የአስተዳደር ቦርዱ እንደ ቦይ ውሃ ማንም ሲነዳው ባይነዳ ፤ እራሱን ችሎ በማስተዋል እያሰበ ቢሠራ፤ አባላቱን ሁሉ በእኩልነት የሚመለከትበት ያልተጠናገረ ጤናማ ዓይን ቢኖረው፤ማኅበረ ቅዱሳንን ከቤተክርስቲያን አጠፋለሁ ብሎ ባይነሣ፤እልኸኛ ባይሆን፤እንዲያገለግል የተመረጠው ቤክርስቲያንን እንጂ ቀበሌን አለመሆኑን ቢያውቅ ኖሮ፤ተው ሲሉት የነበሩትን አማካሪ ሽማግሌዎቹን ቢሰማ ኖሮ ፤ ውሸታም ሆኖ በፍርድ ቤት ፊት ሳይቀር ባይወሻክት ኖሮ ወ.ዘ.ተ.. እዚህ ሁሉ ማጥና ቅሌት ውስጥ አይወድቅም ነበር፡
ሰላም ተዋሕዶ - ትምህርታዊ የሆኑ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፤ ዘገባዎችን ፤ በሕብረተሰባችንና በሌላው ዓለም ሕዝብ ባህልና ሕይወት ውስጥ የሚመላለሱ ወጋወጎችን የምታስነብ አስተማሪ ፤ አዝናኝና ቁም ነገር አዘል ብሎግ ናት፡፡Blogging Since Oct 2009
Wednesday, November 25, 2009
Monday, November 23, 2009
የከሳሾችና የፖሊስ ፍጥጫ
የአስተዳደር ቦርዱ ሕግን በመጣስና የቤተክርስቲያኑን አባላት መብት በመግፈፍ በአባላት ተከሶ ፍርድ ቤት ከቆመ ማግስት ጀምሮ ከሥራ ሰዓታቸው ውጭ የሆኑ የጋርላንድ ፖሊሶችን በሰዓት እየቀጠረ በዕለተ እሁድ በቤተክርስቲያኑ ማቆም ከጀመረ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡
Friday, November 20, 2009
ምኞት አይከለከልም !
አስተዳደር ባላዋቂ ሰዎች ሲያዝ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ዝርዝር ጉዳይ አይስፈልገውም ፡፡ ውጤቱም በዓይን የታየ ስለሆነ ይህ አባባል ግራ የሚያጋባ አይይደለም፡፡
Tuesday, November 17, 2009
ንቁ ! ስለ ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም እወቁ !
የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቦርድ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ ችግር ውስጥ መውደቅ ፤ የምርጫው በሕግ መታገድና የአስተዳደር ቦርዱ መፍረክረክና አቅም ማጣት በቤተክርስቲያኗ ላይ ከፍተኛ ችግር ለመጋረጡ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡
Monday, November 16, 2009
ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለ ዕዳው አይሸከመውም !
ክህነትን አክብሮ ለመረጣቸው ሰዎች የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፡፡ ክብሩም ታላቅና ዘለዓለማዊ ነው፡፡ከእግዚአብሔር በተሰጠ የክህነት ስልጣን ሕዝብ ይገለገላል ፤ ይባረካል፡፡የሰው ልጆች በደልና ኃጢኣትም በክህነቱ አገልግሎት ይሥተሠረያል፡፡ከዚህ አንጻር የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ለካህናት አባቶች ከፍተኛ አክብሮት አለን፡፡
Thursday, November 12, 2009
የቦርድ ሕግ አማካሪ ምርጫው እንዲካሄድ ዳኛውን አጥብቆ ለምን ተማጸነ?
ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ምርጫ ለማካሄድ ሲጣደፍ የሰነበተውን ቦርድ ከዚህ ተግባሩ ለማስቆም በከሳሾቹ በኩል የተጠራውን ችሎት ጉዳዩ እንዳይሰማና ችሎቱ እንዳይቀጥል የቦርዱ ጠበቃ አጥብቆ የተማጸነ ቢሆንም ዳኛው ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ችሎቱ እንዲቀጥልና የካሳሾች ጠበቃ ጉዳዩን እንዲያቀርብ አዟል ፡፡
ከዚህ የተሻለ ጊዜ የለም !
የቤተ ክርስቲያንቱን ሕጋዊ ህልውና ለማስከበርና የአባላቱንም መንፈሳዊ መብት ለማስጠበቅ ስትሉ ከሕገ ወጦቹና ከአምባገነነኖቹ የቦርድ አባላት ጋር እየታገላችሁ ላላችሁት እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ፤ ሰላም ተዋሕዶ ከፍተኛ አክብሮቷን ትገልጻለች ፡፡
ዲሞክራሲያዊ የተባለው የአስተዳደር ቦርድ አባላቱ ምርጫ ፉርሽ ሆነ !
ዘመናቸውን በጨረሱ ሦስት የአስተዳደር አባላት ምትክ ምርጫ አካሂዳለሁ ብሎ በመረጣቸው የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት በኩል ዲስኩር ሲያስነፋ የሰነበተው የአስተዳደር ቦርድ ምርጫውን እንዳያካሂድ ዛሬ NOV 11 2009 የዋለው ችሎት አገደ፡፡
Sunday, November 8, 2009
የቦርድ አባላቱ ምርጫ ይካሄዳል ወይስ ምኞትና ወሬ ሆኖ ይቀር ይሆን ?
የአስተዳደር ቦርዱ በራሱ ያዘጋጀውንና አባላት ያላጸደቁትን አወናባጅ ባይሎውን መሠረት አድርጎ ዘመናቸውን በጨረሱ ሶስት የቦርድ አባላት ምትክ አዲስ አስመርጣለሁ ብሎ መከራ እያየ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡ ታዲያ ይህ ምርጫ ፤ ቦርዱ በሚፈልገው መንገድ ይሳካለት ይሆን? ይህንን ጥያቄ የሚመልሰው የረቡዕ ኖቬምበር 11 2009 የ 9.00 amu የፍርድ ቤቱ ችሎት ይሆናል ፡፡ የእውነት አምላክ ፍርዱን በቶሎ ያሳየን ፡፡
አሜን
Tuesday, November 3, 2009
ይህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ነው
በብዙ የተመሰቃቀለና የተበላሸ የአስተዳደር ሥራ ውስጥ ገብቶ የሚዳክረው ቦርድ ጨርሶ ቤተ ክርስቲያኑዋን ለማስተዳደር እንዳቃተው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ፡፡ ከእለት ወደ እለት ከመታረም ይልቅ ጥፋትን እንደ ሥራ የተያያዙት የቦርድ አባላቱ ከምርጫው ወሬ ዋዜማ ጀምረው በወደቀ አጥንት እርስ በእርስ እንደሚናከሱ ውሾች በቡድን ተከፋፍለው እርስ በእርሳቸው ሲባሉና በሃይለኛ የቃላት ጥይት ሲጠዛጠዙ እንደሰነበቱ ተገለጸ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)