Monday, November 23, 2009

የከሳሾችና የፖሊስ ፍጥጫ

የአስተዳደር ቦርዱ ሕግን በመጣስና የቤተክርስቲያኑን አባላት መብት በመግፈፍ በአባላት ተከሶ ፍርድ ቤት ከቆመ ማግስት ጀምሮ ከሥራ ሰዓታቸው ውጭ የሆኑ የጋርላንድ ፖሊሶችን በሰዓት እየቀጠረ በዕለተ እሁድ በቤተክርስቲያኑ ማቆም ከጀመረ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡

ይህ ጉዳይ በከሳሾቹ ክስ ዝርዝር ውስጥ ተካቶ ቦርዱ ያለአግባብ አባላትን ከስብሰባ አዳራሽ በፖሊስ ማስወጣቱ ለከፍርድ ቤቱ የቀረበና በክቡር ፍርድ ቤቱ የሚታወቅ ቢሆንም ቦርዱ ፖሊስ ያቆምነው የትራፊክ መጨናነቅን ለማስቀረት ነው በማለት መዋሸቱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ አስተዳደሩ ለትራፊክ ሥራ የመጡ ናቸው ያላቸውን ፖሊሶች ከቅዳሴ በኋላ ሕዝቡ ጸበልና ጸዲቅ ለመቅመስ ወደሚገባበት የመመገቢያ አዳራሽ በመላክና ሰርቆ የጠፋ ሌባ የሚፈልጉ ይመስል በሕዝቡ መካከል እንዲሽሎከለኩ መደረጉ የብዙ ክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ስሜት እያወከ ነው፡፡

ባለፈው ኖቬመበር 11 የዋለው ችሎት ምርጫው እንዲታገድ ሲያደርግ ቦርድ ያወጣው ሕግ ትክክለኛ ነው ሲል የሕግ ድጋፍ ማስረጃ እንዲያቀርብ የቦርዱ ጠበቃ ሲጠየቅ የካሳሾችም ጠበቃ ከሕግ አንጻር የሚቃወምበትን ማስረጃ እንዲያቀርብ መጠየቁም ይታወሳል ፡፡

በዚህ መልኩ የከሳሾች ጠበቃ ለሚያቀርበው ማስረጃ ከሳሾች ቦርዱ ያወጣውን አዲስ ሕግ የሚቃወሙትንና የደጋፊዎቻቸውን ሥምና ፊርማ በነጻነት ማሰባስብ ይችሉ ዘንድ የሚያሳውቅ ደብዳቤ ለቦርዱ በጠበቃቸው በኩል መላኩን ለማወቅ ተችሏል፡፡በዚህ መሠረት ከሳሾች ይህንኑ ቦርድ ያወጣውን አዲስ ባይሎ የማይደግፉትንና የሚቃወሙትን አባላት ሥምና ፊርማ የማሰባሰብ ሥራን ጀምረዋል፡፡

ይሁን እንጂ ትናንት እሁድ November 22 2009 የቦርዱ ጸሐፊ ከቅዳሴው በኋላ በቤተ መቅደስ ውስጥ ወደ ነበሩት ወደ አንድ የካሳሾ ወገን በመሄድ ‹አንድ ጊዜ ስለምፈልግህ ና ተከተለኝ › በማለት ተከትለዋቸው ሲወጡ ‹ ሕገ ወጥ ሥራ እየሠራ ነውና አስወጣው› በማለት በር ላይ ለነበረውን ፖሊስ ትእዛዝ ከሰጡ በኋላ የውጤቱን መጥፎነት በመፍራት ወዲያው ከአካባቢው በመሠወር ቢሮአቸው ገብተው ተቀምጠዋል፡፡

የጸሐፊው ትዕዛዝ የደረሰው ፖሊስም ‹ ግለሰቡን ባለ ንብረቱ ንብረታቸውን ለቀህ እንድወጣ ስለጠየቁ ለቀህ ውጣ በማለት ለማስወጣት ቢሞክርም ፖሊሱ ከከሳሽ ወገን ከሆኑትን ግለሰብ ንብረቱ የሳቸውም እንዲሁም እዚያ የተሰበሰበው ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ የጋራ ንብረት እንደሆነና ፖሊሱ ማንንም ማስወጣት እንደማይችል በሰነዘሩበት ጠንካራ ሕጋዊ ተቃውሞ መሠረት ትእዛዙን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይችል ቀርቷል፡፡ ግለሰቡም ተመልሰው ወደ መመገቢያ አዳራሹ በመግባት በተረጋጋ መንፈስ ሥምና ፊርማ የማሰባሰብ ሥራቸውን እንደቀጠሉ ለማየት ተችሏል፡፡

ጉዳዩን ወዲያውኑ የሰሙት ዋና ከሳሽዋም ከሌሎች ደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆንና ወደ ፖሊሱ በመሄድ ‹የአንተ ሥራ መኪና መጠበቅ እንጂ በንብረታችን ላይ መጥተህ ማንንም ውጡ ብለህ ማዘዝ አትችልም ፡፡ የተፈጠረ ችግር የለም ፡፡ ችግር ቢፈጠርም እንኳን በሥራ ላይ ያለ ፖሊስ ጠርተህ እርሱ ጉዳዩን እንዲከታተል ተደርጋለህ እንጂ ከሕጉ አንጻር አንተ ከዚህ ቤተክርስቲያን ማንንም ለማስወጣት መብት የለህም› በማለት ፖሊሱ የሠራው ሥራ ስህተት እንደሆነና ትዕዛዝ የሠጠው የቦርድ ጸሐፊም ከነግብራበሮቹ ሕግ በመጣስ ክስ፤በሕግ እጅ ውስጥ እንዳለ በመግለጽና በማስረዳት ፖሊሱን ይቅርታ እንዲጠይቅ አድርገውታል፡፡

ከዚህ አንጻር ከሳሾቹም በቤተክርሰቲያኒቱ ውስጥ እንደማንኞቹም አባላት ሁሉ ባለ ሙሉ መብት መሆናቸውን በግልጽ አረጋግጠዋል፡፡ በርቀት ሆኖ ጉዳዩን የሚከታተለው ቦርድም ሤራው እንደከሸፈበት ሲያውቅ ወዲያውኑ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ እንደተቀመጠም ለማወቅ ተችሏል፡፡

1 comment:

  1. Could it be 'a' simple misunderstanding among all parties, the secretary, the member and the police man?
    As we see what kind of pressure the secretary has(in-&-out), I also do agree that every member could have hard time to exercise his/er right at the current situation.

    let's make it work together_no hard feeling!

    Peace and love for all of us.

    ReplyDelete

አስተያየት