የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ከመሠረቱትና ቤተክርስቲያኗም በሃገሩ ደምብ መሠረት እውቅናን እንድታገኝ ከፈረሙት 3 ሰዎች መካከል አንዱና ዋና ነኝ የሚሉት አቶ ዮሴፍ ረታ ክሱን ለመከላከል ሊረዳን ይችላል ብለው የቦርድ አባላቱ ያመኑበትንና ከክሱ ጋር ግንኙነት የሌለውን የማኅበረ ቅዱሳንን ስም የሚጎድፍ አዲስ ደብዳቤን ለፈርድ ቤቱ በስማቸው ፈርመው መላካቸው የሰሞኑ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ከርሟል፡፡
የቤተክርስቲያን አባልነት መብታችን ተደፈረ ብለው ክስ ከመሠረቱት አባላት ውስጥ የቤተክርስቲያኗ መሽራቾችም በዋናነት እንደሚገኙበት እየታወቀ ጉዳዩን ከማኅበረ ቅዱሳንና ከሃይማኖት ጋር አያይዞ ፍርድ ቤቱን ለማደናገርና የክሱን መንገድ አቅጣጫ ለማስቀየር መዳከር እሚሠሩትን እዳለማወቅ ይቆጠራል በማለት አስተያየት የሚሠጡም አሉ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓላመውና ከአገልግሎቱ ሂደት እንደምንረዳው በጠንካራ የሥራና ሃይማኖት መሠረት ላይ የቆመ በመሆኑ ብዙ አሉባልታዎችንና የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን በእግዚአብሔር ኃይል እየጣለ እዚህ የደረሠ ትልቅ ማኅበር ነው፡፡ ኃይሉም ብርታቱም ሠው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው፡፡ ከሠው ከሆነ ይጠፋል ከእግዚአብሔር ከሆነ ግን ይኖራል ፡ እንደተባለ የእነ አቶ ዮሴፍና የመሰሎቻቸው የሀሰትና የሥም ማጥፋት ዘመቻ አገልግሎቱን የሚገታው አለመሆኑም ሊታወቅ ይገባል፡፡
ከደብዳቤው ይዘት እንደምንረዳው የአቶ ዮሴፍን አላዋቂነትና በስም እንጂ በተግባር የሌሉበትን የምክትል ሊቀመንበርነት ስማቸውን በመጠቀም እንደ እቃ የተጠቀመባቸው ሌላ አካል እንዳለ እንረዳለን፡፡ ምክንያቱም በአሜሪካን አገር የቆዩት ከ30 ዓመታት በላይ ቢሆንም ከሀገሩ ኑሮና ሥልጣኔ እንዲሁም ትምህርት ጋር እስካሁን ገና ያልተዋወቁና ያልተዋሃዱ ናቸው፡ የሚሉት የኑሮ ጎረቤቶቻቸው ዮሴፍ በዚህ ድራማ ውስጥ አንገቱን ለማስግባት የተነሣሣው ለምን በእርጥብ እንጨት ተመሠልኩ በሚል ቁጭትና እልህ ነው ብለው ይናገራሉ፡፡
No comments:
Post a Comment
አስተያየት