የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲያቆን አንዱአለም መሪነት ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ እየሔደ ነው!
‹ከሥጋው ጾመኞች ነን ከመረቁ አውጡልን› በሚል አቋም የኢትዮጵያውንም ሆነ ስደተኛ ሲኖዶስ ነኝ ብሎ አሜሪካ የተቀመጠውን አንቀበልም ፤ ነገር ግን የምንከተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት ነው ፤ በማለት የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በዚህ አቋሙ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያኑ የቀድሞ አስተዳደር ቦርድ አቋሙን እንደገና በማሻሻል ከጥቂት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ አይሰደድም፤ሲኖዶስና መንበሩ ያለው አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ነው፡፡ሕጋዊው ፓትርያርክም አባ ጳውሎስ ናቸው፡፡ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንም የኢትዮጵያውን ሲኖዶስ ሕጋዊነቱን ያምናል፤ ይቀበላል ፡፡ ነገር ግን አባ ጳውሎስ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ይልቅ በማይመለከታቸውና ሃይማኖቱ በማይፈቅድላቸው ሁኔታ የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ ተግባር ወኪልና አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ በመሆናቸው አስተዳደራቸውን አንቀበልም ፤ በማለት የቆየ አስተዳደር ነበር፡፡
ይሁን እንጂ በአዲስ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ምርጫ ወቅት የተሐድሶ መንፈስን የሚደግፉና አንዳንድ የዘር አድሎ ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ተቀላቅለው በመግባታችውና አስተዳደሩን በመቆጣጠራቸው የነበረውን አንጻራዊ ሰላም በማደፍረስ የቤተክርስቲያኑን ችግር አባብሰውታል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ የሚያገለግሉ ካህናት ቦርዱ ለሚፈጽመው ስህተትና ጥፋት ድጋፍ የማይሠጡና በአውደ ምሕረቱ ላይ ቦርዱን የማያመሰግኑ ከሆነ ፤ በምትኩም ተሐድሶን የሚነቅፉና ጠበቅ ያለ የሃይማኖትና የሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ትምህርቶች ከሕይወት ጋር አያይዘው የሚያስተምሩ ከሆነ የቦርዱ ጥርስ ውስጥ ይገባሉ፡፡አሊያም በቀይ ካርድ ይባረራሉ፡፡
እውነተኛ ካህናትን በማሰቃየትና ከሥራ በማፈናቀል ፤የሕዝብንም ድምጽ በማፈንና በመናቅ ፤ ፖሊስ በመቅጠርና ምዕመናንን በማስደብደብ ያለማጋነን ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት የዳላሱን ቅዱስ ሚካኤል የአስተዳደር ቦርድን የሚያህል የለም ፡፡ ይህም የቅርብ ጊዜ ትዝታና ዓለም ሁሉ በቪደዮ መስኮት ያየው ሐቅ በመሆኑ የሚረሳ አይደለም፡፡ የዚህን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቦርድ ኢሃይማኖታዊና ኢክርስቲያናዊ ተግባር በመረዳት በሃይመኖታቸውና አቋማቸው ጠንካራ የነበሩ ካህናትና የደብሩ ሰንበት ተማዎች ለቀው መውጣት ቦርዱን እንዳሻው እንዲያደርግ ረድቶታል ፡፡
በካናዳ ስደተኛው ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የነበረውን ደላላ (ለቃሉ አጠቃቀም ይቅርታ) ዲያቆን አንዱአለምን ቀጠረ፡፡ እርሱም አስተዳደሩን በውዳሴ ከንቱ ሰማይ እያደረሰ ቦርዱም ያለዲያቆን አንዱአለም አዋቂ ሰው የለም እያለ ሁለቱም እርስ በእርሳቸው እየተፎጋገሩ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ትልቁን የቁማር ጫወታ ተያይዘውታል፡፡
ዲያቆን አንዱ አለም ለልጆች አስተማሪ ተብሎ የተቀጠረ ይሁን እንጂ በዋነኛት እየሠራው ያለው የዳለስ ቅዱስ ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የተሐድሶ መንፈስ ስሜትን ማርካትና ቤተ ክርስቲያኑን በስደተኛ ሲኖዶስ ሥር እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም
1.የመጀመሪያ መንገድ ጠረጋ ሥራውን ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ቦርድ መካከል ሁለት የቦርድ አባላት ከሦስት ወራት በፊት በካናዳ ካልግሪ ከተማ በተደረገው የስደተኛው ሲኖዶስ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በምስጢር ተኝተው በቅድመ ጉዳዮች ላይ እንዲነጋገሩ ሁኔታዎችንን በማመቻቸት ከፍተኛ ሚናን ተጫውቷል፡፡ ይህ ተግባር በዲያቆን አንዶአለምና በጥቂት ቦርድ አባላት መካከል የተያዘና ጥያቄ እንኳ ቢነሣ ማስተባበያ ለመስጠት የተዘጋጀለት ጉዳይ በመሆኑ አንዳንዶቹ የቦርድ አባላትም ለጉዳዩ ባዕዳን መሆናቸው ታውቋል፡፡
2.ከሌሎች መሰል ጓደኞቹ ጋር በፕሮቴስታንታዊ አስተምሕሮው ተከሶ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በተሠየመ የሊቃውንት ጉባዔ ጉዳዩ በመረጃ ቀርቦ ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበትንና እራሱም ጥፋቱን ያመነውን ተሐድሶ መምህር ልዑለ ቃልን ጉባኤ አዘጋጅቶ በዳላስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መጋበዙ ዲያቆን አንዱ አለም ለሃይማኖቱ መጠበቅ ግዴለሽና የሚሠራው ለሆዱና ለገንዘብ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ ለመውሰደ ሥራ መጀመሩን የሚያሳይ ነው፡፡
3.ነፍሶቻቸውን ይማረውና ብጹዕ አቡነ መቃሬዎስ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ፤ መጋቤ ብሉይ ሠይፈ የጉባኤው ጸሐፊ ሆነው አሁንም በሕይወት ባሉት ታላላቅ አባቶች በእነ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤልና ሌሎችም ሊቃውንት አባቶች ፊት በጉባዔ ቀርቦ ሲጠየቅ ከድንጋጤው የተነሣ ላብ አስጥሞት መናገር እስኪያቅተው ድረስ ሲርበተበት የነበረውን መምህር ልዑለ ቃልን ‹ ‹ እንኩዋን ሲኖዶሱ ሊያወግዘው ይቅርና በጉባዔያቸው ላይ ቀርቦ እንዳልተጠየቀ እኔ አውቃለው፡፡› በማለት አንዱአለም የሠጠው ዐይን ያውጣ የሐሰት ምስክርነት እርሱን ራሱን ብቻ ሳይሆን የቆመበትንም የወንጌል ዓውደ ምህረት ጭምር በውሸት ያረከሰ እጅግ ውሸታምና ፍጹም እምነት የማይጣልበት ሣሙና የሆነ ሰው መሆኑን አረጋግጧል፡፡የሊቃውንት ጉባኤ እኮ እንዲህ ዓይነቱን ሥራዎች እንዲሠራለት ሲኖዶሱ እራሱ ያቋቋመው ሕጋዊ ዕውቅና ያለው ጉባዔ ነው ፡፡ በውግዘትና ኑፋቄ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሊቃውንትን ጉባዔ ሳያማክርና የውሳኔ ሃሳብ ከዚያ ሳያገኝ በግብታዊነት እንደማይወስን ዲያቆን አንዱዓለም ወይ አላወቀውም አሊያም በትክክል የተሐድሶ አራማጆችን ተግባር አምኖበት ሽፋን ለመስጠት በዓላማ የተናገረው ነው፡፡ይሁን እንጂ አንዱዓለም ችግር ያለባቸውን መምህራን በቅዱስ ሚካኤል እየጋበዘ ቢያመጣም ከራሱና ከሚመጡት መምህራን ፊት ላይ የሚነበብ ውጥረት ፤ውስጣዊ ፍርሃትና አለመረጋጋት መታየቱን በጉባዔው የሚገኙ ታዛቢ ምዕመናን ይናገራሉ ፡፡ ግልጽነት የሌለውን የድብቅ ሥራ የሚሠራ ሰው ነፍሱ የሚሠራውን ሥራ ልክ አለመሆን ስለምትነገረው ይጨነቃል ፤በውጪ ሰላመዊ ለመምሰል ይሞክራል እንጂ ውስጡ ግን ሰላም አይኖረውም፡፡
4.ዲያቆን አንዱዓለም ከስደተኛው ሲኖዶስ አብያተ ክርስቲያናት ለጉባዔ የሚጠራቸውን መምህራን ስማቸውንና የሚመጡበትን ቦታ በጉባዔው ማስታወቂያ ፖስተሮች ላይ አያወጣም፡፡ ይህን የሚያደርገው ሕዝቡ የመምህራኑን ማንነት ቀድሞ መርምሮ እንዳይረዳና ለምን ? በሚል ጥያቄ እንዳያፋጥጡት በመስጋት ነው፡፡ይሁን እንጂ አልቀረለትም፡፡ ‹ ለምሳሌ ልዑለ ቃልን ጨምሮ በወር ልዩነት በተደረጉ ሁለት ጉባኤያት የተጋበዙት መምህራን ስማቸውና የመጡበት ቦታ አልተገለጸም፡፡ ለጉባዔ የሚጋበዙ መምህራንን ለምን በፖስተር መግለጽ እንደማይፈልግ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ በሆኑ አንዳንድ ምእመናን ሲጠየቅ የሰጠው መልስ ‹እኛ የምንፈልገው አዋቂ መምህራንን እንጂ ታዋቂ መምህራንን አይደለም ›በማለት ተመጻድቋል፡፡ ይህ ስህተት ያለበት ንግግሩ ብዙ ትንተና ሊሠጥበት የሚያስችል ቢሆንም በዚሁ እንለፈው፡፡ አንዱአላም ግን አሁንም በንግግሩም እየሳተ ነው፡፡
ይህ ዓይነቱ የአንዱአላም አሠራር እየሔደ ያለበት ሥውር መንገድ ለአጥቢያው ምእመናን ከጥቅሙ ይልቅ እጅግ ከፍተኛ የሆነ አደጋና ጉዳት አለው፡፡
አንደኛ ሥርዓት ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ የ3000 ዘመን ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ ያለችውን ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ የለችም እኛ አሜሪካ ይዘናት መጥተናል፡፡ ሲኖዶሷም ያለው አሜሪካ ነው፡፡ በማለት ቤተ ክርስቲያኒቱንና ሃገሪቱን የካዱ ጥቂት ጳጳሳት ለጊዜው አባባሉን ለፖለቲካ ዓላማቸው ቢጠቀሙበትም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ግን ይህ ተግባር ውግዘትን የሚያስከትል በመሆኑ ስለዚህ የአሜሪካው ስደተኛ ነኝ ባይ ሲኖዶስ በሕጋዊው የኢትዮጵያው ሲኖዶስ የተወገዘና የተለየ ሆኖአል ፡፡ ከዚህ አንጻር አንዱአለም የዳላስ ቅዱስ ሚካኤልን ምእመናንን ወደ ውግዘቱ በረት ለማስገባት እየሠራ መሆኑ ለምእመናኑ ትልቅ አደጋ ነው፡፡
ሁለተኛ- የስደተኛውን ሲኖዶስ ከላላ አድርገው የተሐድሶን ሥራ በሥውር የተያያዙ በአካላቸው ኦርቶዶክስ በልባቸው ግን ፕሮቴስታንት የሆኑ አያሌ መምህራነ ወንጌልና መነኮሳት በኢትዮጵያም በአሜሪካንም ውስጥ አሉ ፡፡ አንዱአለምም አሁን የተያያዘው እነዚህን መምህራን ዳላስ እያስመጡ ምእመናኑ የፕሮቴስታንትን ትምህርትና መምህራኖችን እንዲለማመዷቸው ማድረግ ነው፡፡ እስካሁን እነዚህን መምህራን ባዘጋጃቸው ሁለት ጉባኤያት በየተራ አስመጥቶ የሕዝቡን ስሜት ለመሰለል ሞክሯል፡፡
በሦስተኛው ጉባዔ ግን በፕሮቴስታንታዊ ትምህርታቸው የለየላቸውን ተሐድሶ አባ ወልደ ትንሣኤን ለማስመጣት ከቦርድ ጋር ስምምነቱን ጨርሷል፡፡ ይህም ከመስቀል በዓል ጀምረው ለሦስት ተከታታይ ወራት ያህል ስለ ስደተኛው ሲኖዶስ አስፈላጊነትና ፒያኖን በመጠቀም መዝሙርን እንዴት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መዘመር እንደሚቻል ከሎስ አንጀለስ ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ተሞክሮአቸው አንጻር ለዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ምዕመናን ለማስተማር እንደሚመጡ ከቅርብ ምንጮች የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡
አባ ወልደ ትንሣኤ ከዛሬ 12 ዓመታት በፊት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አውደ ምሕረት ላይ የእመቤታችንን ክብር የሚያጣጥል ፕሮቴስታንታዊ ትምህርት በማስተማራቸው ምክንያት በካህናትና በምዕመናን በኩል በገጠማቸው ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ መሠረት ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛ እንዳይመጡ ታግደው መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ጊዜ የሠጠው ቅል ድንጋይ ይሠብራል እንዲሉ › በቤተክርስቲያኒቱ ላይ እንደፈለጋቸው ለመሆንና ለመፈንጨት ጊዜ ያገኙ የቦርድ አባላት ጧፍ ይዞ እፊት እፊት ከሚመራቸው ዲያቆን አንዶአለምና ከወደፊቱ አስተማሪያቸው ከአባ ወልደ ትንሣኤ ጋር በመሆን ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ፈቃድ ቤተክርስቲያኗን ቀስ ብለው በዘዴ ለስደተኛው ሲኖዶስ ለመስጠትና የተሐድሶ መፈንጫ ለማድረግ ነው፡፡
በተያዘው መርኃ ግብር መሠረት አባ ወልደ ትንሣኤ ከመስቀል ጀምረው እስከ ሕዳር ሚካኤል ድረስ በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በግልጽና በሥውር ሲያስተምሩ ይሰነብታሉ፡፡ አንደኛው የስደተኛውን ሲኖዶስ አስፈላጊነት - በግልጽ ፡፡ ሁለተኛ የቤተ ክርስቲያኒቱን የተሐድሶ ጉዳይ በሥውርና በሰም ለበስ የስብከት ዘይቤ፡፡ ከዚያ በኋላ በዲያቆን አንዱአለም በተከፈተላቸው በር ፤ በአባ ወልደ ትንሳኤ በተጠረገላቸው መንገድ ሁለት የስደተኛው ሲኖዶስ ጳጳሳት ለኅዳር ሚካኤል ክብረ በዓል ይመጣሉ ፡፡ ከዚያስ ? ከዚያማ The mission is Over ! ማኅሌታዊው ፤ ሰባኪውና ቀዳሹ ካህን አባ ምሕረት ዘውዴስ ምን ይሆናሉ ? እርሳቸውማ በቢጫ ካርድ ስላሉ አባ ወልደ ትንሣኤ ሲመጡ በቀይ ካርድ ይሰናበታሉ፡፡ ጸባያቸውን አሳምረው ፤ቦርዱን አወድሰው፤ ጳጳሳቱንም ቄጤማ ጎዝጉዘው ከተቀበሉ ደግሞ የደብሩ አለቃ ሆነው ይሾማሉ ፡፡
ይህ እንዳይሆን እውነተኛ ነን የሚሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ?
በፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ ፡፡
አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ፡፡
የሚለውን ተረት ምን ማለት እንደሆነ ደጋግሞ ማሰብ ነው ፡፡አንድ ችግር ከደረሰ በኋላ ከመጮህና ከመቆጨት ይልቅ አሁኑኑ ‹ሳቃጠል በቅጠል ማጥፋት ነው፡፡› ባለፈው ሐምሌ 30 2003 ስለቤተ ክርስቲያናችን ውቅታዊ ሁኔታ መነጋገር እንፈልጋለን ብለው ቦረዱን ስብሰባ እንዲጣራ ቁጥራቸው 60 የሚደርሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ ይሁን እንጂ ቦርዱ ደጋፊዎቹን ወደ ስብሰባው እንዳመጡና ኮረሙ እንዳይሞላ አድርጎ ስብሰባውን ቢበትነውም ፤አባላቱ ግን እኛ አንበተንም ፤ ያለነው ተወያይተን አቋማችንን ለቦርዱ ማሳወቅ አለብን በማለት ያለውን ችግር አንስተው ተያተዋል፡፡ አሁንም ተቆረቋሪ አባላትን በማብዛትና ድምጽን ያለፍረሃት በማሰማት በቦርዱ ላይ ጫና ማድረግና ያሰበውን ዕቅዱ ሽባ ማድረግ የመጨረሻና ብቸኛ መፍትሔ ነው፡፡ ያም ካልሆን የስደተኛውን ሲኖዶስ አንቀበልም የሚሉ ምዕመናን ቁጥራቸውን አስተባብረው ሕጋዊ የንብረት ጥያቄ ለፍርድ ቤት ማቅረብ ብቻ ነው፡፡
ለማንኛውም የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ምእመናን የደረሰባችሁን ፈተናና ግፍ ሁሉ ቆጥሮ እግዚአብሔር የሚበጀውን መፍትሔ እንዲሰጣችሁ ሰላም ተዋሕዶ መልካም ምኞቷን ትገልጻለች፡፡
አንድ ያልገባኝ ነገር አለ አባ ወልደ ትንሣኤ ሆነ ሌሎቹ መምህራን የሚአምኑት አምላክ እመቤታቸን ቅድስት ድንግል ማርያም እርሱን ስሙት ያለችውን አምላክ አይደለም ወይስ ሌላ ኢየሱስ አለ። እኔ ግን አንዳንዲ ሳስበው ይህ ስም አጥፊ ግሩፕ በሐዋርያት ዘመን ቢኖር ኑሮ ሐዋርያትን ታድሶ የሚል ይመስለኛል። ለምን ብንል ሐዋርያት እድሜ ልካቸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው የሰበኩት ያስተማሩት። እባካችሁ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ክሱን ተውትና ኢየሱስ ክርስቶስን ስበኩት።
ReplyDeleteዲ/ን ወንድወሰን
Deacon Wondwosen,
ReplyDeleteI don't know how you became a Deacon or you just pretending to be one.
Of-course, God is one but the way how people worship him is different and that is why there are millions of religions in this world which is against what God says (Ephesians 4:5 one Lord, one faith, one baptism)
Do you think our Lord Jesus Christ is God or do you worship him like the Protestants (Tehadeso Menfafiqan) believe him as ኣማላጅ (intermediary between God and human being?) or do you believe Jesus Christ is a prophet of God?
I don’t know about you but I believe Jesus is God and he does not intercede to any one because there is nothing in this world he can not do. There is only one truth and one Jesus but if you tell me Jesus is a prophet or ኣማላጅ we are worshiping different God and the one you are believing is the Anti-Chris (that is what the protestant believe)
Do you think the protestant respect the mother of God as she should be? Or do you believe like Protestants believe she had other sons besides Jesus? And do you believe she remained a virgin with the birth of Christ (Matt. 1:23, Luke 1:27, 23:53) or she did not? Don't you see any difference how we worship God and the way we respect his mother, his angels and his disciples?
If you don’t know about Tewahedo, why don’t you learn first before you call yourself a Deacon otherwise do not tell us there are false preachers in our church (አባ ወልደ ትንሣኤ , etc.)
ዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDeleteሊገባህ አይችልም ምክንያቱም እንዲገባሕ ስላልፋልግክ
እኔ የምለው ይሄ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ የለውም እንዴ ተዉ የሚል፡፡ ወንበዴና ቀማኛ ሲወረውና በቁሙ ሲሸጠው ዝም ብሎ ያያል እንዴ ? ምን ጉድ ነው ? አሁንስ የባሪያ ንግድና ጥንታዊ የባርዮሽ ሥርዓተ ማኅበርን አስታወሰኝ፡፡
ReplyDeleteሰላም ተዋሕዶዎች እግዜር ይስጣችሁ፡፡ ጥሩ ምስጢር ነገራችሁን ፡፡ደላላው አንዱአለም ያላችሁት ትክክለኛ ስያሜ ነው ፡፡ ምንም ይቅርታ አያስፈልገውም፡፡ እኛ ስንት ዓመት የደከምንባትን ቤተ ክርስቲያን እርሱ ትናንትና መጥቶ ለስደተኛ ሲኖዶስ ለመሸጥ ካስማማ ትክክለኛ ደላላ ነው፡፡ ይሄን ሰው ግን አንድ ነገር ማድረግ የሚኖርብን ይመስለኛል
ReplyDeleteእንዲት ዲቆን እንደሆንኩ ለጠየከው በእግዚአብሔር ምርጫ እና ፈቃድ ። ለሁሉም ግን ግብዝነቱን ትታችሁ አባ ወልደ ትንሣኤ ሳያመልጧችሁ ከእግራቸው ስር ሁናችሁ ተማሩ። እንደ ምታውቁት ሐዋርያትን ብዙ ሰዎች ሳይጠቀሙባቸው አሳደዋቸዋል ገለዋቸዋልም። እኔም አባ ወልደ ትንሣኤን የዘመኑ ሐዋርያ ጳውሉስ ብየ ስለማምን ከእግራቸው ስር ሁኘ እንደ ጢሞቴዎስ እማራለሁ።
ReplyDeleteእግዚአብሔር ለሁላችን ልቦና ይስጠን
ዲ/ን ወንድወሰን
@ዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDeleteወዳጄ ግብዝ እና ውሸታሙ እኮ አንተ ነህ:: መቸም የመናፍቅ ዲ/ን የትም የለም:: ያለህበት እምነት ካልተመቸህ ውልቅ ማለት ትችላለህ::
ዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDeleteበዛሬ ዘመን በጣም የሚቸግረው ሳይመረጡ አራሳቸውን ዲያቆናት፣ ሰባክያን፣ ካሕናት፣ ጳጳሳት ብለዉ ሠይመዉ በእግዚአብሔር ምርጫ እና ፈቃድ ነው በማለት አያወናበዱ ለሰዎች መሰናክል በመሆን ቅድስት ቤተክርስትያንን የሚያዉኩ በመብዛታቸዉ ነዉ
(1 John 2:19 ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ። )
በጣም ያሳዝናል። መጀመሪያ ጸሐፊው/ዋ እንዲህ አይነት ስም አጥፊ ደብዳቤ ሲያቀርብ ስሙን ወይም ስሟን ቢጠቀስ መልካም ነበር። የሐይማኖት ሰው ሆኖ፤ ሰውን በሐሰት ወንጅሎ ስም አለመጥቀስ ተገቢ አይመስለኝም። ይህን ካልሁ በኋላ ሁለት ሦስት ነገር ላውጣ ከጸሐፊው ግድፈቶች(ስህተቶች) 1- ስለዲያቆን አንዷለም የተባለውን ነው። ለመሆኑ ይህ አዋቂን የማጥፋት፣ ከምድረገጽ እንዳይታይ የማገድ ተንኮል ሐይማኖታዊ ነው ተብሎ ሊታመን ይቻላል? ለማንም ተመልካች ያስገምታል። ዲያቆኑና መምህሩ ከመጡ ወዲህ ቤተክርስቲያናችን ትልቅ መሸሻል አለው። ይህን መሸሻል የማይወድ በሰው አምሳል ቆሞ የሚሄድ ሰይጣን ብቻ መሆን አለበት። ደግሞም አሁን አውነ ተክለሐይማኖት/አረጋዊ ከሄዳችሁ በኋላ ምን ፈለጋችሁና በሌላ ጉዳይ ትገባላችሁ። እባካችሁ እያስተዋላችሁ ወገኖች። ስለሐይማኖት ስንተችም ሆነ ስንጽፍ ከጥላቻ፣ ቂምና በቀል የጸዳ ቢሆን ጥሩ ነው። ለእምነታችንም ለተከታይ ትውልድም መልካም አረያ እንድንሆን መጠንቀቅ ይጠበቅብናል። 2ኛው፣ "አቡነ ጳውሎስ ሕጋዊ ናቸው" ይላል። የትኛው ሕገ ቤተክርስቲያን ፈቅዶ ፕትርክናውን እንደተቀበሉ ጸሐፊው አልጠቀሰም። በዚህ ሐረግ ተራ የፖለቲካ ጽሁፍ በመሆኑ አዝኛለሁ። አቡነ ጳውሎስ ሕጋዊ አይደሉም፣ ቤተክርስቲያን ከምትፈቅደው መንበሩን በሕግ አልተቀበሉም፡ እንዲያውም የፖለቲካው ሐይል በመንደር ልጆቻቸው እጅ ሲገባና፣ ልጆቻቸውም የአማራ ትምክህተኝነትን የጀርባ አጥንት ለመስበር ከመንግስታዊ ስልጣን ብቻ ሳይሆን፣ ከቤተ እምነትም እናሶጣለን ብለው በመወሰናቸው ያገኙት ምድራዊ ስልጣን ነው። በዚህ ነጥብ ከመጠቆም ባለፈ ብዙ ማለት አልሻም። ይህን ያዩ አባቶችና፣ አዋቂ ምእመናን ዝም ብለው እንዳያልፉት ግን አሳስባለሁ። እኔ የጠለቀ እውቀት ስለሌለኝ ማለቴ ነው። 3ኛው፣ እራሱን መሐበረ ቅዱሳን የሚለው ክፍል የሚሰራቸው መልካም ስራወች እያሉና፣ እነዚያን አጠናክሮ ህዝብን በማስተማርና በማገልገል ከማተኮር ይልቅ፣ የሰራውን መልካም ስራ በተበላሸ የስም ማጥፋት ተግባሩ እያበላሽው በመሆኑ፤ የቤተክርስቲያናችን አማንያን ያን ደግ ተግባር ከማየት ይልቅ ክፉው የስም ማጥፋት፣ የመከፋፈል እና አባቶችን የማቃለል ተግባሩን በማየት እየሸሹት ይገኛሉ። ለመልካም ተግባሩ አድናቂ ከሆኑት ይህን አስተያየት ሰጭ ጀምሮ የተለወጠ አስተሳሰብ ስለማህበሩ እንዲኖረን የሚአያደርገው ስራ አመዝኖ ይታያል። ዛሬ ቅዱስ ሚካኤል ከማንኛውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ዲያቆን አንዷለም የሚሰጠው አገልግሎት በእጅጉ የሚመሰገን እንጅ እንዲህ ተጣጥሎ የሚሰገር አይደለም። ታዲያ ለዚህች ቤተክርስቲያን አስባለሁ፣እሰራለሁ በሚል መሰረት የተቋቋመ ድርጅት፣ አገልጋዮቿን ስም በክፉ ማንሳቱ ምን ሊሆን ይችላል? ለአቡነ ጳውሎስ የከፋፍለህ አዋጋው ተግባር አገልጋይነት እንበለው ወይንስ ምን ሊሆን ይችላል? 4ኛው፣ የስደተኛውን ሲኖዶስ ከለላ አድርገው ተሐድሶን እያስፋፉ የሚለው ነው። እረ እባካችሁ እየተስተዋለ። እነዚህ ሁሉ ከአገራቸው በግፍ ተገፍተው የተሰደዱ አባቶችን እንዲህ አይነት ስም መስጠት ለማን ይበጃል? ደግሞስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን እየተከተላቸው ባለበት በዚህ ግዜ ማንን አስደስቶ ማንን ለማስከፋት የሚለውን አቢይ ጉዳይ እንዴት ማሰብ ተሳነ? ይህ ቤተክርስቲያኗ ለሁለት ተከፍላ እንድትቀጥል የሚፈልግ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል። እባክህ ጸሐፊው አንድ ደብርን አጠቃሁ ብለህ ድፍን አማንያንን አትሳደብ። ሀላፊነት ይሰማህ። 5ኛው፣ የዘረኝነቱን ጉዳይ ነው። አመድ በዱቄት ሳቀ ነው የሚሉት? አውነ አረጋይ ቤተክርስቲያንን ለማሳደግ ሌሎችን መሳደብ ያውም በዘረኝነት ፈርክጆ ማለት ነው። እንደጸሐፊው ሐላፊነት የጎደለው ሕዝብን የሚያጋጭ ማለት አልፈልግም። ግን ከተባለ መሆን ያለበት አገር ያለው የፖለቲካና የሐይማኖት መንበሩን የያዙት ናቸው ዘረኞች። ይህ ሐቅ ማንም የሚያውቀው ነው። አቡነ ሞርቆርዮስም የተባረሩ በዚሁ መስፈርት ነው። ታዲያ ብዙሐንን ዘረኛ ለማለት መከጀል አግባብነት የለውምና ይታረም እላለሁ። ይህን ካልሁ በኋላ ስለ "ማሕበረ ቅዱሳን" ትንሽ ልበል፤ እንደሚታወቀው ማሕበሩ ምንም እንኳን እራሱን ቅዱስ ቢልም ተግባሮቹ ግን ይኸው እዚህ ጽሁፍ ላይ የምናያቸው ስለሆኑ የማሳስበው ብዙ ጥሩ ተግባሮቹን እነዚህ የስም ማጥፋት ዘመቻወቹ ስላበላሹበት እባካችሁ ይታረሙ። በቅርቡ አቶ ሙሉጌታ በሰጠው ቃለ ምልልስ አስታኮ በዲያቆን ዳነኤል ክብረት የወጣው የድርጅቱ ገመና ብዙ ያበላሸ የመስለኛል። ጸሐፊው እንዳለው ማሕበሩ በከፍተኛ አመራር ጭምር በፖለቲካ አገዛዙ ስር ያሉ አባላት ስላሉትና ካለውም አገዛዝ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በመስራት ላይ በመሆኑ (እኔ ያልሁት አይደለም በራሱ አመራር አባላት የተጠቀሰ ነው) ብዙ ንጹሐን ተራ አባላት፣ በእውነት ለዚሕች ቤተክርስቲያን ለማገልገል የተነሱ ስላሉ እርምት ማድረግ፣ ብሎም የተላበሰውን መጥፎ ገጽታ መቀየር ሲገባ፣ ሌላ የስም ማጥፋት ዘመቻ መጀመር ተገቢ አይደለም። የኔን ብጤወች ጥሩ ብዙ ተግባራት ያረጋል በማለት የሚጠብቁ፣ እንዲህ የከፋ ሰይጣናዊ ስራ ሲያዩ ያዝናሉ። ለዛሬ ይህን ካልሁ ይበቃል። ስለ ቅዱስ ሚካኤል ማንም ሌላ ደብር የሄደ አይወስንም። አባላቱ ብቻ ናቸው ይሁንም አይሁንም ሊሉ የሚችሉትና ባትደክሙስ? ቸር ያሰማን
ReplyDeleteዲ/ን ወንድወሰን
ReplyDeleteበዛሬ ዘመን በጣም የሚቸግረው ሳይመረጡ አራሳቸውን ዲያቆናት፣ ሰባክያን፣ ካሕናት፣ ጳጳሳት ብለዉ ሠይመዉ በእግዚአብሔር ምርጫ እና ፈቃድ ነው በማለት አያወናበዱ ለሰዎች መሰናክል በመሆን ቅድስት ቤተክርስትያንን የሚያዉኩ በመብዛታቸዉ ነዉ። (1 John 2:19 ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።)
mr. andualem by the way who are you and who gave you all this pawer to spend our money the so cold board good for you. dallas micheal will ask u one day........how money kess or aba and zemari u will bring for the next 3 month u teaching the holly bible for dallas sunday mass or for u good luck
ReplyDeleteእውነተኛ ከሆናችሁ ስም ከማጥፋት ይልቅ ስምን መግለጽ። እኛ ወንጌልን ይዘን ወደፊት ነው እውነትን እንናገራለን አንፈራም ። ኦርቶዶክስነታችን በወሬ ሳይሆን በተግባር ነው እናንተ ሰላላችሁ ኦርቶዶክስነታችን አይቀየርም። ስሜም ዲ/ን ወንድወስን ዛኦርቶዶከስ ነው። እንዳገለግለው የመረጠኝ አምላክ ስሙ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ የተመሰገነ ይሁን። አባ ወልደ ትንሣኤ እንደ ስማቸው ብርሃን ናቸው በወሬ ሳይሆን በተግባር ከወንድሞቻቸው ጋር ዓለምን ሁሉ በወንጌል ጎርፍ እያጥለቀለቋት ነው። የእናንተ ተግባር ደግሞ ቤተ ክርስትያንን በጥፋት ጎርፍ ማጥለቅለቅ እና ማጥፋት ነው።
