Tuesday, December 29, 2009

የኔ ናርዶስ የኔ ቤዛ


የኔ ናርዶስ የኔ ቤዛ
በመዓዛው ልቤን ገዛው፡፡
ያንን መዳን ተመልክቼ
ተከተልኩት ሁሉን ትቼ፡፡
እንቅልፍ የለኝ በአልጋዬ
ፊቴም ታጥቧል በእንባዬ፡፡
በውድቅቱ ነቅቻለው
እርሱን ብዬ ወጥቻለሁ፡፡……

Wednesday, December 23, 2009

እውነት የረመጥ እሳት ሆነች፡፡

በከሳሾችና በተከሳሹ የአስተዳደር ቦርድ አባላት መካከል የነበረው የፍርድ ቤት ጉዳይ በአስተዳደር ቦርዱ አሸናፊነት መጠናቀቁን ትናንት ታህሳስ 13 2002 ዓም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Saturday, December 19, 2009

አቶ ዮሴፍ ለፍርድ ቤቱ ላኩ ስለተባለው ደብዳቤ - የሕዝብ አስተያየት

የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ከመሠረቱትና ቤተክርስቲያኗም በሃገሩ ደምብ መሠረት እውቅናን እንድታገኝ ከፈረሙት 3 ሰዎች መካከል አንዱና ዋና ነኝ የሚሉት አቶ ዮሴፍ ረታ ክሱን ለመከላከል ሊረዳን ይችላል ብለው የቦርድ አባላቱ ያመኑበትንና ከክሱ ጋር ግንኙነት የሌለውን የማኅበረ ቅዱሳንን ስም የሚጎድፍ አዲስ ደብዳቤን ለፈርድ ቤቱ በስማቸው ፈርመው መላካቸው የሰሞኑ መነጋገሪያ ርእስ ሆኖ ከርሟል፡፡

Wednesday, December 16, 2009

እግዚአብሔር የድሆችን እንባ በመስጠት ያደርቃል !

እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጆች ከሚሠጣቸው ብዙ ጸጋዎች መካከል አንዱ ድህነት  ነው፡፡ ስለ ድህነትና ድሃ ሆኖ ስለመወለድ ብዙ መጻፍ ቢቻልም ነቢዩና እናቱ የሚተርኩት የድህነት ሕይወት ግን ከጽሑፉ በላይ ልብን የሚነካ ሆኖ ስላገኘነው ታደምጡት ዘንድ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን 50 ሎሚ ለ50 ሰው በሚለው ዝግጅቱ ያቀረበውን ወስደን አቅርበነዋልና ይህን በመጫን ያድምጡ ፡፡ 

Tuesday, December 15, 2009

ንጋት ቀትርና ምሽት


ሊነጋ ሲል ይጨልማል!ግን ለጊዜው ነው፡፡ ትንሽ ቆይቶ ጎሕ ይቀዳል፡፡ ውጋገኑን ተከትሎ ደግሞ ይነጋል፡፡ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ጸሐይ ትወጣለች ፡፡በዘገምተኛ ጉዞዋ ጸሐይም ቀስ እያለች ምድርንና በላይዋ ያሉትን ሁሉ እያሞቀች ወደ ቀትር ትደርሳለች፡፡

Saturday, December 12, 2009

የዘር ምልመላ በቤተክርስቲያናችን !

ለቤተ ክርስቲኒቱ የወደፊት እድገትና አንጻራዊ ሰላም መስፈን እንዲሁም ለተፈጠሩት መጠነ ሰፊ ችግሮች በጋራ ለመወያየትና የመፍትሔ ሃሳቦችን እየፈለጉ ከመሰንበት ይልቅ የሥልጣን ሱስ ያሰከራቸው ሂሳብ ሹምና ደጋፊዎቻቸው ዛሬም የእልህ ሥራቸውን ቀጥለውበታል፡፡

Tuesday, December 8, 2009

አሸናፊው ማና ነው ? ተሸናፊውስ ?

ከላይ በርእሱ የተቀመጠውን ጥያቄ በትክክል የሚመልሰው የፍርድ ቤቱ ውሣኔ ነው ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች በቦርድና በከሳሾች መካከል የተጀመረውን ክስ አስመልክተው በሚሰጡት አስተያየት አሸናፊና ተሸናፊ የለም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ በፍርዱ ፍጻሜ የግድ አንዱ ይሸነፋል ሌላው ደግሞ ያሸንፋል፡፡

Monday, December 7, 2009

ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ ! ዮሐ 14 ፡ 1

እውነት ሕይወት ነው ! ሕይወትም እግዚአብሔር የሆነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡በእርሱ የሚያምን ክርስቲያን ሁሉ ልቡ አይፈራም ! አይሸበርም፡፡ እውነት የሌለው ግን ሕይወት የሆነ እግዚአብሔር በውስጡ የለውምና ይፈራል ! ይሸበራል፡፡