ለቦርዱ መልካም የጌትነት ጊዜ እየተመኘን አስቀድሰውና 30 ብራቸውን ከፍለው ከመሄድ በቀር ቀና ብለው ቦርድን በሁለት አይናቸው ለመመልከት እንኳን መብት ለሌላቸው የቤተክርስቲያኑ አባላት ሁሉ መልካም የሎሌነት ጊዜን እንመኛለን፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት