ሰላም ተዋሕዶ - ትምህርታዊ የሆኑ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፤ ዘገባዎችን ፤ በሕብረተሰባችንና በሌላው ዓለም ሕዝብ ባህልና ሕይወት ውስጥ የሚመላለሱ ወጋወጎችን የምታስነብ አስተማሪ ፤ አዝናኝና ቁም ነገር አዘል ብሎግ ናት፡፡Blogging Since Oct 2009
Wednesday, August 24, 2011
Tuesday, August 23, 2011
Tuesday, August 16, 2011
የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲያቆን አንዱአለም መሪነት ወደ ስደተኛው ሲኖዶስ እየሔደ ነው!
‹ከሥጋው ጾመኞች ነን ከመረቁ አውጡልን› በሚል አቋም የኢትዮጵያውንም ሆነ ስደተኛ ሲኖዶስ ነኝ ብሎ አሜሪካ የተቀመጠውን አንቀበልም ፤ ነገር ግን የምንከተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነትና ሥርዓት ነው ፤ በማለት የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በዚህ አቋሙ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያኑ የቀድሞ አስተዳደር ቦርድ አቋሙን እንደገና በማሻሻል ከጥቂት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ አይሰደድም፤ሲኖዶስና መንበሩ ያለው አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ነው፡፡ሕጋዊው ፓትርያርክም አባ ጳውሎስ ናቸው፡፡ የዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንም የኢትዮጵያውን ሲኖዶስ ሕጋዊነቱን ያምናል፤ ይቀበላል ፡፡ ነገር ግን አባ ጳውሎስ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ይልቅ በማይመለከታቸውና ሃይማኖቱ በማይፈቅድላቸው ሁኔታ የገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ ተግባር ወኪልና አስፈጻሚ ሆነው እያገለገሉ በመሆናቸው አስተዳደራቸውን አንቀበልም ፤ በማለት የቆየ አስተዳደር ነበር፡፡
Wednesday, August 10, 2011
Sunday, August 7, 2011
ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን ! መዝ 123፡7
ቤተ ክርስቲያን የገጠማትን አስቸጋሪ ፈተና ለመጋፈጥና ስለ ቤተክርስቲያን መከራን ለመቀበል ገና በወጣትነት እድሜያችሁ ከትምህርትና ከልዩ ልዩ የሥራ ገበታችሁ ላይ ተጠርታችሁ ለቤተ ክርስቲያን ጠበቃ በመሆን ለቆማችሁ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ !
ሰይጣን በማኅበራችሁ የሥራ አመራርና በዲያቆን ዳንኤል ላይ ያጠመደውን የመለያየት ወወጥመድ እንባና ይቅርታ በተዋሐደው የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ውይይት መፈታቱን ከደጀሰላም በመስማታችን እኛምን ተደስተናል ፡፡ ሰላሙንም ዘለቄታዊ ሰላም ያድርርገው፡፡ አገልግሎታችሁንና ለቤተክርስቲያን ሥርዓትና ዶግማ መጠበቅ የምታደርጉትን ተጋድሎ ሁሉ ከልብ እያደነቅን እግዚአብሔር የአገልግሎታችሁን ጸጋ እንዲያበዛላችሁ ሰላም ተዋህዶ ከልብ ትመኛለች፡፡
Monday, August 1, 2011
ከተሐድሶ ዓላማዎች አንዱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓውደ ምሕረትና የዘፈን ቤት መድረኮች አንድ ዓይነት ገጽታ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው !
የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሁለ ገብ ተሐድሶ ያስፈልጋታል ብሎ ለጥፋት የተነሣው ኢኦርቶዶክሳዊ ድርጅርት ዓላማውን ለማሳካት በሥውር ከሚንቀሳቀስባቸው ዘዴዎቹ አንዱ ባልነበሩበት መንፈሳዊ ሕይወት መነኩሴ ፤ ቄስና ባሕታዊ እየመሰሉ አስነዋሪ ድርጊቶችን በአደባባይና ሰው በሚታይባቸው ቦታዎች በመፈጸም ሕዝቡ ካህናትንና ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲጣላ ማድረግ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ‹እኔ ድሮ ቄስ ነበርኩ ፤ መነኩሴ ነበርኩ ፡ አሁን ግን ጌታን ተቀብያለው እያሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ግራ በማጋበት የፕሮቴስታንት መንፈስ ሰለባዎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡
ይህ በፎቶግራፍና በቪዲዮ ምስሉን የምታዩት ዘማሪ ‹ ድሮ በገዳም በቀን አንድ ጊዜ ጥራጥሬና የሻገተ እንጀራ እየበላው በገዳም ውስጥ በጾምና በጸሎት እኖር ነበር፡፡ አሁን ግን ያንን ትቼ ባሻኝ ሰዓት እየበላሁ ለጌታ ዘማሪ ሆኛለሁ › ፤ የሚለው ናትናኤል የተባለው የፐሮቴስታንት ዜማ አቀንቃኝ ነው፡፡
አስቀድሞ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ያከበራቸው ጻድቃን ክብራቸው በሰዎች አንደበት የሚጨመርና የሚቀነስ ባይሆንም መናፍቁ ዘማሪ የጻድቃንን ክብር በዝማሬው ለመቀነስ ሞክሯል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)