ለቤተ ክርስቲኒቱ የወደፊት እድገትና አንጻራዊ ሰላም መስፈን እንዲሁም ለተፈጠሩት መጠነ ሰፊ ችግሮች በጋራ ለመወያየትና የመፍትሔ ሃሳቦችን እየፈለጉ ከመሰንበት ይልቅ የሥልጣን ሱስ ያሰከራቸው ሂሳብ ሹምና ደጋፊዎቻቸው ዛሬም የእልህ ሥራቸውን ቀጥለውበታል፡፡
በሂሳብ ሹሙ በእጅ አዙር እየተመራ ያለውና የወላጅ ኮሚቴ ነኝ በማለት የወሮ መብላት ሥራን በሰፊው የተያያዘው የአመጸኖች ቡድን ቤተ ክርስቲያኒቱን ጨርሶ የዘር ልዩነት ጎልቶ የሚንጸባረቅባትና አባላቱም ከክርስትና ዜግነታቸው ይልቅ ወንወዛቸውንና የተወለዱበትን ቀዬና መንድር እያመለኩ እንዲሰባሰቡ እያደረገ ነው፡፡
የሂሳብ ሹሙና ቡድናቸው አስተዳደሩን ከወልቃይቶች እጅ አላቀን በወለዬዎች እጅ ማስገባት አለብን በማለት ሥውር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጡ፡፡ በአንድ ወገናቸው ጉራጌ በሌላው ወገን ደግሞ ወለዬ መሆናቸው የሚነገርላቸው ሂሳብ ሹሙ ደጋፊን በማብዛት የሊቀመንበርነት ቦታውን ለመያዝ ይህ አዲሱ እስትራቴጂያቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡
በሌላም በኩል ደግሞ በኅዳሩ ምርጫ በትረ ጻሐፊነት ስልጣኑን ለመረከብና የሂሳብ ሹሙ መነጽርና ቀኝ እጅ ለመሆን ቋምጠው የነበሩትና ያልተሳካላቸው ወ/ሮ ሰሎሜም በወሎ ሀገር ተወላጆች ማኅበራቸው ውስጥ ጉዳዩን ቀስ ብለው በማስገባትና በማያያዝ የድጋፍ ሠጪ ማሰባሰብ ሥራ እየሠሩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ለብዙ አመታት በወልቃይቶች የዘረኝነት መንፈስ ይበሳጩና ይናደዱ የነበሩ ገንዘብ ያዡም ይህ የሂሳብ ሹሙ አካሄድና አሠራር የጎንደር ዜግነት ያላቸውን ባለቤታቸውን ከወልቃይቶች እጅ የሚያወጣና የሚያለያይ ጥሩ መንገድ ሆኖ በመገኘቱ ሚስታቸውን ይዘው እዚያው ተጠቃለዋል ፡፡ በአንጻሩም ደግሞ በትውልዳቸው ወለዬ የነበሩት የደብሩ ጸሐፊም የሚስታቸውን የጎንደር ዜግነት ክብርን ለመጠበቅ ሲሉ ወዳጃቸው የነበሩ የሂሳብ ሹሙን ትተው ከሊቀመንበሩና ከወልቃይት ተወላጆች ጋር መሰለፋቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም ‹ ከሃዲ › በማለት የሂሳብ ሹሙ ቀደም ብለው ይጽፉበት በነበረው ሰንበት በተባለው ብሎጋቸው ላይ መርገማቸው ይታወሳል፡፡
ሁለቱም ካህናት ( አባትና ልጅ ) ለብዙ ዓመታት አብረዋቸው ከኖሩት ከሊቀመንበሩና ከወልቃይት ተወላጆች ጋር ያላቸውን ወዳጅነት ትተው ወደ ሂሳብ ሹሙ የኮበለሉት በወሎ ሀገር ተወላጅነታው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡
እንግዲህ ይህ ዘመን ያለፈበትንና ለቤተክርስቲያኒቱ የማይጠቅመውን ኋላ ቀር አሠራር ስወግዶ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ዜጎች ሁሉ መብትና ሃይማኖት የሚከበርባትና ቤተ ክርስቲያኒቱ ስብሐተ እግዚአብሔር በሥርዓቱ የሚደርስባት ቤት ክርስቲያን እንድትሆን ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ያስፈልጋል፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት