ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ምርጫ ለማካሄድ ሲጣደፍ የሰነበተውን ቦርድ ከዚህ ተግባሩ ለማስቆም በከሳሾቹ በኩል የተጠራውን ችሎት ጉዳዩ እንዳይሰማና ችሎቱ እንዳይቀጥል የቦርዱ ጠበቃ አጥብቆ የተማጸነ ቢሆንም ዳኛው ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ችሎቱ እንዲቀጥልና የካሳሾች ጠበቃ ጉዳዩን እንዲያቀርብ አዟል ፡፡
ቀደም ሲል አዲሱን ባይሎው የቦርድ ጠበቃ ከሕግ አንጻር ብቻውን ያለ ሕዝብ ድጋፍ ማጽደቅና ሥራ ላያ ማዋል የሚያስችለውን በሕግ የተደገፈ ማሥረጃ እንዲያቀርብ፤ በአንጻሩም ደግሞ የከሳሽ ጠበቃም እንዲሁ ቦርዱ ብቻውን ማጽደቅና በሥራ ላይ ማዋል የማያስችለውን ማስረጃ ከሕግ አንጻር እንዲያቀርብ ለሁለቱም የጊዜ ገደብ የተሠጠ ቢሆንም የቦርዱ ጠበቃ የታዘዙትን በወቅቱ ባለማቅረባቸው አሁንም እንደገና እሰከ ዲሴምበር አጋማሽ ድረስ እንዲያቀርቡ ዳኛው በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘው እስካሁን መሠረታዊና ዋና ወደ ሆኑት ክስ ዝርዝሮች ውስጥ ስላልተገባ ዳኛውም አዲስ ወጥቷል የተባለውንና የድሮውን ባይሎ በሚገባ አጢነው ከወር በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ውሳኔ እንደሚሠጡበት በማሳወቅ እስከዚያ ድረስ ግን ምርጫው እንዳይካሄድና እንንዲቆይ ውሣኔ ሰጡ፡፡
ይሁን እንጂ የቦርዱ ጠበቃ መልሶ መላልሶ ምርጫው ከዚያ በፊት እንዲካሔድ የልመና ያህል ቢማጸንም ዳኛው ‹መብታችን ተረግጧል የሚሉ አባላት እያሉ እንዴት ነው ምርጫው ይካሄድ የምትለው በማለት በቁጣ ቃል ጭምር ተናግረው ምርጫው እንዳይካሄድ ቢያግዱም የቦርድ ጠበቃ ዳኛው እስኪናደዱ ድረስ ‹ እሺ በድሮ ባይሎም ቢሆን ምርጫው ይካሄድ › በማለት በሽማግሌ አንደበቱ ቢማጸንም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡ የሚገርመው ነገር በመጀመሪያው ቀን ችሎት ‹ይህ ባይሎአችን አይደለም አናውቀውም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ የካደውን የድሮ ባይሎ ግራ ቢገባው እሺ በእሱም ቢሆን ምርጫው ይካሄድ ማለቱ ዳኛውን ጨምሮ በሥፍራው የነበሩትን ሁሉ አስገርሟል፡፡ በእድሜው አረጋዊ የሆነው የቦርድ ጠበቃም በዚሁ ችሎት አንድ ወጣት ጠበቃን በረዳትነት ይዞ መምጣቱ ታውቋል፡፡
የቦርድ ጠበቃ ከመጀመሪያው ችሎት ቀን በቀር የአስተዳደር ቦርዱን ያስደሰተበት ቀን የለም፡፡ይህም የከሳሾች ጠበቃ ክሱን ለማጠናከር እንዲረዳው አንዳንድ ዶክመንቶች ከቤተ ክስቲያኑዋ እንዲሰጡት ቢጠይቅም ዳኛው ‹ ክስ ለመመሥረት ዶክመንት የግድ ከቤተክርስቲያን ማግኘት የለብህምና አለመስጠት መብታቸው ነው፡፡› ስላለው የአስተዳደር ቦርዱ ‹ክሱን ውድቅ አድርገን ፋይሉንም አዘግተንና አሸንፈን መጣን ፤ ሚካኤል አሸነፈ፡፡› በማለት በከተማ ውስጥ ሲዘፍኑና ሲጨፍሩ እንደሰነበቱ ይታወሳል፡፡ በቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረትም ሊቀመንበሩ ወጥተው ይህንኑ ማወጃቸውም አይዘነጋም፡፡
ከዚያ ወዲህ ግን የክሱ መጀመርና የእውነት ቀስ እያለች እየታየች መምጣት በውሸት የተካኑትን የአስተዳደር ቦርድ አባላት እያስደነገጣቸውና እያሳሰባቸው ስለመጣ ጠበቃቸውም እንደበፊቱ እነሱን ለማስደሰትና ለማስፈንጠዝ ባለመቻሉ አዲስ ዘዴ መፍጠር ግድ ነበረበት ፡፡
ይህም ፍርድ ቤቱን እውነት በሚመስል ነገር ተከራክሮ የከሳሾቹንም ጠበቃ በመርታት ጉብዝናውን ለቦርድ እንደ መጀመሪያው ቀን ማሳየት ነበረበት፡፡ ስለዚህ ዘጠኙንም የቦርድ አባላት ቢሮው በመጥራት ‹እየተከሰሳችሁ ያላችሁት ጉዳይ አንዱ በባይሎው መሠረት አትሠሩም› ተብላችሁ ነውና ኖቬምበር የቤተክርስቲያናችሁ የአስተዳደር ቦርድ የምርጫ ወር ነውና ወሩ ሳያልፍ ምርጫውን አካሂዱ፡፡ እናንተ ግን ተመልሳችሁ ባትገቡ መልካም ነው፡፡ ይህ ከሆነ ምርጫው ያለችግር ተከናውኗል፡፡ነባሮቹም ወጥተው አዲሶች ገብተዋል› በማለት ዳኛውን ማሳመን ይቻላል ብሎ መከራቸው፡፡
ይህ ዘዴ ግን ሳይታሰብ በአስተዳደር በርዱ ላይ በቡድን መከፋፈልን አመጣ፡፡ ዋና ጸሐፊውና እቃ ክፍሏ ከቦርድ መውጣትን ስለማይፈልጉ በጠበቃው ምክር አልተደሰቱም፡፡ ሂሳብ ሹምና ገንዘብ ያዡ ደግሞ በቦርድ ውስጥ ኃይል እንዲበዛላቸውና ደጋፊዎቻቸው ከሆኑት ከወላጅ ኮሚቴ ሰዎች ተመርጠው እዲገቡላቸው የጠበቃውን ሃሳብ በጽኑ በመደገፍ የራሳቸውን እጩዎች ለማስመረጥ ተዘጋጁ ፡፡ ሁሉም ግን እንዳይሆን ሆኖ ቀረ፡፡
እነዚህ ሠዎች ሥጋውያን ናቸው ፡፡እግዚአብሔርን በስም እንጂ በአምልኮ አያውቁትምና የሚያስቡት ሁሉ አይሳካካለቸውም !
No comments:
Post a Comment
አስተያየት