ReplyDeleteዲ/ን ወንድወሰን
‘እኛ ፍጥረቱ ነንና እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርሰቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።” ኤፌ.፪፥፲
SELAM TEWAHIDO I AM ONE OF THE PRIEST FROM ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH . I AM LIVING IN ARIZONA . IAM READING YOUR INFORMATION THAT YOU ARE POSTING ON YOUR WEBSITE BUT I FELL BAD BECAUSE YOU GUYS THE NAME OF THE WEBSITE IS VERY GOOD BUT SOME INFORMATIONS ARE UNBELIEVIBLE JUST DEFAMING AND COMPLAING. GUYS PLEASE WRITE GOSPEL, SAINTS STORY LIKE THAT . YOU ARE BLAMING ABA WOLD TENSAE ,WHAT IS HIS FAULT ? IF THERE IS PROBLEM PRAY FOR HIM . I KNOW HIM I DID NOT GET DIFFERENT TEACHING HE IS ALAWAYS REFERE FETAH NEGEST INSTEAD OF BLAMING HIM GO AND READ THE FETA NEGEST. GUYS PLEASE PLEASE WHY WE ARE BITTING EACH OTHER LIKE DOGS ? ARE WE CHRISTIANS? NO YOU ARE IN THE SIDE OF MEHIBER KIDUSAN . MK HAS ITS WEAKNESS GO AND WRITE ITS WEAKNESS TOO INSTEAD OF WRITING ABA WOLDE, DN ANDULALEM MEMHIR LEUL KAL . I AM NOT IN THE SIDE OF THESE PEOPLE BUT YOU ARE STUGGLLING FOR GROUP OR MK. I DO NOT CARE THAT YOU POST OR NOT
ReplyDeletehi guys you are under saint teklahimanot church. this chuch is ruled by aba poulos you said aba poulos is illegal pope .why you complain saint micheal bouard they have apower to invite every priests, deacons etc... if you want learn come and learn when the great man , aba wolde coming.
ReplyDeleteአንተ ግን ዘማሪው ዲ/ን ወንድወሰን ነህ ወይስ ሌላ ቀጣፊ ?
ReplyDeleteመቼም ያ የቤ/ክንን ጣዕመ ዜማ የሚያሰማን አይደለም፡፡
ምነው ስምህን ወንድወሰን ከሚሉ ጉዳንጉድ ወይም ጉዲት ቢሉት
አይ እናት ልጅ የወለዱ መስላቸው ለካ ተኩላ ነበርክ፡፡
ከእኔ ጋራ ልዑለቃል ለአጭር ጊዜ እንተዋወቃለን እቤቱ ሄጄ ነበር ምንም ሙሉ ወንጌል መሆኔን ቢያዉቅም እቤቱ ገብተን የእኛ ፓስተር ጸሎት ካደረሰ በሀላ ልዑለ ቃል ያስተማረንን አንረሳዉም በመደምደሚያዉም እኛ ምንም መናፍቅ ብንባል ያለንን እዉነት በቤተ ክርስቲያናችሁ ልናስተምር እንፈልጋለን ስንለዉ በመገረም ጀርባችንን መታመታ በማድረግ እንኮን ለእናንት ለእኛም አልተታለም እናንተስ ትንሽም ቢሆን የመዳን ተስፋ አላችሁ ኦርቶዶክሳዉያን ግን ገና ብዙ ይቀራቸዋል እኛም ብዙ መስራት ይቀረናል ብሎኝ ነበር ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ ማስተማሩን ያስተምር ነገር ግን ቃሉ እንደሚለዉ ተሰዉሮ የሚነገር ትምህርት ስለሌለ እራሱን ገልጦ ስለክርስቶስ ተጠልቶ ተሰድቦና ተገፎ ኢየሱስን መስክሮ ወደኛ እንዲመጣ ያስፈልጋል ጊዜዉ አሁን ነዉ በሉት ባይሰማችሁ ግን በጌታዉ አፍሮልና ጌታህ ያፍርበሐል በሉልኝ + + + + + + + + + +
ReplyDelete