Thursday, February 25, 2010

ምሁራኑ ባልና ሚስት ተራቡ ! የቤተክርስቲያኒቱንም ካዝና ከበቡ !

 በኢኮኖሚክስ እንጀራ ያልተበላበት ዶክትሬት ያላቸው ዶክተር ግርማና በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ ባለሙያ የነበሩት ባለቤታቸው ወ/ሮ ዙሪያሽ በሙያቸው ከሚሠሩበት ካምፓኒ ከተባረሩ ከራርመዋል ፡፡ ዶክተሩም ባለባቸው በወዝ ሠርቶ የማግኘት ስንፍና ምክንያት የጀመሩትን የታክሲ ሥራ እንጀራዬ ብለው ጠንክረው መሥራት አልቻሉም፡፡ስለዚህ ችግር በቤታቸው ውስጥ ዘመድ ሆኖ መኖር ከጀመረም ሰነባብቷል፡፡ በዚህ የተነሣ የቅርብ የሆኑ ወዳጆቻቸው ገንዘብ በማዋጣት ቢደጉሟቸውም ዘለቄታዊ አይደለምና ኑሮ  እጅግ ከብዶባቸዋል፡፡  

Tuesday, February 16, 2010

‹ከዚህ የመጨረሻ ዕድል በኋላ ግን እጃችንን አጣምረን አንቀመጥም ! መረጃዎቻችንን ይዘን የ I.R.S ን በር እናኳኳለን ! ሕዝቡ ግን ያን ጊዜ ይህ ለምን ሆነ እንዳይለን !

ሰላም ተዋሕዶ በአስተዳደር ቦርድ ጤናማ ያልሆነ አሠራር ችግር ምክንያት የተናጋውን የቤተክርስቲያኗን ሰላም አስመልክቶ የችግሩን ምንጮችና ለዚህ አስተዋጽዖ ያበረከቱትን ግለሰቦች በግልጽ ከመተቸት ጀምሮ ምእመናኑ እንዲገነዘቡትና በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ምን እየተደረገ እንደሆን ከውስጥ የምታገኘውን መረጃ መሠረት በማድረግ ስታሳውቅ መቆየቷ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ በመሄዱና ሕዝበ ክርስቲያኑ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሠጠውም ገንዘብ ያለይሉኝታ እየተዘረፈና ምሥጢሩም አደባባይ እየወጣ በመውጣቱ ድርጊቱ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ተቆርቋሪዎች ነን የሚሉትን ሁሉ አበሳጭቷል ፡፡ አስቆጭቷል፡፡

Monday, February 1, 2010

የሂሳብ ሹሙ በገንዘብ ወንበር ላይ መቀመጥ ምስጢሩ ምንድን ነው ?

ሂሳብ ሹሙ ሊቀመንበር ለመሆን ያደረጉትን የትግል መሥመር ቀይረው በቦታቸው ላይ ለመቆየት መወሳነቸው ሁለት ነገሮችን ያመላክታል፡፡

1.ቦታውን ለማገኘት ያደርጉ የነበረው ትግል በአደባባይ ተደጋግሞ በመነገሩና ምሥጢሩ በብሎግም ላይ በመውጣቱ የዚህን እውነታ መንገድ ለማስቀየርና የተባለው ነገር ሁሉ ውሸት ነው ተብሎ እንዲነገር ለማድረግ ነው፡፡( ይህ አይነቱ ዘዴ ደግሞ ከፖለቲካዊ ጫወታዎች አንዱ ነው፡፡)

2.እርሳቸው የተማሩና የከተማ ልጅ (አራዳ) በመሆናቸው በዋና ዋናዎቹ የሥልጣን ቦታዎች ላይ የገጠር ሰዎችንና ያልተማሩ ሰዎችን በማስቀመጥ ቦርዱን ባሉበት ቦታ ላይ ሆነው እንደፈለጉ ለማሽከርከርና የገንዘብ ጥማታቸውን በዘዴ ለማርካት ነው፡፡